አብይ ኬኛ መቅድም።

 ራስንም ማዬት ከትዝብት ይታደጋል።
ኦህዴድን ከመተቸት በፊት ራስንም 
ማዬት ከትዝብት ይታደጋል።
  ከሥርጉተ ሥላሴ (Sergute©Sselassie)
 18.12.2017 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
„መለዬት የሚወድድ ምኞቱን ይከተላል፣ 
መልካሙን ጥበብ ሁሉ ይቃወማል።“ 
(መጸሐፍ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፰  ቁጥር ፩)

ይድረስ ለ„ማማ“ አዘጋጅ ለጋዜጠኛ ማስራሻ አለሙ። 
ከዚህ ከጭምቷ ሲዊዝ እንሆ „ከለማውያን“ ወገን እጅ ነሳን



  • ·         እፍታ።


ዛሬ የኢሳቱ ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ በአቶ ለማ መገርሳና በድርጅታቸው በኦህዴድ ጉዳይ ባነሳቸው ጥቂት ጉዳዮች ዙሪያ ልሞግተው አሰብኩኝ። በዚህ መልክ በአንድ ወቅትም „በድምፃቻን ይሰማ“ ጉዳይ እንዲሁ ያልተመቸኝ የአምክንዮ ጭብጥ ስለነበር ባልደረባውን የኢሳቱን  ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ ሞግቼ ነበር። ያን ጊዜ ባለ ማንፌስቶዎች መንገድሽ ትክክል አይደለም በማለት ማሳሰቢያ በጓሮ በር መጥተው ሰጥተውኝ ነበር። 

በአደባባይ ደግሞ ትክሻ ለትክሻ ሲተቃቀፉ አይ ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ „የድምጻችን ይሰማ“ ደጋፊዎችም ሁሉንም ቅንነትን በመለገስ ለዬስበሰባውም የሚከፍሉት መስዋዕትነት አንቱ ነበር፤ ከእኔ ቀደም ብሎም ዘለግ ባለ ደቂቃ „በድምጻችን ይሰማ“ ዙሪያ የሊሂቃኑን የግንቦት 7 ሊቀመንበር ንግግር አዳምጫለሁ። የንግግሩ የጭብጥ ማዕከልም ነበር። ያን ጊዜ ዝም ብዬ እኔ አስተውል ነበር። 

ከዕለታት አንድ ቀን የኢሳት ጋዜጠኛ አንድ ጹሑፍ አወጣ „በድምጻችን ይሰማ“ ጉዳይ። አንዲት ኢትዮጵዊት ሙስሊም ለንድን ኖሪ የሆነች አንድ የአሸባሪ ቡድን አባል ስላገባች ብቻ በ„ድምጻችን ይሰማን“ ዙሪያ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል የሚል ዕድምታ ነበረው። በውነቱ ጹሑፉ ቅንነት የነበረው ግልጽ ነበር። ሌላ ኮተት አልነበረበትም። ነገር ግን አንድ የእምነቱ አባል ስለሚያደርገው ማናቸውም ጥፋት እምነቱ በጥቅል ሥሙ ሊነሳ ስለማይገባ፤ በተጨማሪም እስልምና ሃይማኖት በኢትዮጵያ ቀለሙም ተፈጥሮውም የተለዬ ስለሆነም ያን ጊዜ እኔ „ድምጻችን ይሰማን“ በዚህ ልንጠራጠረው አይገባም በሚል ተከታታይ ጹሑፎችን አወጣሁ። 


ለነብዩ መሃመድም ኢትዮጵያ የቃልኪዳን ሐገራቸው ናት። ይህን ቃልኪዳን ይጥሱታል አልልም እነ „ድምጻችን ይሰማ“ አንዲያውም አንዱ ጹሑፌ  „እኔም ድምጻችን ይሰማ ነኝ“ ብዬ ሁሉ ነበር ያወጣሁት። እግዚአብሄር ይመስገን አላሰፈሩኝም፤ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በባለሙያዎች ንቅናቄው ተፈትሾ ከዚህ ነጻ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ የእትብት መንደሬም ጎንደርዬም „ድምጻችን ይሰማ“ ድምፄ ነው ብሎ በደሙ ተዶሞ አተመበት። አስተውሉ የአርባራቱ መንደር ነው እንዲህ ያለው።

ወንድሜ ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ አሁን የአንተን ሃሳብ በህሊናዬ እያተወያዬሁበት እና እዬጻፍኩት እያለ እረፍት ላድርግ ብዬ ሳተናው ድህረ ገጽ ስገባ ጋዜጠኛ መሳይም መኮነን አንድ ጹሑፍ አውጥቶ አነበብኩኝ። ለነገሩ ሲጀርም፤ አሁን ባለው ሁኔታ የጋዜጠኛ መሳይ አቋም ወጥነት እና ተሰመሳሳይነት አለው። 

በቅንነት ነገሮችን ማየት ብቻም ሳይሆን ወቅቱን የማድመጥ አቅሙ የሚሠራበትንም ድርጅት የሚያስከብር ይመሰልኛል። ምክንያቱ አንድ ሰው ለዚህ ሃላፊነት ይበቃል ተብሎ ምስክርነት ሲሰጠው ከግል ኑሮው ጀምሮ ያን የተሰጠውን ምስክርነት ሳንክ እንዳይገጥመው፤ ምስክር የሰጡት ሰዎችም እንዳይፍሩበት ራሱን መግራት አለበት። በእሱ ምክንያትም ድርጅቱ ሆነ ምስክርነት የሰጡት ሰዎች አንዳያወቀሱ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባዋል። 

ይህ እኔ በግል ህይወቴ የምመራበትም መርኼ ነው። እኔ ለትኛውም ሃላፊነት ቦታ ስመደብ፤ ለትምህርት ስላክ፤ ለወርክሾፕ ስላክ እኔን ብቁ ናት፤ ትምጣናለች ብለው የመሰከሩልኝም ሃላፊዎቼን አንድም ቀን በእኔ ዙሪያ አስወቅሻቸው አላውቅም። አንድ ሰው ለአንድ ቦታ ብቁ ነው ሲባል እጅግ ጠንቃቃ መሆን አለበት። 


ስሜቱን መቅጣት አለበት። አንድ ሰው ስለግሉ በሚነገራቸው፤ በሚጽፋቸው ነገሮች ሁሉ የወከለውን ድርጅት መንፈስም የውክልና ማህበርተኛ ስለመሆኑ ላፍታም ቸል ሊለው አይገባም። ምክንያቱም ድምጹ ከሁለት አቅጣጫ ሊመዘን ስለሚችል። ሚዛኑ ከሚሠራው የድርጀት አቋም እና ከግሉ ከነፍሱ ካለው አቋም ጋር አያይዞ ነው ሰው የሚያዳምጠው። 

ስለዚህ አንድ ሰው ከአንድ ድርጅት ጋር ሲሰራ ወይንም አንድ ድርጅት አንድን ሰው ለማሰራት ሲፈቅድ ከስሜታዊነት ደዌ መዳን አለበት። የሰው መንፈስ ስስ ነው። አብሶ ብዙሃን በደገፈው ሃሳብ ላይ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ዴሞክራሲ ማለት እኮ ይሄ ነው። ብዙሃን የፈቀደውን፤ ብዙሃን የወደደውን እንደራስ አድርጎ መቀበል።
  • ·         ይጀመር።


„ማማ“ ከሚለው ትርጉም ልነሳ እፈልጋለሁ።
„ማማ“ በአውንታዊ ትርጉሙ፤
·         ጋህዱ ዓለም ትርጉሙ „ከፍብሎ፣ ከሌላው ልቆ፣ ከሌላው ጎልቶ የሚታይ ቦታ - ሥፍራ ሲሆን የትርጓሜው አግባብ እንደ አረፍተ ነገሩ በአንራዊነት ወይንም በፍጹማዊነት ሊሆን ይችላል።

·         „ማማ“ በነፍሳዊ ትርጉሙ „እናት“ ታላቁን የመኖር ፍቺ ቁልፍ የያዘ ነው። ርህርህናን፤ ደግነትን፤ መምህርነትን፤ አጽናኝትን፤ ቻይነትን ሰውን ያህል ታላቅ ነገር በጽንስ የመሸከምን ተፈጥሮ፤ ከተወለደ በኋዋላም ሃላፊነቱን ፈቅዶ መውስድ ብቻም ሳይሆን ተፈጻሚነቱ ከራስ በበለጠ እንክብካቤ ስለመሆኑ የሚገልጽ የፍቅር ተፍጥሮ ህግ እና  መርህ ምልክት ወይንም ዓርማ ነው። የነፍስ አናባቢ የቁልምጫ ሥም ነው።  በመንፈሳዊ ትርጉሙ „መንበርረ - ቅድስናን" ያመልክታል።

„ማማ“ በአሉታዊ ትርጉሙ የሚሟሟ፤ በነበረው በራሱ ውስጥ የማይቀጥል። እራሱን ቀይሮ ወይንም ለውጦ በሌላ ቅርጽና ይዘት ጣዕምና ሁነት የሚተካ። እንደ ተፈጥሮው ሆኖ ለመቀጠል ያልታደለ ወይንም የተረገመ፤ ግን ከሌሎች ንጥረ ነገሮች ጋር በመቀላቀል ሳይሆን በመዋህድ አዲስ ንጥረ ነገር የሚፈጥር ማለት ነው። በጣምም በይዘትም አዲስ ሆኖ ነው የሚፈጠረው።

ይህ ሥያሜ  ለእምዬ ኢትዮጵያ ከሆነ ለተደራሹ ትርጉሙ በሁሉም አቅጣጫ እንዲታይ የሚያደርግ የአቋም ጽናት የጎደለው፤ ለጥቃት የተጋለጠ ስያሜ ነው። ኢትዮጵያን ለመግለጽ መዋስ፤ ብድር ፍለጋ መኳተን፤ ወይንም አሻሚ ቃል ፈልጎ ትርጉሟዊ ተፈጥሯዋን መፈታተን የተገባ አይደለም። 

„ኢትዮጵያ“ የተወላጠ ሥም አያስፈልገውም። እራሱን የቻለ የነገር ሥም፤ መጠሪያ ነው። ኢትዮጵያ የሚሊዮኖች ደም እና አጥንት፤ ረቂቅ መዋለ መንፈሶች ተቃቅፈውና ተደጋግፈው ቃላት ሊተረጉመው በማይችለው፤ ልዩ የመክሊት አቅም ባላቸው ጥልቅ የፍልስፍና ተፈጥሯዊ አመክንዮች የበለጸገ፤ ማህበረ ረቂቅ ንጥረ ነገሮችን ያጣጠመ፤ ያዋሃደ፤ ያመሳጠረ፤ ያስተሳሰረ ዓለም የሚያውቀው ሥም ማለት ነው። የመቻቻል ባንዴራ። 

ሥሙ በራሱ ሃይለቃሉ ተፈሪ ነው። ኢትዮጵያ የሚለው ሥያሜ የክርስትናውን ዓለም እና የመንፈሳዊ ህይወት በሚመራው ቅዱስ ወንጌል ተደጋግማ ስትወሳ ዛሬ ሰለጠኑ፤ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት አላቸው የሚባሉት እንኳን በዛ ቅዱስ መጸሐፍ ውስጥ አንድም ቦታ ላይ የሉም። ሃያላን ሀገራት አንዲት ቦታ ስማቸው አልተጠራም። አሜሪካ ወይንም ጀርመን ወይንም ራሺያ ወይንም ፈርንሳይ፤ ወይንም ጣሊያን የሚል የነገር ሥም አንድም ቦታ ላይ የለም በቅዱሱ መጸሐፍ ውስጥ። ሌላው ቀርቶ ጸሐይ አይጠልቅባትም የተባላችው ታላቋ ብርታንያ ሳይቀር የለችም።

