ጎንደር እንግዳዋን ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂን ነገ እልል ብላ መቀበል ይኖርባታል።

ጎንደር እና ነገ።
„አግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
መዝሙረ ዳዊት ፳፮ ቁጥር ፲፬
ከሥርጉተ©ሥካሴ
 08.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ



ነገ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጎንደርን እንደሚጎበኙ እዬተነገረ ነው። እኔ ያልወደድኩት የአማራ እና የኤርትራን የብቻ ለብቻ ግንኙነት እንጂ ማዕካላዊ መንግሥት በሚመራው ከሆነ መልካም ነገር ነው። ጠ/ሚር አብይ አህመድም አብረው እንዲመገኙ አዳምጫለሁኝ። አንዲት ሉዑላዊት አገር ከጎረቤት አገሮች ጋር የሚኖራት ግንኙነት በዚህ መልኩ ነው መከወን ያለበት። በስተቀር ሥርዓተ አልበኝነት እና ፍንገጣ ይመጣል። መርሁም አይፈቅድም። ቤተሰባዊ ትውፊቱ ሆነ ትሩፋቱ ግን ያው እንደ ተጠበቀ ሆነ። ምናችን ይለይ ነበር። DNN የሁለታችንም አንድ ዓይነት እኮ ነው። መለዬት አያችልም።  

በነገው ጉብኝት ላይ የወልቃይት እና የጠገዴ ሆነ የራያ እና የመተከል ጥያቄዎችን መፈክር ይዞ መውጣት በፍጹም የተገባ አይደለም። እንግዳ ለማስተናገድ እንደ አባት አደሩ የበሞቴ አፈር ስሆን ጉርሻ የፍቅር እንጂ ሌላ መሆን አይኖርበትም። የተገባው የህዝቡ ጥያቄ ባለፈው ጊዜ ወጥ በሆኑ ሁኔታ ከ10 ባለነሱ የአማራ ክልሎች ቀርቧል። ከዚህ በላይም በተለያዬ ሁኔታ በግልም በጋራም አቅርበናል።

አሁን እንግዳ ነው የሚመጣው። እንግዳ በአባባ በጉዝጓዝ፤ በመና ዳቦ፤ በሳቅ፤ በፈገግታ በደስታ ነው አቀባበል መሆን ያለበት። ቀደም ብዬ በተከታታይ እንደ ተናገርኩት የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ሰላም መሆን ከማንም በላይ ለጎንደር ነው ተጠቀሚ የሚያደርገው። ምክንያቱም ከፋኝ ያለው ሁሉ መሸጋገሪያው ጎንደር ነው። ምሽጉ ደግሞ ኤርትራ ነው። ኤርትራን ማግኜት ያልቻለ ሁሉ ቁንጫኑን የሚወጣው በጎንደር ላይ ነው። በዚህም የጎንደር እናት ዓመት ይዞ እሰከ ዓመት ድረስ የልጅ ዋጋ ከፍላለች።

ጎንደር ከ50 ዓመት ሙሉ በጦርነት ስትናጥ ኖራለች። ከእንግዲህ የጎንደር ህዝብ ጦርነት በቃን ማለት ይኖርበታል። ማንም ከፋኝ ብሎ ጎንደር እጠጋለሁ የሚለውን ሁሉ ጎንደር ማስጠጋት ከእንግዲህ አይኖርበተም። ጎንደር በጦርነት ስትደቅ ሌላው ልማቱን በማካሄድ፤ ልጁን በማስተማር በወግ በማዳር እና በመኳል ለትልቅ ሃላፊነት በማብቃት ተጠቃሚ ሆኗል። 

ዛሬ የጎንደር አፈር ልብሶ መቀመጥ እና የልጆቹ ተቀብረው መቀረት ዋናው ምክንያት የትወልዱን ብክነት ራሱ በመፍቀዱ ነው።  የሌላው አካበቢ መልማት ሰው ማውጣት አባባ መሆን ጎንደር በዬዘመኑ በከፈለው መስዋዕትነት የተገኜ ነው። እናመሰግንሃለንም ተብሎ አያውቅም። 

ሌላው ቀርቶ እነዚህን የዘመን ጌጦች ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ የተገኙበት የዞግ ድርጅት ኦህዴድ መሰረቱ አርማጭሆ በለሳ እና ላሊበላ መሆኑ ባለፈው ጊዜ አቶ አባ ዱላ ገማዳ ግለጸውታል። 

ከእንግዲህ ግን በሞኝ ክንድ ዘንዶ መለካትን በቃኝ ማለት ጎንደር ይኖርበታል። የፈለገ በራሱ ጫካ ይሸፍት። ጎንደር ግን ከእንግዲህ  የአማጽያን ዋሻ በመሆን ራሷንም ትውልዷንም አትገድልም። ለዚህ ደግሞ ተግተን እንሰራለን። 

ጎንደር ሰላም እለታዊ ህይወቱ መርህ ማደርግ ይኖርበታል። ስለሆነም የኢትዮ ኤርትራ ሰላማዊ መንገድ ሰፊ ተጠቃሚው ጎንደር ነው። እናም ጎንደር ነገ የእልልታው ቀን ነው። የጎንደር ህዝብ ከጭንቅ የተገላገለበት ቀን ነው የኢትዮ ኤርትራ የስምምነት አውደ ምህረት።

በሌላ በኩል ዛሬ ለውጡን በመደገፍ እረገድ የጎንደር ሰው ለውጡ የእኔ አካል ነው ብሎ ዘብ መቆም ይኖርበታል። ለለውጡ ማገር ባላ እና ወጋግራ መሆን መቻል አለበት - ጎንደር። ለውጡም የእሱ ገናና ተጋድሎ ውጤት ነውና። በተመሳሳይ ሁኔታ ጎጃም ቅኔውም ይህንኑ በተግባር መፈጸም ይኖርበታል።  

በምንም ሁኔታ፤ በምንም መስፈርት ለጎንደር ህዝብ ለአማራ ህዝብ ከዚህ የተሻለ ጊዜ አይመጣለትም።

የጎንደር ህዝብ ሃላፊነቱን ወስዶ እኔም አሳምነው ጽጌ ነኝ ብሎ ጎንደር ለሚኖሩት ወገኖቹ ሁሉ ግንባር ቀደም የሰላማቸው አስከባሪ ወታደር መሆኑን በተግባር ማረጋገጥ ይኖርበታል።

ነገ በሚደረገው አቀባባል ላይ በፍቅር፤ በደስታ፤ ከልብ በመነጬ ሐሴት እና እልልታ እንግዳን ከመቀበል ውጪ ሌላ ተደራቢ ጥያቄ በመቅረብ የእንግዳ አቀባበሉን ማወክ የተገባ አይደለም። እንግዳ እንዴት እንደሚቀበል ለጎንደር ሰው እኔ አልነግረውም። ያውቀዋል፤ ያውቅበታልም።

ሥርጉተ የዛሬ ዓመት ስለ አብይ በምን ያህል ተሟገተች። በጥቂቱ ይህን ይመስል ነበር የዛሬ ዓመት ሙግቱን ስጀምረው። ፖስት የተደረገበትን ሳይሆን ቀኑን የተጻፈበትን ማዬት ይቻላል።


በተረፈ መልካም የአቀባባል ጊዜ።
ክብረቶቼ ቅኔቹ የቻላችሁ ሸር አድ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።