ስለሆነም ነው ዛሬ ለዚህ ትውልድና ለቀጣዩም መጸሐፍ ቅዱስ ላይ ኢትዮጵያ የሚለውን ሥያሜ „ኩሽ“ በሚለው ለመቀዬር ሰፊ ዘመቻ የተጀመረው። ምንስ አሰፈራ „ኢትዮጵያ“ የሚለውን ሥያሜ ለመጠቀም? ከትርጓሜው ስንነሳ ኦህዲድ በኢትዮጵያዊነት ሄርተኝነት ሥም ንግድ ጀመሯል ነው የሚለን ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ። አቅም የለውም የዝግጅት ክፍሉ ይህንን ሃሳብ ለማመጣጠን። 

ስለምን? ራሱን የማዬት አቅሙ ስስ ስለመሆኑአረፍተ ነገሮች መግቢያ እንኳን እንደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ „አገር“ ነው የሚለን። ስለሆነም የዝግጅት ክፍሉ በነገረ ኢትዮጵያ ከሥያሜው ጀምሮ ድፍረት ያንሰዋል - ልፍስፍስ ነው። 

መጀመሪያ „እማማ ኢትዮጵያ“ ወይንም „ኢትዮጵያ“ ብሎ ሥሙን ይሰይምና በዚህ አጀንዳ ዙሪያ ሳንክ፤ ችግር የሚላቸውን ነገሮች መፈተሽ ይችላል። ዝም ማለት እኮ መቀበል ወይንም መሰማማት አይደም። አቅም አንሶንም አይደለም። ፍርሃትም አይደለም። ቀለብ ስለማይቆረጥልኝ ሃሳቤን ለመግለጽ የሚያሥረኝ የውል ቋጠሮ የለም። የሃሳብ ድህነትም የለብኝም።

ምን እንዳለኝ፤ ምን አንደምንችል፤ ምን ደግሞ እንደሚያንሰኝ ጠንቅቄን አውቃለሁ። የተመክሮም ክሳት የለብኝም - የጓድ ገ/መድህን በርጋ ልጅ ነኝ። እግዚአብሄር በፈቀደው ሁሉ ዩንቨርስቲ ብገባም ከማገኘው እውቀት በላይ ውስጥን ለመፈተሽ የሚያስችል ዕድሎችን በአግባቡ በመጠቀም ህሊናን የማዳበር፤ የተመክሮና የክህሎት ማሳዎችን በመስፋት እረገድ ባያንጠራራም፤ በይወጣጥርም ግን ልኬን አውቄ በልክ እንኖር ዘንድ፤ መሬትን በርጋታ እና በስክነት እራመድባት ዘንድ ስለፈቀድኩ ብቻ ነው ዝም የምለው። ሌሎችም ወገኖቼ እንዲሁ። አያዬን እዬሰማን ምርጫችን ዝምታ ሆነ። 

ዝም የምንለውም ለማንም ለምንም ተብሎ ሳይሆን፤ ለአፍቅሮተ ማልያ ወይንም ለንድፈ ሃሳባዊ ፍልስፍና ንጥረት ተብሎ ሳይሆን የነፃነት ራህብ ያለበት ሰው የነፃነትን አቅምን ሞራል መጠበቅ ስለሚገባ ነው። ለዚህም ነው ቅን ነገሮች ሲታዩ ብቻ ታይተው እንዳይከስሙ፤ አቅም እንሁናቸው በማለት „ጉዲት“ እሰከ መባል የደረስኩት። ካለ አንዳች አይዞሽ ባይም በግራ በቀኝ የተቀጠቀጥኩት። እርግጥ ነው የዘሀባሻ እና የሳተናው አዘጋጆች መንፈስ ለመንፈሴ ይለፍ በመስጠት ከጎኔ ነበሩ፤ ማመስገን ብቻ ሳይሆን ፍቅሬም የተለዬ ነው። 

አዲሱን ሥምን፤ አሁን ደግሞ በእግዚአብሄር ይስጥልኝ በልዩ ክብር ነው የማስተናግደው የጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙን „ለማውያን“ ተቀብየዋለሁ አንደ ማለት። እንኳንም „ዘማውያን አልተባልን“ ብትለንም የጸጥታ ህይወታችን፤ ቁጥቡን ተፈጥሯችነን ፈጣሪ ስለሚያውቀው አይደንቅም። ለአዲሱ አቅም ፈሪ፤ አቅም በታኝ፤ አቅም ተጸያፊ፤ ቅናተኛ የፍልስፍና ቃል ስላገኘህለት ግን እንኳን ደስ አለህ - ላንተው።  „ለማውያን“ ጥሩ ነው „አናስደንግጣቸውን“ ዘመን አሻጋሪ ፍልስፍና ጨምርኽ ነው ልብሱን አስወልቀህ እንደ አረመኔው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ባልተወለደ አንጀትህ በጅራፍ የወቃኸው።

አዬህ ኢትዮጵያዊንት ሸቀጥ አይደለምኢትዮጵያዊነት በጅምላና በችርቻሮ ንግድ የሚተዳደር ወይንም፤ በአስመጪና ላኪ ኩባንያ የገቢና የወጪ፤ የትርፍና የኪሳራ የገቢ ሰንጠረዥ የሚዘጋጅለት ማንነት አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የነፍስ መንገድ ነው። ኢትዮጵያነት የመንፈስ አንጡራ ንጥር ጥሪት ነው። ኢትዮጵያዊነት ሥያሜው ተጠዋሪ አይደለም። በራሱ ሙሉ መንፈስ ውስጥ የነበረ፤ ያለ የሚኖር ይባቤ ነው። 

በሌላ በኩል ኦህዴድ ድርጅቱ በነፍሱ „ኢትዮጵያ የምትባል ሐገር የለችም፤ ይህ ማንነት አልተፈጠረም፤ ኢትዮጵያዊነት አልነበረም፤ ኢትዮጵያ ገና ያልተሰራች ሀገር ናት፤ በምትፈርሰው ኢትዮጵያ ላይ ሀገረ ኦሮሞን እንመሰራታለን“ ብሎ አይደለም የተደራጀው። በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ነው የተደራጀው። 

ሌላው ኢትዮጵያዊነትን በሚመለከት የሰዎች የእጅ ሥራ አይደለም። ወያኔ ሃርነት ትግራይ አቅሙ አይፈቅድለትም ይህን የኦህዴድ ሊሂቃኑ እንዲናገሩለት የማድረግ። 

አዬህ ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ የመቀበል ወይንም አንጥሮ የመመለስ ጉዳይ ነው። ቅናት ካልሆነ በስተቀር በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ለሚታታር አንድ ጋዜጠኛ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ሲባል የሚያላግጥበት፤ የሚያባጭልበት፤ ጢባ ጢቦሽ የሚጫወትበት፤ ከሌላ የፖለቲካ ሸክምና ደበሎ ጋራ የሚያነካካበት፤ ንጹህ መንፈሱን የሚበርዝበት፤ ምንም ምክንያት ሊኖረው አይገባም። 


ጋዜጠኝነቱ በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ የዕውነት ከሆነ። ኢትዮጵያውነቴን ከምንም ነገር በላይ ሆነብኝ፤ እጅግም ወደድኩት፤ ሐሤትም አገኘሁበት ማለት ከቶ ያስወቅሳልን? በአንዳንድ አጋጣሚ ዛሬ ባዬሁት ነገር ኢትዮጵያዊነቴን ኮራሁበት፤ አኮራችሁኝ እንላለን። አሁን የስሜን አሜሪካን የእግር ኳስ ፌስቲባል እኔ ስመለከት እንደዛ እላለሁ። ብሄራዊ ሰንድቅ ዓላማዬ ድምቅ ብሎ ሲወጣ፤ ወይንም ከተለመደው ውጪ ኢትዮጵውያን ወገኖቼም ድንቅ ነገሮች ስናይ እንኳንም ኢትዮጵያዊ ሆንኩ እንላለን። ይህ ማለት ከዛ በፊት ኢትዮጵያዊ አልነበርኩም ማለት ነውን?  


  • ·         መነሻ።

በዚህ የመነሻ ሃሳብ የአዘጋጁ መንፈስ ብቻ ይፈተሻል። ምክንያቱም ኢሳት ላይ ሦስት ምልከታዎች እንደ ነበሩ ተመልክቻለሁ። አዳምጫለሁ። እነኛ አቅምን ለማዳበር ሃሳብን በሃሳብ በማፋተግ በሙገታ አሸናፊ ሆኖ የወጣውን የሃሳብ አቅም ያስተናገዱ ብቻ ሳይሆን የተለዩ ሃሳቦችንም ነጻነት ሳይጫኑ፤ ነፃነታቸውን ያልተጋፉ ውይይቶች ነበሩ። ለምሳሌ „ በአባ ዱለ ገመዳ እና በአቶ በረከት ስምዖን የሥራ መልቀቂያ፤ በአቶ ለማ ካቢኔ እና አዲስ ጅምር ቀናነት ላይ ሰፊ ጊዜ ሰጥተው የእኛ የራሳችን እስከሚስለን ድረስ ቀልባችን ሰጥተን ነበር በአክብሮት ያዳመጥናቸው። የሚደግፉ እና የማይደግፉ ሃሳቦች እኩል ተስተናግደው ለአድማጮች ሚዛናዊነትን አስተምረው ነበር። አሁን ያነን ጥረት፤ ያነን ድካም በመናድ የእንቧይ ካብ አደረገው ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ። 

ጋዜጠኛው እኔ የምላችሁን ብቻ አድምጡ፤ እኔ በምቀድላችሁ መስምር ብቻ ተጓዙ። በእኔ ውቅያኖስ ብቻ ቅዘፉ ነው የሚለን። አሉታዊ ነገሮችን  ብቻ ልቅም አድርጎ አውጥቶ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውን“ ተዋጉ ይለናል። እግዚኦ!

ይህ አካሄድ የተጠለለበትን ድርጅት እራሱ በፍጹም ሁኔታ ያስገምታል። ጠቢቡን ቴወድሮስ ካሳሁን ኢሳት የ2017 የዓመቱ ምርጥ ሰው ብሎ ሸልሟል። ምክንያቱም ዓለም ዐቀፍ ተጽእኖ ፈጣሪነቱ የመንፈስ አቅሙን ተመልክቶ ወይንም ከኢትዮጵያዊነት ጋር ፍቅር ይዞት። ይህ ከሆነ በሁለቱም መንገድ በየትኛውም መንገድ ለፍላጎታችን መፍትሄ አቅም ሲገኝ፤ ወይንም ከኦሮሞ ብሄርተኝነት የወጣ መንፈስ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ማለት ምኑ ነው ጦር ያሰመዘዘበት? 

ባለፈው ዓመት እኮ የነፃነት አርበኝነትን በአትሌት ሊሊሳ ፈይሳ ታይቷል። ከዛ በፊትም አትሌቱ ሩጧል። አርበኛ አትሌት ሊሊሳ ፈይሳ ግን የኢሳትም ሆነ የዓለምም ልዩና ድንቅ አጀንዳም አልነበረም። አርበኛ ሊሊሳ ፈይሳ በዚህ አርበኝነት ይመጣል ተብሎ የገመተ አልነበረም። ሲሆን ግን ድንቅ ነበር። አሁን ጋዜጠኛ ማስረሻ ዓለሙ የሚነግረን አቶ ለማ መገርሳ ሲመረጡ "እንዲህ ይሆናሉ ተብሎ ያሰበም አልነበረም" ነው የሚለን። 


ጊዜ ታሪክ ይሰራል። አንተ ያልገባህ ይህ ነው። ጊዜ ዓይነ - ገብ እንዲሆን ሲፈቅድላቸው ደግሞ ያዬነው የሰማነው፤ እራሳቸውን አንጠራርተው፤ ከእኔ ወዲያ ላሳር ብለው ሳይሆን ስብር ብለው ውስጣችን እንዲያዳምጣቸው ያደረገውያሳዩት ፍጹም የሆነ ሥነ - ምግባር፤ ትህትናዊ ጉዞ ነው። ዝቅ ነው ያሉት። መመስገኑም ይቅርብኝ ነው ያሉት። አለወረፉንም ለእኛ ስደት እያገላጥ ለሚገርፍን ምንዱባን እዚህ ያለውን ወገናችን እያገለለን፤ እዬገፋን እሳቸው ግን አክብሮት ነበር የላኩልን። ይህ ለእኛ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው። አብሶ ባለቤት ለሌለን ማንፌስቶ ላላቀፈን፤ ማንፌስቶ ደህነታችን ለማያስጨንቀው ዕንባማ ስደተኞች።

የሆነ ሆኖ አርበኛ አትሌት ፈይሳ ሊሊሳ ከአርበኝነት ገድሉ በኋዋላ ደግሞ ያዬነው አይተናል። በአውሮፓው ህብረት እንዲጋበዝ ተደርጓል። ተጽዕኖ ፈጣሪነት አቅም ነው። እሱም የኦሮሞ ልጅ ነው። የአቶ ለማ መገርሳ ኦህዴድም የኦሮሞ ድርጅት ነው። ምን ልዩነት አለው። 

የነጻነት አርበኛው አርበኛ አትሌት ሊሊሳ ፈይሳ እኮ የቁቤ ትውልድ ነው። አዲሱ የኦህዴድ ካቢኔም የቁቤ ትውልድ ናቸው። ልዩነቱ አርበኛ አትሌት ሊሊሳ ፈይሳ ለሥልጣን ተቀናቃኝ አይደለም። የአቶ ለማው ኦህዴድ ካቢኔ ግን የተደራጀው ለፖለቲካ ሥልጣን ነው። ስለዚህ ጎልቶ ከወጣ የፖለቲካ ሥልጣን ለሚሹ ሁሉ ተፎካካሪ ሆኖ ይውጣል። የአቶ ለማ ኦህዴድ ከማዳጋስካር የመጣ አይደለም። 

ኢትዮጵያን በመጉዳትም ይሁን በመጥቀም ስንት ጉድፍ ተችሎ ነው ይሁን እዬተባለ በችሎት የተቻለው። የመከራው ጊዜው አንዲህ የተንዛዛ እና የገለማ የሆነው መሰረቱ እና ምንጩ ጊዜ መስታውት አለው። 


የነፃነት ትግሉን በፖለቲካ ብስለታዊ አመራር የብቃት ምጡነት ማነስ ግድፈት ምክንያት ነው ነፃነታችን እንዲህ ይህን ያህል የህልም እንጀራ የሆነው። ይህንንም አቅም ያላቸውን አምክንዮ አቅርቦ መሞገት ይቻላል። ወር አይሞላም አንድ አቋም በሌላ አቋም ሲተካካ። ዝም እምንለው አሁንም ለነፃነት ትግሉ ሞራል ሲባል ብቻ ነው። 

እንሞግተው ቢባል በቅንነት ብቻ ወድቆ እንዳይነሳ አድርጎ ውልቅልቁን ማውጣት በተቻለ። ለሙግት የሰው ወይንም የድርጅት ወይንም የማንፌስቶ ትክሻ ሳይሆን አቅም ያለው ጉልበታም የአምክንዮ ድልዳል ብቻ በቂው ነው።
  • ·         የጋዜጠኛ ማስረሻ ዓለሙ ሆድ ዕቃ በጥቂቱ።


https://www.youtube.com/watch?v=1qx2gJSTkks&t=1484s 

ESAT Mama Dec 13 , 2017“

"„ጤና ይስጥልኝ „የማማ“ ተከታዮች ህወሃት ኢህዲግ ችግር አለብኝ ብሎ ችግሬ እንዲህ እና እንዲያ ነው ብሎ በአደባባይ የማያፍር ድርጅት ነው። ነገር ግን ችግሩን ለመፍታት የሚሄድበት መንገድ ዓይኔን ግንባር ያደርገው ዓይነት መሆኑን 100 ሚሊዮን ዜጎች በሞት ጥላ ሥር መካከል እንዲጓዙ እያደረገ ይገኛል። የህወሃት ኢህድግ መንገድ በቀላሉ ልንወጣው ከማንችለው ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥም ከቶናል፤ የብሄር ዘውገ ፖለቲካዊ ሁነት ሐገሪቱን እንደ ቆዳ ወጥሯታል። 

ከአቶ መለስ ሞት በኋዋላ የጠቅላይ ሚ/ር ቦታውን የተረከቡት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የተሃድሶ ስብከቱን በኢትዮጵያዊ ውስጥ ለማስቀመጥ የሚያስችሉ አቅምና ብቃት በማጣታቸው „በአገሪቱ“ ብዙ አይነት አስፈሪ ሳቶች ሲንቀለቀሉ ዓይተናል፤ ከተነሱት እሳቶች አንዱ በኢትዮጵያ ሱማሌ እና  „በኢትዮጵያ ኦሮሞ“ መካከል የተነሳው  ግጭት ነው። ይሄኛው እሳት ለመጀመሪያ ጊዜ አንደ በረከት ስሞዖን እና እንደ አባ ዱላ ገመዳ የመሳሰሉ ባልስልጣናትን የሥራ መልቀቂያ እንዲያስገቡ ጭምር አስገድዷቸዋልም አይተናል። 


የፓርቲው ጎምቱ ሰዎች የሥራ መልቀቂያ ማስገባት በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የሚያሳዬን የፓርቲው ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መንኮታኮቱን ነው። ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ማለት ከላይ ወደ ታች የሚወርደውን „እዬቀዱ በማንቆርቆሪያ ማንቆርቆር“ ማለት ነው። 


አቶ መለስ ዜናዊ የተከተሉት „ከላይ የማንቆርቆር“ አባዜ በአቶ ሃይለማርያም የሥልጣን ዘመን ወደ መቃብር እዬተጓዘ ነው፤ ይህን በግልጽ ማዬት የቻልነው። በኢትዮጵያ ሱማሌ እና „በኢትዮጵያ ኦሮሞ“ መካከል በተነሳው ግጭት ድንጋጤ ውስጥ የገባው ኦህዲድ መዳኛችን አንድነት ነው የሚል „መዝሙር የሚያዜሙ“ „ለማዋያንን“ ወልዶ በአደባባይ ሲመጣ ስለተመለክትን ነው። በ2010 ዓ.ም የኢህአድግ ፖለቲካ „ከዘመነ መለሳውያን“ ወደ ዘመነ „ለማውያን“ ፊቱን ማዞሩንም በትዝብት እዬተመለከትን እንገኛለን። እንኳን ወደ „ለማውያን ዐለም“ በደህና መጣችሁ። ዛሬ ስለ ለማ መግርሳውያን እና ስለ „ለማውያን“ ጥቂት እናዋጋለን።“ 

ማን ያፈረውን ኢህአዴግ ይፈር ይላሉ ክቡር ጋዜጠኛው? ስንቱ ግድፈት ተቆጥሮስ ይዘለቃል? ለመሆኑ ለግድፈቱ ብዛት መጋዘን ይችለዋልን፤

የሆነ ሆኖ „እንኳን ወደ ለማውያን በደህና መጣችሁ“ ብለህናል አንኳን በደህና ቆዬህን እንልሃለን እኛም። እንኳንም  አቅምን እንደጦር የምትፈራ ጋዜጠኛ ስለመሆንህ ውስጥህን እንኳን አስጎበኘህን እንላለን። አንተ ደግሞ እነማን ትብል እንደሆነ ዘለግ አድርገኽ ብትገልጽልን እራስህን ገለጥለጥ አድርገህ ብትነግረን መልካም ነበር። ሌላውን እንደምታብጠለጥለው ሁሉ። እኛም ተራችን ደርሶን የምንለውን ባልን በነበረ።

ኢትዮጵያ ሱማሌ የሚባልበት ምክንያት አለው። ሱማሌ የሚባል ሀገር ስላለ። „ኢትዮጵያ ኦሮሞ“ ማለት ግን ለመሆኑ ምን ማለት እንደሆነ ገብቶሃል ወይንስ ለአንድ ሰፊ ማህበረሰብ ይህን አዲስ ሥም ስታስታጥቀው ፖለቲካዊ ግንዛቤህ ወገቤን ብሎ ይሆን? ምን ማለት ነው ይህ አገለላለጽ? „ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ“ ይገርማል። ይህ በራሱ ከራስ ጠጉርህ እስከ እግር ጥፍርህ ያለውን ሰብዕና ይግልጠዋል። ይግለጥ መዝገቡ ይነበብ ነው የሆንከው።

ለመሆኑ የመፍትሄ አፍላቂነት ችግር የኢህዴግ ብቻ ነውን? በዬትኛው የመፍትሄ መንገድ ተሂዶ ነው የነፃነት ትግሉ መፍትሄውን ያስገኘው? መፍትሄ አፍላቂነት ክህሎቱ ከነበረ ስለምን ቅንጅት ተበተነ? በዬትኛው ሀገር ፖለቲካስ ነው ህዝብ መድፍ እዬረገጠ ምራኝ ብሎ ድምጽ ከሰጠ በኋዋላ ልግባ // አልግባ ተብሎ ተጠይቆ የሚታወቀው? ይሄ ነው ብልህነት? ነፍሰጡር ሴት ከምጧ በኋዋላ ልጄ መወለድ የለበትም ይመለስ እንደገና ያረጋ ደም ይሁን፤ ይጸነስ ሁለተኛ ዙር እርግዝና እና ምጥ እሻለሁ ማለት እኮ ነው። የጊዜንም ቀምር ይጋፋል። ሁለት ልጅ በምትወልድበት አቅም ለአንድ ልጅ ድርብ ጊዜ መስጠት ስቃዩ እንደ ተጠበቀ ሆኖ። ልጁም  እግሩ መሄድ ከመጀመር አራስ እንዲሆን። 

የፖለቲካ የስልጣን እርክክብ መሰረታዊ ንድፍን ተፈጥሮ የገለበጠ ከመርህ ውጪ የሆነ እርምጃ ነበር። ከሥረ - መሠረቱ ተነስተህ አጥነተኸዋልን ይሄን ድክመት? ዛሬ አንዲት ቀንጣ ወንበር ማግኘት የሰማይ ደጅ ሆነ። ይህም ብቻ ሳይሆን ከዛ በኋዋላ የፈሰሰው መከራ በመንፈስም፤ በሃብትም፤ በሰውም ምንዛሬ ሊወጣለት ከቶውንም አይችልም።


መንስኤው ምን ነበረ? የውድቀቱ ግብዕትስ? ከዛ በኋዋላ በነበረው ጉዞ የተገኙ ትርፎች ለነፃነት ትግሉ ስምረት ጉልበት እና አቅም ያለው የሚጨበጥ፤ የሚዳሰስ ምን አለን በእጃችን? ይሄ አውሎ ንፋስ በተነሳ ቁጥር የሚወዛወዘውን የዛፍ ተክል ብትለኝ  እኔ እሞግትሃለሁ። 

ያን የመሰለ ከሥር የተደራጀ እና በተሟላ ኢትዮጵያዊነት ስሜት የተገነባ „የአርበኞች ዘብ“ ተጋድሎ ለወያኔ ሃርነት በቀል የሳት እራት የሆነው የፖለቲካ ብስለት፤ የመምራት ጥበብና ልቅና፤ የአቅምና ጥራት ስለነበር ነውን? 


ከዚህስ ሌላ አናቱ የገማው ጭንቅላት ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ሲያልፉ በነበረው ክፍተት ምን ተረፈ? የነፃነት ትግሉ በአመራር ብስለት እና ልቅና ብልጫ ስለተጓዘ የትኛው እርከን ላይ ተደረሰ? ትናንት „ የአማራ ተጋድሎ ወላዱ የጎንደር አብዮት“ የወያኔ ሃርነትን ሲያንቀጠቅጥ ያን የህዝብ መንፈስ አክብሮ በመነሳት በየትኛው የፖለቲካ አቅም እና ብልህነት ተመርቶ ነው ለድል መዳረሻ የሆነው?

እንዲያውም የአማራ ልጅ በግራና በቀኝ በነበረው የፕሮፖጋንዳ ሽኩቻ እዬታደነ በበቀል መዋራረጃ ነው የቀለጠበት? ሁልጊዜ ክሽፈት?የውጭ ሃይሎች አያስፈልጉንም በራሳችን እንወጣዋለን“ ተደጋግሞ የሚደመጥ ነው? ይህ ከሆነ የአሁኑ የወ/ሮ አና ጉምዝ ተማህጽኖ ስለምን ያስፈልጋል? 

አቅም በእጅ የሚተማመኑበት ከኖራቸው ሊሂቃኑ? ስለዚህስ እምትለው ይኖርሃልን? አዬህ አሁን ባለፈው ሰሞን „የማር እሰከ ጧፍ መታገድ“ ያሳዘናቸው አንድ በሃሳባቸው የበለጸጉ አባት ባህርዳር ያለውን በጉልበታም አመክንዮ የአማራ ሚዲያ ሞገቱት። አሁን ሰሞኑን አንድ ፕሮግራም በዚህ ዙሪያ ሰርተዋል። 

ባለፈው ዓመት በአማራ ተጋድሎ ዕወቅና መነፈግ ብዕራችን ቧንቡራ አስኪያወጣ ድረስ የድርሻውን ተወጥቷል፤ ግን ሆነን፤ አዳመጣችሁን? ለዚህ እኮ ነው የዘንድሮው የጎንደር የመስቀል በዓል „እንክባበርን“ ይዞ ከች ያለው። 


ቢያንስ ህዝብ ከወደደው መንፈስ ጋር እዬሄዱ መላተሙ መንፈስን ከመናድ ውጪ አትራፊ መንገድ አይደለም። ህዝብ የሚወደው ፈጣሪ የወደደውን ነው። ከዚህ ሌላ ማንፌስቶ አይደለም ቅብዕ ያለው የሰው ልጅ ሲፈጠር ነው ቅብዕ የሚሰጠው። የተቀባ ካለ ይጠብቀዋል። 

አሁን ሄሮድስ መለሰ ዜናዊ ሞተው ቦታቸውን አቶ ሀይለማርያም ደስአለኝ ይይዛሉ ተብሎ ታስቦ ነበርን? እሳቸውም በህይወታቸው እያሉ አያስቡትም ነበር። የሳቸው ጠ/ሚርን ቦታ በውርስ ለባለቤታቸው ለወ/ሮ ሄሮዳዳይ አዜብ መስፍን ነበር ዕሳቤው። እሳቸው ሲዝሉ ደግሞ ከልጆቻቸው አንዳቸውን ነበር ህልማቸው። „መተካካት“ ፍልስፍናው ይሄ ነበር። ነገር ግን ቅብዕው ለበጎም ይሁን አይሁን ለተመደበለት ሆኗል። ነገም እንዲሁ ነው። 


መንግሥት ሥልጣን እና ክህነተ ሥልጣን ቅብዕው ምድራዊ አይደለም። አዬህ እስከዛሬ ድረስ የሄድንበት መንገድ አላዋጣም፤ አላተረፈም። ደግሞ አዲሱ መንገድ እንደ ድሮው ሁሉ እንዲታጨድ ተነሱ እያልክ ነው። ለዚህ ሞኝ የለም። 

አቶ ሂደት እውነቱን በጥብጦ ግቶናልእድሎቻችነን ብክነት እንዳይገጥማቸው አማራጮችን ሁሉ መጠቀም ሰከን ያለ ጉዞ ይጠይቃል። የገበርዲን እና የከረባት ምርጫ አይደለም ጉዳዩ የተስፋ ኩራዝ እንጂ። 
  • ·         ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት።


ስለ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ያነሳህው የትኛው ፓርቲ ነው ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ልዋህድ ነው፤ ልቀላቀል ነው፤ እከሌ ከሚባል ድርጅት ጋር አብሬ ለመሥራት  አስቢያለሁ ምክሩበት ብሎ አባላቱን ጠይቆ፤ በፈቃዳቸው ላይ ተመስርቶ ውህደቱን ይሁን ግንባሩን የሚመሠረተው? በግራ ፖለቲካ ይህ ሂደት ቁሞ ቀር ነው። አባላቱም እንደ እኛ አባል እንድልሆነው ሚዲያ ላይ ነው እኩል ከእኛ ጋር የሚሰሙትእራሱ መሪዎቹ ማን መረጣችሁ ቢባሉ መልስ የላቸውእነሱም ብለው አያውቁም። 

አታጋይ አርማችሁን ማን አጸደቀላችሁ ቢባሉም እንዲሁ። ከላይ ራሳቸውን ቁጭ አድርገው ተመስርተናል ነው የሚሉት። በቃ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ይሄው ነው። ለመሆኑ በትክክለኛው መስመር የሄደ አንድ ለምልክት ለናሙና የምታቀርበው የፖለቲካ ድርጅት አለህን? ስለምን ይመስልሃል ሁሉም የግራ ፖለቲካ አንጡራ መንፈስ ወራሾች ስለሆኑ መርሃቸው የሆነው የዲሞክራሲ ማዕከላዊነት አምላኪ በመሆናቸው ነው። 


አሁን ይህ መንፈስ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ቅርፊት ቢፈርስም በሌሎቹ ያደጉበት ስለሆነ ጠቅልለው መያዛቸውን አመሳካሪ ቃል ከመፈግ፤ የመዋቅራቸውን ሊስት ዞር ዞር ብለህ ፈልግ እና ታምበት። ማንፌስቷቸውንም። ንግግሮቻቸውንም ፈትሽ። ይህም ብቻ አይደለም ሁሉ ቦታ አንድ ሰው ብቻ ነው ድርጅቱን ወክሎ እሚታዬው። ዝም የሚባለው ሰው ተፈርቶ አይደለም፤ እውነትን መድፈርም አቅቶ አይደለም፤ ለነፃነት ትግሉ የሞራል አቅም ሲባል ብቻ ነው።

ሌላው የሚገርመው የጉድ ቁንጮ ደግሞ የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት በአንተ ቤት ጨዋታ አሳምርኩ፤ አቃቂር አወጣሁ ብለህ „በማንቆረቁያ የሚንቁረቆር“ አድርገህ አምጥተኸዋል። ማርክስዚም ሌሊኒኒዚም ሳይንስ ነው። ከሳይንስም ልቆ ፍልስፍና ነው። አንድ የዕውቀትና የምርምር ዘርፍ ነው። የሚመረቁበት ሙያም ነው። 

ፍልስፍናው ትኩረቱ በነቃው ህሊና አስተዳደር እና አመራር ላይ ነው። መርሁ ዴሞክራሲያዊ ማዕላዊነት ነው። ጠላ አይደለም በማንቆርቆሪያ የሚንቆረቆር ወይንም የበተሃ ጠጅ አይደለም በማንቆርቆሪያ የሚንቆረቆረው። 

አንዷ ነጠላ፤ ወይንም አንዷ ዘለላ የተረፈ ዕሴት ፅንሰ ሃሳብ „Surplus Value Theory“ እንዴት እንደሚፈጠር ራሱን የቻለ የእድሜ ልክ ትምህርት ነው፤ የምርምርም ማዕከል ነው። 

የፈላስፋው የካርል ማርክስ የካፒታል መጸሐፍ ፍሬ ነገሩ የተረፈ ዕሴት ፅንሰ ሃሳብ „Surplus Value Theory“ ምንጩ እንዴት እንደሚፈጠር የሚያስተምር እጅግ ሩቅ፤ የቀደመ ፍልስፍና ነው። በሌላ በኩል አንድም ሀገራዊ ፓርቲ ከዚህ ፍልስፍና ውጪ ነኝ ማለት አይችልም። 


ምክንያቱም ሁሎችም ከዛ ከግራ ፖለቲካ ዘመን የተገኙ ናቸውና። ለምሳሌ የአማራ ተጋድሎን „የነፃነት ሃይሉ“ እንዲባል ያደረግነው እኛ ነን የሚል መልዕክት እጅግ በተሰበረ ልቦና ውስጥ ሆኜ አዳምጨዋለሁ። ካመንኩት መንፈስ ከግንቦት 7 ሊቀመንበር ግን ያልጠበቅኩት በእጅጉ አስደንጋጭ ነበር። ይህ የማዕከላዊነት ቁልጭ ያለ መንፈስ ነው። 

ስለምን ዋናው የተጋድሎ ጥያቄ አማራነት ነው። ይህ ከሆነ መቆናጠጫ መሬት አይገኝም። ስለዚህ ከፈቀደው ትግሉን ከሚያደርገው ከባለቤቱ ይልቅ እኔ በምልህ ሥም ተጠራ ነው የተባለው። በሌላ ድርጅት ቀልድ የለም። „በቄሮ“ ላይ ይህ ድፍረት የለም። ይህ ብቻ አይደለም የአንተ ዝግጅትም ይህን ማዕከላዊነት ተዳፍሮ አንዲት ስንዝር መራመድ አይችልም። ቃሏን አውጥተህ “የአማራ ተጋድሎ አትልም“ ሚዲያህ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ አልደፈራትም። የተከለከለ መንገድ ነው። 


የኦሮሞ ግን „የኦሮሞ ተቃውሞ“ ትላለህ/ ትላላችሁ። በሁለቱ ማህበረሰቦች ወጣቶች ማህል የተፈጠረው የሥነ - ልቦና አድሏዊ መንገድ እና የተጎዱ የሚሊዮን የአማራ የሥን - ልቦና ጥቃት የደረሰባቸው ጉዳይ አጀንዳችሁ አይደለም። ለዚህ ነው "ለቄሮ“ "መላዕክታኑ" ሲቆጡ ማዕበሉ ለሁሉም ተደራሽ ስለሚሆን ስለ እነሱ ብርቱ ጥንቃቄ ይደረጋል። የሚገርምህ ከዚህ አስኳላዊ ጥያቄ መነሳት ያልቻለ ማንኛውም ሂደት ሰላሙ ለዝንተዓለም ይታወካል። ህይወት ነዋ። ጉሮሮ ነዋ። 


ይህን መልክ ሳያስዝ አማራ ይተኛል ተብሎ አይታሰብም። ከትውልድ ወደ ትውልድ ተጋድሎው ይቀጥላል። ሃይልና ጠበንጃ ለደርግም አልሆነው። ሀገር የህዝብን ጥያቄ ፍላጎት አክብሮ በተነሳ መሪ ነው ጸጥ ብሎ መተዳደር የሚችለው። 

በእያንዳንዳችን መንፈስ ውስጥ ነበልባል አለ፤ የሚንቀለቀል ቋያ አለ። ነገን የሚጠብቅ። የደም ዋጋ በጭነት እና በማናሕሎኝነት አይወራረድም። በዚህ ሂደት ብቻ ረቂቅ አቅም በፍጹም ሁኔታ ባክኗል። ለዛውም የመንፈስ። ሥነ - ልቦናቸው ለተቀጠቀጠው የአማራ ተጋድሎ ወጣቶች ወታደሮች አለን።   
  • ·         ጫማሪ ጭብጥ።


 እንዲህ ይላል ተረበኛው ጋዜጠኛ አቶ ማስረሻ „እነ አቶ ለማ መገርሳ ያለን ምርጫ „መደመር“ ብቻ ነው ወደ ሚል አማራጭ የገቡት ሁላችንም ጠራርጎ ያጠፋል በበሩ ላይ እንዳገባ ስለገባቸውና ስለስደነገጣቸውም ጭምር ነው። ለማውያንን  በአዲሱ የፖለቲካ ጨዋታ ልዩ የሚያደርጋቸው በኢህአዴግ ውስጥ „የዘውግ ቆብ“ ደፍተው በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ማልያ የሚጫወቱ መሆናቸውን ነው። አቶ ለማ የኢትዮጵዊ ብሄርተኝነትን ማልያ ለብሰው ስለ ኢትዮጵያ አንድነት በባህርዳር ላይ የዘመሩት እንዲህ በማለት ነበር። …“

በነገራችን ላይ ይሄን „መደመር“ እንዲህ በግልብ ፖለቲካ የሚደፈር እንዳልሆነ በአጽህኖት ልነግር እፈልጋለሁየአብሮነት ጉልላት ነው። ሌላው ካነሳኽው ዘንዳ እንዴት ነው ሀገራዊ ንቅናቄውን ሲቀላቀሉ እኮ ኦነጋውያን ኢትዮጵያዊነትን ዘምረው አይደለምን? እነሱንም እኮ ነው አብረህ ጨመረህ እዬወቃኽ ነው ያለኸው።

መብታቸውንም ተዳፈርክ? ደግሞስ አገራዊ ንቅናቄ የሚባለው የኦሮሞው፤ የሲዳማ፤ የአፋሩ የዞግ ድርጅቶችን ስብስብ አይደለምን? ሌላው ስለ አቋም መገላበጥ ምነው ብተወን። እንዴት እንደሚያቅለሸልሽ። መገለባባጡ አሁንማ ዓመት መቁጠርም ተስኖታል፤ በዬወሩ፤ በየሩብ ዓመት ሆናል የአቋም ለውጡ የምናዬው። ስለምን? ቋሚ የሆነ ተከተታይ የመንፈስ ሃብት በእጅ ያለ ስሌለ። 

ፕሮፖጋንዳ ወንዝ የሚያሻግር ታንኳ እንጂ ወንዝ አይሆንም። የፖለቲካ ብስለት አማራር ብቃትም ተስጥዖም ነው። አባቶቻችን ከቶ ከዬትኛው ዕውቅ ዩንቨርስቲ ተመርቀው ነው  በትፍውፊት አዱኛ የከበረች ኢትዮጰያን ያቆዩልን? አባቶቻችን ጸጋቸው ሰማያዊ ነበር። አዬህ የፖለቲካ ብልህነት ወቅትን አስቀድሞ ተረድቶ ቀድሞ ማቀድ፤ መተለም እንጂ በነፈሰ ቁጥር መወዛወዝ አይደለም። 


መፍትሄ ተብሎ በታቀደው ታክቲክና ስትራቴጅ ቀበቶን ጠብቅ አድርጎ ሞጥሮ በጽናት በተከታታይ መታተር ያስፈልጋል። 

የፖለቲካ ትርፍ ተጥልሎ ወይንም ተበድሮ የሚገኝ ሳይሆን በህሊና የማድረግ አቅም፤ ህሊናን በማደረጃት አቅም፤ በጥበብ ክህሎት እና በጥንቃቄና በስልት በመምራት የሚገኝ ሰብል ነው። የማሰብ፤ የማሰብ፤ የማሰብ። የመሆን። የመሆን። የመሆን።

ዛሬ አንድ ገበሬ „ያለንበት ዘመን 21ኛው ምዕተ ዓመት ነው። ጦርነተን እንኳን የሰው ልጅ እንሰሳትም አይፈልጉትም“ እያለን ነው። ጭልጋ ገበሬ መንደር ያዳመጥኩት እንደዛ ነው። ዘመኑን የሚመጥን የመንፈስ አቅም ነው ሊመራ መቻል ያለበት እያለ ነው ያ ደሃ ገበሬ ከእነእርፉ፤ ከእነቀንበሩ ያለው፤ "አልተማረም ቁምጣ ለባሽ" የምንለው የሚነግረን። ዘመንን ለመምራት ሲሆን ቀድሞ በስተቀር አቻዊ ጉዞ ይጠይቃል። 

የሚገርመው ነገረ ኦነጋውያን የሚባል ኢትዮጵያን ተጸይፎ የተነሳን ድርጅት፤ ሻብያ የሚባል ሞቶ እንኳን ኢትዮጵያን ከማጥፋት የማይቆጠብ እንኳን ድሮ፤ ዛሬ የነፃነት ትግሉን አግዛለሁ በሚልበት ሰዓት የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ በአደባባይ የሚጠቀጥቅ፤ የሚያቃጥል ድርጀት አቅፎ ኦህዴድን ማብጠልጠል ምን የሚሉት የፖለቲካ አስተምኽሮ ነው? በፍጹም አይገባኝም። እንዲገባኝም አልፈቅድም። ለሰሚውም ግራ ነው። ሲወዱ እስከ ንፍጥ ልጋጉ ነው፤ ሲጠሉም እንደዛው።

ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ የአትዮጵያዊነት ብቸኛ ጠበቃ ሆነህ ይህን የአምክንዮ ሞጋች ፍሬ ነገር አላዬሁህምም፤ አልሰማሁህም ልትል ከቶውንም አትችልም። ኤርትራ ላይ እንደዛ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማህ ሲጠቀጠቅ በአደባባይ ብዙ ሚሊዮኖች ሲያላግጡበት ከቶ አንተ የት ነበርክ? ደፋሩ ጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ ዕውነትን ትራስ አድርጎ ወጥቶ ነበር የሞገተው። የማንፌስቶ ማህበርተኛ ስላልሆነ።  „ማማ“ ዝግጅትህ መሰረቱ አልባሳቱ፤ ጌጡና ተስፋው ብሄራዊ ሰንድቅዓላማ አይደለምንም? 

ባለፈው ዓመት አገራዊ ንቅናቄው ባካሄዳቸው ስብሰባዎች ሁሉ የነበረውን ዥጉርጉር ከቶ ዝግጅትህ እንዴት ነበር ያስተናገደው? ይህ ብቻ አይደለም አቦ ሌንጮ ለታ ቁርጥ አድርገው ነበር የተናገሩት። ብሄራዊ ሰንድቅዓላማውን ሲዩ ደማቸው ስለሚፈላ፤ ከዛም የጉልማ መሬት በጌቶቹ ተፈቅዶ ስለተሰጠው እሱም ስላልተመቻቸው ገና ለውይይት ይቀርባል ነበር ያሉት። 


ምነው ይህን የእውነት እንክብል መድፈር ተሰነህ? እንዲያውም ደልድል ብለው አቦ ሌንጮ ለታ „ወዳዳችሁም ጠላችሁም የኦነግ አርማ ቀጣይ ነው“ ነበር ያሉት። አቶ ለማ መገርሳ አሳምረው መልስ ሰጥተውበታል። ፈልግ እና አድምጠው ጋዜጠኛ አይደለህ። ለዚህም ነው አንድም ማገናዘቢያ ሊንክ ያለጠፍኩት። 


ያ የአቦ ሌንጮ ለታ ንግግርንም አንተ ባትጀምረው እንኳን ጀግና ጋዜጠኛን ተከትለህ የማጠናከሪያ ትንተና ለመስጠት ምነው ድፈረቱ አነሰህ? ብሄራዊ ሰንደቅዓላማችን እንደገና ለውይይት ይቀርባል ሲባል ከዛው ውስጥ እንኳን ተነስቶ የሞገተ ሊሂቅ አለመኖሩ ከቶ መንፈስህ አላሰረረውም፤ አላኮፈተረውምን፤ ደምህን አላስቆጣውም? የመንፈስ ጥግ አጥቶ መለመላውን ሲቆም እንደ ኢትዮጵያዊነት ተቆርቋሪነትህ ስለምን አልተሟገትክለትም? ይህን በሚመከትም ደፋሩ ጸሐፊ አቶ ታሪኩ አባድማ ፊት ለፊት ወጥተው ነበር የሞገቱት። 

ኢትዮጵያዊነት እና ጋዜጠኝነት፤ ኢትዮጵያዊነት እና ጸሐፊነት ኪዳኑ እዚህ ላይ ነው። ጎለጎታን እና ቀራንዮን መፍቀድ። ወይንስ አንተ አልነበርክም ምድር ላይ እኛ ይህን ስንመለከት አንተ ወደ ሜሪኩሪ መጥቀህ ነበርን? ለመሆኑ የት ነበርክ? በምታመልከው ማንፌስቶ ጉድብ ውስጥ?

ስለ ሰብዕዊነት በተቆርቋሪነት አንስተሃል። አሶሳ ላይ ንጹሃን የአማራ ህጻናት ትምህር ቤት ተዘግቶባቸው ሲነዱ፤ ሲቃጣሉ የሥጋቸው ጢስ ሰማይ ላይ ሲያርግ ለዚህ ተጠያቂው ማን ነው ብለህ አስበኽው ታውቃለሀን? 

ሌላው ቀርቶ ዛሬ እንኳን ጥያቄው ሲነሳ ግልጽነት ታዳፍኖ ማን እንደ ፈጸመው አናውቅም ሲባል ምነው የወገኖችህ ዕንባ አልጎረበጠኽም? አላንገረገበኽም? ንገሩን ያን ጊዜ ይህን ኢ - ሰባዕዊ ድርጊት የፈጸመው ሻብያ ወይንስ ኦነጋውያን ብለህ ስለምን አለሞገትክም? አንተ የ100 ሚሊዮን ኢትዮጵውያን ዕንባ አስጨነቀኝ እያልከን ነው እኮ። ታዲያ ይህ ከሆነ ማን አስፈራኽ እውነት ወይስ የሥጋ ጉዳይ ወይንስ የማንፌስቶ? ጋዜጠኛ ዕውነትን ከደፈረ የሚያጣው ጭብጨባን ብቻ ነው። ይህን ደግሞ ከልቡ፤ ከህሊናው፤ ከነፍሱ ጋር የወገነ ጋዜጠኛ አጥብቆ የሚጸዬፈው ስብዕና ነው። አያስጠጋውም የቲፎዞን መንፈስ።
  • ·         ዞግ።


ሃሳቡን ከላይ አንስቸዋለሁ ግን ማጠናከር እፈልጋለሁ። አሁን ስለጎጥ ድርጅት የሲዳማን፤ የአፋርንና የኦሮሞ ድርጅቶችን አቅፎ የሚንጎባለል ሚዲያ ስለዞግ ክስ ፋይል መከፈት አለበትን? የጎጥ ድርጅትን ያላቀፈ ድርጅት ኢትዮጵያ የላትም። ስለምን ኢትዮጵያ የምትመራው በጎሳ ፖሊሲ ነው። 

„ጎጠኞች አትበሉን“ ብለዋችኋዋል አኮ „የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ጉባኤያችሁን በስያትል ስታካሂዱ“ ዶር ሌንጮ ባቲ። „ይከፋናል“ ብለዋችኋዋል። እንዴት ነው ፍቅሩ በድርጎ ወይንስ በሲሶ ነውን? ፍርጥ አድርገው „እኛም ይሰማናል“ ብለዋችኋዋል። ጭጭ ነበር ያለከው አንተ ራሰኽ እና አይዋ ጋዜጠኛውኛ ማስረሻ አለሙ አቦ /ዶር ሌንጮ ባቲን ወጥትህ ለሞሞገት አልደፈርክም ትናንት። 

አቶ ለማ መገርሳም ኦሮሞ፤ ኦቦ /ዶር ሌንጮ ባቲም ኦሮሞ፤ ኦቦ ሌኔጮ ለታም ኦሮሞ፤ ኦቦ ለማ መገርሳም ኦሮሞ ምን ልዩነት አለው። ኦቦ ሌንጮ ለታ እኮ ኢትዮጵያ ድረስ ሄደው ነበር እኮ፤ ወያኔ በሄዱበት ትኬት መልሶ ነው የሸኛቸው። በሌላ ቃለ ምልልስም „አልተጠዬቅንም እንጂ በራችን ክፍት ነው“ እኮ ነው የሚሉት። እና አቶ ለማ መገርሳን የማብጠልጠል አቅምህ „አይህያውን ሲፈሩ መደላድሉን“ አያስብልህምን? 


ከውስጥህ ከራስህ ጀምር? ድፍረቱ ካለህ። ያንጊዜ በህሊናህ ውስጥ ሰለመኖርህ አንተ ራስህን የማዬት አቅሙም ክህሎቱም ይኖርሃል። የሲዳማው፤ የአፈሩ የኦሮሞ የዞግ ድርጀት እኮ ነው ኢትዮጵያዊ አገራዊ ድርጅት ነን የሚሉን። ኢትዮጵያን እንታደጋለን የሚሉን፤ ትናንት ከወያኔ ጋር ዛሬ ደግሞ ከባለተራው ጋር። አሁንም አገራዊ ንቅናቄው ከአውሮፓ ኮሚሽን ጋር ተቀምጫለሁ ሰነድ አዘጋጅቻለሁ እያለን ነው። 


መሆኑ ስለምን ይሆን ያን ብሩክ ሙሁር ፕ/ ፍቅሬ ቶሎሳን ይህ „የኢትዮጵያ ብሄራዊ የአንድነት ጉባኤ“ አክብሮ ያለተነሳው፤ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ገዳይ ማንፌስቶ መሥራች እና የወልቃይት እና የጠገዴ የዘር መንጣሪ አውራሪስ ዶር. አረጋይ በርሄን በክብር የጋበዘ ጉባኤ ስለ ኢትዮጵያዊነት የፊደል ገበታ የሆኑትን የመንፈስ ዲታውን ሙሁር ፕሮፌሰር ፍቅሬን ምነው በጎሪጥ አያቸው? ጥብቅናህ ለኢትዮጵያዊነት ከሆነ አዘጋጆችን ስለምን አልሞገትክም? ያው ፕሮፌስሩም ዶር. ፍቅሬ ቶሎሳም ኦሮሞ ናቸው። 

የነገረ አማራ ነገር ይከደንና። አዬህ በራሱ መተማመን ላይ የሰከነ ህሊና ድፈረቱ ከውስጥ ነው የሚነሳው። ትዮጵያዊነት ውጪ ላይ የምታሰጣው ጨርቅ አይደለም። ስለ ኢትዮጵያዊነት ጉድለት በታዬበት ቦታ ሁሉ ጋዜጠኛ ዓይኑ ጆሮው ጠረን አዳኝ መሆን አለበት። ብታውቀው።

ከዚህ ባለፈ ህብረ ብሄራዊ ነኝ የሚለውም መዋቅሩን ዝርዝር ስትመረምር እጅግ ያስደነግጣል። አካባቢው ሁሉ በራሱ ዞግ አጥሮ ነው ያለው። ይህም ብቻ አይደለም ተዋህድኩ ሲልም ሌላውን እዬገፋ ራሱን በውስጥ እያደራጀ ነው በራሱ ሰዎች። ይህን የማናውቅ ይመስልሃልን? 

በእያዳንዱ መንፈስ ውስጥ ጎጡን ያስቀመጠ መዋቅር ነው ተዘርግቶ ያለው። ርዕሰ አንቀፆችም እንዲሁ። ቀድሞ ነገር አማራ ተገልሎ „ ኢትየጵያዊነት“ አለን? መልስ አለህን ለዚህ ጭንቅላታዊ አመክንዮ። 

እውነትን የምትደፍር ከሆን ሰለምን ይሆነ አሁን ባላፈው ጊዜ አገራዊ ንቅናቄውን ጋዜጠኛ ሲሳይ ሲያወያይ „ነገረ አማራን“ አንስቶባቸው ውሹን ያነሳ ውሻ እንዲሉት የሆነው። አማራን አልቦ ኢትዮጵያዊነት የድቡሽት ቤት ነው። ብልህ የፖለቲካም አይደለም። በዬቀኑ ነው መንፈስ የሚሸፍተው። 


ስለምን ይሆን አገራዊ ንቅናቄው መተማመኑ ጠፍቶ በሁለት ተባባሪ ሊቀመንበር በአንድ የሥ/ አስፈጻሚ ሰብሳቢ የሚመራው? ነገ ደግሞ ሦስት ፕሬዚዳንት እንጠብቅ ይሆን? ያው ፕሬዚዳንታዊ እንዲሆን ነው ምርጫችሁ ግንቦቶች። 

ስለምን በዚህ ጉዳይ ላይ አጠገብህ ያሉትን ሊሂቃን አትሞግታቸውም? አቅም ቢኖር እኮ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት በማደናገሪያነት የተሰዬመው „የኢህአዴግ“ አባል ድርጅቶች እንደ መፍትሄ ባልታዩ ነበር። 

አዬህ ከመዝገብ ቤት በአንድ ቀንጣ ሰው በወጣ የሥም ዝርዝር የጥናት እና የምርምር ተግባር ብሎ ማማለል ሳይሆን መሬት ላይ መንፈስን በቋሚነት የሚይዝ፤ መንፈስን አደላድሎ በጽናት የሚያቆይ የአምክንዮ አቅም ነው ብልህነት፤ ሥልጡንነት፤ የፖለቲካ አማራር ጥበብም ነው። የምትጠበብበት። 


ለመሆኑ የትናትናው መንፈስ ዛሬ በመዳፍ አለን? እስኪሟጠጥ ካልጠበቀን በስተቀር ሳስቷል ወይንም ከስቷል። ስለምን? ከቃል አጠቃቀም ጀምሮ ለመንፈሳዊ ቁም ነገሮች ጥንቃቄ የለም ውስጥ ተጎድቷል። ተዉ ስትባሉ ደግሞ እንደ ወያኔ አድርጉ ተብሎ የተፈረመላችሁ ይመስል መንፈስን በሚጎዳው መንገድ መጭ ነው። አታዳምጡም። 

አዬህ የተከበርከው „የማማ“ ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢ ጋዜጠኝነት በራሱ መኖር ካልፈቀደ ማንዘርዘሪያ ወንፊት አይኖረውም። ማንዘርዘሪያ ወንፊት ከሌለው ያርጣል ሥነ - ምግባሩ እንዲህ ልፍስፍስፍ ሆኖ የሚታዬው በዚህ ምክንያት ነው። 

ከዚህ ያፈነገጡት ደግሞ ገጆሞ፤ ፋስ ነው ይሄ ነው የዴሞክራሲ ማዕከላዊነት አባዜ ማለት። ሙግት ላይ ብዙ ነገር እንታዘባለን። የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መጠራቅቅን ህግ ላለመተላለፍ የሚደረግ የውጪ ገቢ ነፍስ ግብግብ እናስተውላለን። ቢያንስ መድፊያውን ለማሳመር ሲጥሩም እናታዘባለን። ነፃነት የለም። ታሰሯል። 

ሙያ ሙያ የሚሆነው በቀለሙ ውስጥ መኖር ሲፈቀድ ብቻ ነው። ቢያንስ ለራሱ ነፃነት ሲታገል። ግን መስዋዕትነት ይጠይቃል። የሚቀረው የቲፎዞ ጭብጨባ ነውጋዜጠኛ ደግሞ የጭብጨባ ሃብት ሳይሆን የዕውነት ስንቅ ነው ሊያኖረው የሚችለው ቢያንስ በምንም ሁኔታ ላይ ተስፋ መጠጊያ ሲያገኝ ጋዜጠኛ አበረታች፤ አግባቢ፤ ድልድይ ዘርጊ መሆን ሲገባ እንደ የፖለቲካ ሊቃናት መሆን ያምረዋል። ጋዜጠኝነት እና የፖለቲካ ሊሂቅነት ልዩነት አላቸው። 


ጋዜጠኛ የሥልጣን ተፎካካሪ ሳይሆን አዕምሮን ጠራጊ ነው። ለዚህም ነው በሰለጠነው ዓለም እንኳንስ የፖለቲካ አባል ሊሆኑ ቀርቶ፤ የማንፌስቶ አምላኪ ሊሆኑ ቀርቶ፤ አምልኮተ ሰው ሊሆኑ ቀርቶ በዬትኛውም የድምጽ አሰጣጥ ሂደት አይሳተፉም። ሙያው አንተ ከምታራምደው መንፈስ በእጅጉ የራቀ ነው። 


አሁን አንተን እኔ እማይህ እንደ ጋዜጠኛ ሳይሆን እንደ ሥልጣን ተፎካካሪ ነው። መሆን ግን አልነበረበትም። ይህን እማ እነሱ አሉበት - ሙያቸው ነው የፖለቲካ ሊሂቃኑ፤ ተልዕኳቸውም ነው። አዬህ አሁን ወሳኝ ወቅት ነው። አቅምን ማወቅ በእጅጉ ያስፈልጋል። ቢያንስ ከራሱ ከሥርዓቱ ተባባሪዎች ከውስጡ የወጣውን የእንቢተኝነት አቅም አክብሮ መነሳት ይገባል። ስለምን? በእጅ የሚታይ የሚጨበጥ ምንም ነገር የለም። ተገላጠ፤ ተጠረ፤ ተፋ አሁንም እምናዳምጠው፤ እንደ ታች አምናው በዛው ላይ ነን። 

ለዜና እንኳን የሚሆን አዲስ የብቃት መንፈስ የተግባር ጭብጥ የእውነት ፍሬ ነገር የለም። ከወረቀት የቀለም ነቁጥ በስተቀር። ባይሆን እነሱ በሚያደርጉት ግብግብ ሚዲያው ይድመቅ እንጂ … ዜና የሚባል ነገር ያለው እኮ በእነሱ ፍትጊያ ነው። አይዋ ሚዲያ የሚልሰው የሚቀምሰው ያለው …
  • ·         „እንከባበር“


የዘንድሮ የታምረኛው የጎንደር መስቀል ባዕል „እንከባበር“ ጥሪ ለሁሉም ነው። አዬህ እንደ ጋዜጠኛ አንድን ሰው አስተሳሰቡን ልትጸዬፈው፤ ልትተቸው፤ ልትሞግተው፤ ላትቀበለው፤ ልታወግዘው ወይንም ልታከብረው፤ ልታዳምጠው ወይንም የእኔ ልትለው ትችላልህ። የእኔ የምትለው አስተሳሰቡን እንጂ ሰብዕዊነቱን ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። 

ግን ኢትዮጵያዊ ባህሉን - ትውፊቱን - ወጉን-  ልማዱን ግን ልትዘነጥለው አይገባም - ጋዜጠኝነቱ በውስጥህ ካለ። ያውም አንተ የኢትዮጵያዊነት ዓርት ዓይናማ ተቆርቋሪ አይደለህ? ኢትዮጵያ እኮ ባህል አላት። 


ኢትዮጵያ እኮ ወግ አላት። ኢትዮጵያ እኮ ልማድ አላት። ኢትዮጵያ እኮ የአናኗር ሥርዓት አላት - ያልተጠመነችው ወይንም ያልተዋሰችው። ኢትዮጵያ ሀገራችን ሃይማኖታዊ ትውፊት አላት። „ፈርሃ እግዚአብሄር“ የህዝብ ተሳትፎ የደመቀበት ዕሴት አላት - ያልተበደረችው፤ ያልተቀዬጠ ንጡር። ያልተበደረችው ሁለመና አላት፤ ዕዳ በወለድ የማትከፍልበት። 

አንተ ደግሞ የዛ ተጻራሪ ነህ። „አንተ አንቺ“ ብለህ ስለጠራህ ወይንም ስላልጠራህ የሚቀር የክብር ቁርጥራጭ ባይኖርም፤ ግን ኢትዮጵያዊነት ማለት ባህላዊነት ማለትም ነውኢትዮጵያዊነት ማለት ተፈጥራዊነት ማለት ነው። ማንም ይሁን ማንም ሰው ሆነው ሲፈጠር ከፍጥረት ልዑቅ ሆነው የተፈጠረ ነው።

 „ሰው የእግዚአብሄር ቤተ መቅደሱ ነው“ አሁን አንተኑ አጅግ ሊገለጽ የማይችል ረቂቅ ጸጋ እና ክህሎት የተሰጣቸው፤ ከዚህም ባለፈም መንፈሳዊው መክሊት ሆነ ቅድስናም በብጡልነት የተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ አንተን ቁጭ ብለው ያዳምጣሉ። አንተን በአንተነትህ አይደለም የሚያዩህ፤ በወከልከው ድርጀት ውስጥ ነው „ኢሳት/ ግንቦት 7 ይህን አደረገ ነው የሚባለው።“ ስለወከልከው ድርጅት አንዲትም ቅንጣት ክብር አልተቆረቆርከም፤ ጉዳይም አልሰጠኽም። 

ከዚህ ባለፈ ኢትዮጵውያን ታላላቆችን „ጋሼ፤ እትየ፤ አባ፤ ጥላዬ፤ ጋሻዬ፤ ወለላዬ፤ አሽኮይ፤ ወተተይ“ ያላገቡትን „ወ/ት የአገቡትን ወ/ሮ“ ያገቡትን ይሁን ያላገቡትን „አቶ“ እያለ ነው የሚጠራው። አንተ ደግሞ በቃ ተመቸኝ ብለህ በስማቸው እያንጠለጠልክ ነው የጠራኽቸው። ማድጋ እንኳን ጆሮ አለው። እንዴት ያለ ቤት ውስጥ ነው ያደከው? ለዛውም የፖለቲካ ሊሂቃን ሙሴ እኮ ናቸው። 


ያከበርከው አንድ ነገር ብቻ ነበር „ዶር.“ ያው የቀለም አምልኮት በዬትኛው ድርጅት፤ በዬትኛው ዘመን እንደተ ተጀመረ አሳምረን እናውቃለን። ይህ ፍልስፍናም የማን እንደሆነ እንረዳለን። የሆነ ሆኖ የተጀመረው መቼ በእነማን እንደሆን ይታወቃል። „ማማ“ እያልክ ባህላችን  - ወጋችን - ልማዳችን - ትውፊታችን - ግን እስከ አሻህ ጠቅጥቀኸዋል፤ አዋርደኸዋል። እጅግ ታሳዝናለህ።
  • ·         ወያኔ ሃርነትን ጥሎ ሰለመወጣት።


አቶ አባ ዱላ ገመዳ እና አቶ በረከት ስምዖን ተከታትለው ነበር የወጡት። ሁለቱንም አድማጮች እኩል አላስተናገድነውም። የአቶ አባ ዱላ ገመዳ ቀልባችን የሳበ ደፋር እርምጃ ነው ብለን ነበር አክብረን የተቀበልነው። የአቶ በረከት ግን ከእናንተው „ከትንሳዬ ራዲዮ“ በስተቀር ያደነቀው፤ የከበከበው የለም። ለሚዲያ ፍጆታ አይከፋም ነበር ያለነው „ትንሳኤ“ ራዲዮ ግን "የብአዴን ቢሮው በስልክ ደወል ተጨናነቀ" ብሎ ነበር የዘገበው። ያሰቃል። 

ለዛውም በአማራ መሬት አይደለም መልቀቅ ለዘለዓለም ወደ እንጦርጦስ ቢሰናበቱ እንኳን በአማራ መንፈስ ውስጥ አንድ ቀንጣ መንፈስ ጥግ ሊኖራቸው አይችልም፤ ለአቶ በረክት ስምኦን። 

ምክንያቱም የሚያገናኘው የደም መስመር ስሌለእኛም የሳቸው አይደለነም እሳቸውም የእኛ አይደሉም 


የተፈጠሩት ለጥፋት ነው የተፈጠሩበትን ደግሞ በታላቅ ሴራዊ ዘመቻ ከውነዋል። መልቃቃቸው ስለምን ለሚለው ግን እንደ ተባለው ወያኔ ሃርነት ትግራይ በአባ ዱላ ገመዳ ተደናግጦ የሰራው ተውኔት ነበር፤ አሱም አልሰራለትም። 

ማንም ሰው የ አቶ በረከትን ከሥልጣን መልቀቅ ኩሸት እንደ ጠቃሚ ነገር አላዬውም ነበር። አንደ ተጠቅሞ እንደ ተጣለ ዕቃ ነበር ያዬው። የሁለቱ የአወጣጥ ጉዳይ በሚመለከት ለአቶ በረከት ስምዖን መልቀቂያውን ተቀብለናል ነው የተባለው፤ የአቶ አባ ዱላ ገመዳን ግን እዬጠና ነው ነው ዓይነት ነበር፤ ጠ/ሚር አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ያሉት። ለምነው ለማስቀጠል ትልም ነበራቸው። ስለምን? አቶ በረከት ስምኦን በታቀደ፤ አባ ዱላ ገመዳ ግን ከወያኔ ሃርነት ፈቃድ ውጪ ያፈነገጠ መልቀቂያ ስለነበር። 

ለነገሩ „የቅርብ ሟዋት የቹቻ መንከሪያ“ ይሆናል ሆኖብህ እንጂ ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ኤርምያስ ለገሰ እኮ በሚገርም አቀራርብ የሁለቱንም የጭብጦች ፍሬ ነገሮች አስተምሮኽ ነበር። መመዘን ብትችል። ለመማር ብትፈቅድ ያነሳቸው ነጥቦች የአመክንዮ አቅማቸው ጉልበታም ነበሩ። ለአባ ዱላ ገማዳ በኢትዮጵያ ሱማሌ እና በኦሮምያ የተነሳው ግጭት ስለ ጠፉ ነፍሶች፤ ስለተንገላቱ ዜጎች ጉዳያቸው ነው። 

እንደ ሰው ውስጣቸውን አንዲመረምሩ ትናንት በሌሎች ላይ የሆነው በፈረቃ ከሳቸው ላይ ሲደርስ ደማቸው ተቆጣ ይህም አዎንታዊ ነው፤ አቶ በረከት ስምዖን ግን በጎንደር ደንበር እና በሱዳን ደንበር በሽታ - ሽቶ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰራዊት እና በሱዳን ጦር 27 ዓመት ተቀጥቅጧል። ሳንዱች ነው የሆነው ያ አሳረኛ አሁንም ባለቤት የሌለው ህዝብ። 

ሌላው ቀርቶ በአቶ አባይ ወልዱ ትዕቢት የግልሰብ ቤት ተጥሶ ጎንደር ላይ ህጻናት ሲያልቁ፤ አንባ ጊዮርጊስ ላይ በሱዳን ወታደሮች 26 ህጻናት ሲጨፈጨፉ፤ ባህርዳር በአንድ ጥጋበኛ ተጋሩ 50 ዜጎችን በግፍ ሲረሸን፤ ያ የእሳቸውን ነፍስ ታድጎ የኖረ ቅዳሜ ገብያ ከትግራይ ቤነዚንና ክብሪት ይዘው የመጡ ደመነፍሶች ሲያነዱት፤ አመድ ሲያደርጉት አቶ በረከት ስሞዖን ጫጉላ ላይ ነበሩ። 

ይህን የሚያስደርጉትም በሳቸው ይለፍ ነው። ምናቸው ነው ለሳቸው አማራስ፤ ጎንደርስ፤ ባህርዳርስ? እንዲያውም „አይደገምም“ ቲሸርት ያሰሩት፤ ኮርስ ያዘጋጁው የእሳቸው መንፈስ ነበር። ይህም ሆኖ ተባዳዩ እንደ በዳይ ትግራይ ድረስ ሔዶ ይቀርታ እንዲጠይቅ ተደረገ። ከኢትዮጵያ ሱማሌም መቋቋሚያ ተለገሰ። በማን ፊታውራሪነት በአቶ በረከት ስምዖን። 

ስለሆነም ሂደትን በበሰለ የህሊና አቅም መፈተሽ የማይቻል ከሆነ አለመነካካቱ ይሻለህ ነበር። „አቅምን አውቆ መኖር ታላቅ ችሎታ ነው“ እንዲሉ። ሞጋች ነጥቦችህ ያረገረጉ ናቸው። አፋፍ ላይም የተንጠለጠሉ። 
  • ·         „ኢህድግ“


„ወያኔ/ ኢህአዴግ“ በዚህ ዙሪያ በተሻለ አቀራረብ የማዬው አሁንም ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ነው። የቆረ ይመሰላል። አንተ ግን ገና ነህ። የምትፈራው ነገር አለህ። ገና ከዚህ ማዕቀፍ ውስጥ አልወጣህም። በፍጹም። ኢህአዴግ አለነበረም፤ ኖሮም አያውቅም። የኖረው የየወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት ብቻ ነው። ይህን ከእናንት በስንት ጊዜ ቀድመን ተናግረነዋል - ጽፈነዋል።

„ኢህአዴግ“ ለውጪ ለዲፕሎሚያሳዊ ግንኙነት በመድብለ ፓርቲ ኢትዮጵያ እዬተመራች ናት ለማለት የተሠራ ሽሙንሙን ቅርፊት ነው። የትግራይ ሊቃናትም ይህችን ፍሬ ዘር አይደፍሯትም። 

እነሱም በቀጣዩ ዕድል የትግራይ መሳፍንት ሥርዕዎ መንግስት ናፋቂዎች ናቸውና። በሌላ በኩል ሌላ ስውር የፖለቲካም ቅምረት አለበት - ለዛሬ አልነካካውም። ዛሬ እንዲህ ገመናው ሊፈርጥ ተከድኖ የበሰለ የጉድ አዚም ነበር - ጉድጓድም። 

ስለሆነም ባይሆን ዛሬ እስኪ ድፍረው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ ሲመራ እንደ ነበር። በምን መርህ በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት። ስለሆነም የሚሊዮኖችን ድምጽ ከመጻረር መቆጠብ ትርፉ ለምትወክለው ድርጅትም ጭምር ነው። ምታ መልካም ነገር ነው። አሁን ከሚናገረው ይልቅ ዝም ያለው ኢትዮጵያዊ ይበልጣል። 

ዝም ብሎ የሚመለከተው ቢናገር ምን ሊበጅህ እንደሚችል አላውቅም። አዬህ ተስፋ ቃሉ ብቻ የማግሥት ስንቅ አይሆንም። ተስፋ የማግሥት ስንቅ ሊሆን የሚችለው ያለውን አቅም በአቅም ውስጥ በቅንነት መቀበል ሲቻል ብቻ ነው። 

አቅም በፉከክር አቅም ሊሆን ከቶ አይችልም። መዳኛ መንገዱ በታቀደ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ባልታቀደም ከመጣ መዳኛ ብቻ መሆኑ እንጂ ሃይማኖቱ፤ ያነሳሰው ምክንያት፤ ጎሳው መሆን አይገባም። ጉርጎራም አያሰፈልገውም። 

ጠብ ጠማኝም መሆን የተጋባም አይደለም። አቅሙ አቅም ፈጣሪነቱን ነው በጽሞና መመርምር መፈተሽ የሚገባው። አዬህ ኢትዮጵያ ሀገር ውስጥም / ውጪ ሀገርም ባለቤት ካላቸው ይልቅ የሌላቸው ወገኖች እንበልጣለን። 

ለዚህ ደግሞ አንተ ባብጠለጠልክበት መንገድ ሳይሆን በኖርንበት ተመክሮ፤ ከእኛም የላቁት በፍልስፍና ሙያ የሰከኑት፤ በሃይማኖትም ዕውቀት የበለጸጉት ሁሉ እንደ አንተ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ“ ነውን አልተጸዬፉትም። አቃቂርም አላወጡለትም። 

እንዲያውም በዚህ ዙሪያ ተከታታይ ወርክሾፖች፤ የትምርት ተቋማት ሁሉ እያደረጉበት ነው። እኛ እንኳን ወደዚህ መንፈስ መንፈሳቸውን አቃናልን፤ አመጣልን ብለን አማላካችን ፈጣሪያችን አናመስግንበታልን። ተጽናንተንበታልም። ነገን አማትርነበታልአየህ መጠጊያ ያጣች የአንተ ወገን ደስ ሲላት ይከፋሃል ብዬ አላሰብም ነበር። ደስታዬ ነው ስትል ግን ደስታሽ አይደለም ብለህ ሳቋን፤ ተስፋዋን፤ ህልሟን ልትቀማት አይገባም። ይሄ ወንጀል ነው። 

ብዙ በዞጋቸው፤ በጾታቸው፤ በአቅማቸው መጠጊያ፤ መጠለያ ያልነበራቸውን ሁሉ ነው „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ያቀፈው። እኔ ባጣጣምኩት፤ እኔ በወደድኩት መልክ ወደ እኔ እንዲመጣልኝ ሰው ነው እመታትረው። ሲመጣልኝ እሰዬው ነው። ተስፋዬ ይጨመርልኛል። ተስፋዬ ይዳብርልኛል። ተስፋዬ ይፋፋልኛል። እንቅጩን ልንግርኽ አዎን እኔ ሥርጉተ ሥላሴ „ለማዋያን“ ነኝ። 

እንዲያውም ይህን ስሜቴን በ2013 ይመስለኛል „አቶ ሂደት“ በሚል የጻፍኩት እርእስ ዘሃበሻ አውጥቶልኝ ነበር። በምክንያት መደገፍ በምክንያት መቃወም። እንደ ወራጅ ውሃ መናጆነት እንደ ሰው ይቀፋል።

አንተ እነዚህ የኦህዴድ የፖለቲካ ሊሂቃን ጭራሽ ከእውቀት ውጪ ሆነው የተፈጠሩ ዕብን አድርገህ ተመልክተሃቸዋል። ይቅር ይበልህ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ በማንቆርቆሪያ ያንቆረቆረላቸውን ብቻ ይዘው ተነሱ ነው የምትለው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ እንዲህ የቀደመ፤ እንዲህ የሠለጠነ፤ እንዲህ አቅም ያለው፤ እንዲህ የብዙሃንን መንፈስ የመግዛት ተፈጠሮው የለውም። ከዬት ሊያመጣው። 

አግልግሎቱ ያለቀ ነው የወያኔ ሃርነት ትግራይ እራሱ መንፈሱአንተ ደግሞ የምትነግረን አዲሱ ኦህዴድ ካቢኔ መመራመርም፤ አዲስ ሃሳብ ማፍለቅም፤ ጊዜን ማድመጥ እንደማይችሉ፤ ጭንቅላታቸው አቅም እንደሌለው፤ ከራሳቸው ጋር እንዳለሆኑ፤ ምንም እንደማይችሉ ግዑዛን አድርገህ ነው የሳልክልን፤ አሳዘኙ ነገር የሥነ - ልቦና አቅማቸውን ስስነት ዘለግ አድርገህ ተርከህልናል። 

በራሳቸው የመቆም የማይችሉ ጥገኛ አድርገህ ለማሳዬት ሞካክረሃል። ሞግዚት የሚሻ ሰብዕና እንዳላቸው ነው የምትነገርን። አዬህ ያላወቅከው ነገር እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ የእኔ የሚለው ልዩ መልዕክት እና መክሊት ይዞ እንደሚወለድ ነው። ሁኔታው እስከፈቅድለት ፈቃደ እግዚአብሄር እስኪሆን አንዬውም። ሰማያዊ ጸጋ እና መክሊት ርቁቅ ነው። 

ጊዜ ብቻ ነው ይህን የሚገልጠው። በተለይ አቶ ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ ግልብ የሆነ ነገር አይታይባቸውም። በራሱ ላይ በጽናት የቆመ፤ ተወራራሽነት ያለው፤ መሬት ያያዘ የውስጥ ብቃት እና ክህሎት ነው በነፍሳቸው መንበር የሚታዬው። 

ይህን አቅም ተፎካካሪ ሆኖ መውጣት ለቀደምት ሊሂቃን ፈታኝ ነው። በፖሮፖጋንዳ የሚጠገን አቅም ከእንግዲህ የሚኖር አይመሰለኝ። ነፍስ ያለው አቅም እያዬን ነው ነፍስ ያለው አቅም በብልጫ እንኳን ቀርቶ በአቻነት ካልሆነ አሸናፊው አቅም ቀጣይ ነው  በአበል የብዙሃን የመንፈስ ዲታ ድጋፍ እና ድልድይነት።፡
  • ·         „ጀሮጠቢነት“


የሚገርመው „ጆሮ ጠቢ“ የሚል ቃል እጅግ አቃላህ አንስተሃል፤ እንደ ስድብም ያደርገዋል አጠቃቀሙ። ለመሆኑ ስለ ኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከጫፋቸው ድርሽ እንዳንል በመንፈስ ድንበር እንደ ተሰራ አታውቅንም? 

ሆነ ሆኖ ፕ/ ኢሳያስ አፈወረቂ የሰሩበትን የሥራ ምስክ ታውቀዋለህን? የራሺያው መሪስ ፕሬዚዳንት ብላድሚር ፑቲን የሰለጠኑበትን ሙያ ታውቀዋለህን? ሲ.አይ.ኤ ሆነ ሞሳድስ የተመሠረቱት የማንን ጎፈሬ ሊያበጥሩ ይመስልሃል? 

የደህንንት ሙያው ምንድ ነው ተልዕኮው? የአንተ ደህንነትን ማን ነው የሚጠብቅልህ በምትኖርበት ሀገር? አንድ ሀገር  ሉዕላዊነትን አስጠብቆ የሚያኖረው/ የሚያኖራት ትልቁ ህዋስ የትኛው ነው? ታውቀዋለህ እንደ ጋዜጠኝነትህ። አየህ ነውር አይደለም የደህነነት ሠራተኛ መሆን። ሙያ ነው፤ ሙያው ደግሞ ከልቦና ፈቃድ የመነጨ ነው። ብሄራዊ ስሜቱ እጅግ ልዑቅ ነው - ፖፕሊስትም ነው። ከዬትኛውም ድርጅታዊ መዋቅር በላይ ነው። 

ሁሉ ነገር በመዳፉ ነው። ከዚያ በላይ ባለበት የሚረግጥ ሳይሆን በዬዕለቱ ከዓለምአቀፍ ሁኔታዎች ጋር በፍጹም ሁኔታ የተቆራኘ በመሆኑ ሥልጡን ነው። ግሎባል ነው። አፈጻጸሙ አዳጊ ነው። ምክንያቱም የሚከሰቱ አዳዲስ ሁነቶች አጥነቶ መቋቋሚያ መፍትሄ ካለፈለቀ ተጠቂ ነው። ተጠቂነቱ ደግሞ የግለሰብ አይደለም የህዝብ ሰላም እና ደህነነት ነው። በነፍስ ኔቱ ሁለንትናዊ ነው። አልሰማህም ከሰሞናቱ ስለፕ/ መንግስቱ ሃይለማርያም ተላልፎ የመሰጠት ጉዳይ የሚኖሩበት ሀገር መንግሥት የሰጡትን መልስ። 

እርግጥ ነው ታች ሲወርድ አማተር ነው የሚሆነው፤ የግራ ፖለቲካ በሚያራምዱ ሀገሮች። ከዚህ ርዕዮት ያመለጡት ግን ከካድሬ ጋር ንክኪ ሰሌላቸው በዕውቀት ላይ የተመሰረተ የማዋቅር አደረጃጀጃት ነው ያለው። 

እንደኛ ያለች በግራ ፖለቲካ ሴራ በምታተመስ ሀገር ደግሞ ይህን ሙያው  አብሶ ታች በትምህርት ተቋማት፤ በመኖሪያ አካባቢዎች ወያኔማ በሃይማኖት ተቋማት፤ በሲቢል ማህበራት በካድሬዎቹ ያስፈጽማል። በነገራችን ላይ የግራ ፖለቲካ ደንጋጣ ነው። በፍቅር፤ ተፈቅዶ ተውወዶ አይደለም ሥልጣን የሚይዘው፤ የሚያሰነብተው የጠበንጃ ሃይል ነው። ስለዚህም ርብትብት ነው። ለዚህም ነው ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን የሙጥኝ የሚለው።

በሌላ በኩል የሰው ልጅ የፈቀደውን ሙያ የመማር ሙሉ መብቱ ነው በሌሎች ሀገሮች። በኢትዮጵያ ግን በፍላጎት አይደለም የትኛውም ሙያ። 

ተማሪያዎች የትምህርት ተቋማትን ሲቀላቀሉ በኮታ ነው። ስሜታቸው ተጠንቶ፤ ፍላጎታቸው ታወቆ፤ በበለጠ ትርፋማ ሊሆኑ የሚችሉበት መንገድ ተጠንቶ፤ ዝንባሌያቸው ታይቶና ተመዝኖ፤ በዝነባሌያቸው እና በፍላጎታቸው ከሥር ጀምሮ ተኮትኩተው አያድጉም። 

በዚህም አንጻርም ሲታይ ፍረጃው አግባብ አይደለም። ለማቀለል ሆነ ለማሳጣት የሄድክበት መንገድ ውስጥህን እንድናዬው፤ እንድንፈትሸው ግድ ብሏል። ኤርትራ ድረስም መጓዝህንም ያስተዋልከው አይመስለኝም። ለአንተ አይተወቅህም  በአርምሞ ሆነ ለሚያዳምጥህ ግን ካልሆነ ቦታ ሄደህ ነው የተቀረቀርከው። መቼም ኤርትራን ዝንቧ እሽ ማለት እንደማይቻል አንተም ታውዋለህ። የሆነ ሆኖ ሰከን በል እንደ ሙያው ሥነ - ምግባር። 
  • ·         „ነብይ በሀገሩ አይከርም።“   


„በለማውያን“ ጆንያ ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ ከሰለቃቸው ንጹህ ቅናዊ ዜጋ ማህከል ዶር. አብይ አህመድ ይገኙበታል። ስለ አዶር. አብይ አህመድ በቃኝ አስክትል ድረስ በጉልበታም አማክንዮ ሟተትነት በቀጣዮቹ ጹሑፎቼ ጠብቀኝ። አታውቃቸውም። በስሜት ብቻ ተነሳስተህ አትወርፋቸው። 

እስቲ ይውጣልህ! እኔስ እላለሁኝ - በእኔ ትውልድ ኢትዮጵያ አንዲህ የሆነ ንጹኽ ቅን ልቦና ያለው፤ ከሴራ ፖለቲካ የራቀ የፖለቲካ ሊሂቅ አግኝታ አታውቅም! ዶር. አብይ አህመድ ሥጦታችን ናቸው። ሞጋች እና ምክንያታዊ ሃሳብን ፈሪ እንዳይመስሉህ እንደ ደንጋጦቹ የፖሊቲካ ሊሂቃን፤ ከምስጋና ጋር ነው የሚቀበሉት - አድንቆትም አለበት ለሃያስያኑ።  አብይ ኬኛ!  ይህ በህልም የማይታሰብ ነው ለኢትዮጵውያን ለመላው የኪነ ጥበብ ቤተሰቦች፤ ለጸሐፍት፤ ለከያንያን፤ ለባለቅቤዎች፤ ለገጣምያን፤ ለጋዜጠኛች፤ ለሳዕልያን፤ ለሃያሳያን። 

ከሳቸው ጎን /ከዶር አብይ አህመድ/ መቆም የተሳነው ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ ለምን እና ስለምን እንደሚታገል መንገዱ ጠፍቶበታል። አያውቀውም። አቅጣጫ ጠቋሚ መሳሪያው ተሰብሯል ወይንም አልተፈጠረለትም። 

ነፍሱን ይማረው እና ያ ደፋር ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ እና ዶር. አረጋይ በርሄ ለአንድ አመት ሙግት ላይ ነበሩ በአንዲት ዘለላ ወቀሳ፤ ጉግሱን ይስተናግድ የነበረው በራዕይ መጽሄት አውደ ምህረት ነበር። 

ያን ጊዜ እንዲያው እኒህ ሰው ሥራ የላቸውም፤ እንዲያው የሀገር መሪስ ቢሆኑ እንዴት ሊያስተናግዱት ይሆን ይህን የሃሳብ ነጻነት ሰፊ ማሳ ብለን ነበር። በዶር. አብይ አህመድ ልቦና ግን ነፃነቱ ከታወጀ ቆየ። ጥሩ ተናጋሪ ብቻ ሳይሆኑ ጥሩም አድማጭም ናቸው። ጥሩ አድማጭ ደግሞ የመፍትሄ መንገዱ  በእጁ ነው። ከህዝብ ፍቅር በላይ ምንም ሃብት የለም። የፍቅር ተፈጥሮም ታታሪ ናቸው። 

እኛ እኮ ከሞትም የምናዳላ፤ ከእስራትም አጋ የምንለይ እኮ ነን። ብዙ ነው ጉድለታችን። ቀዳዳችን ስፍር ቁጥር የለውም። ይልቅ ስምህ ጋዜጠኛ ማሰረሻ አለሙ እጅግ የማከብረው፤ የምሳሳለትም የአንድ የትግል ጓዴ ስም ነው በዚኸው ልሰናበትህ። ሙግት ካሰኘህ መምጣት ትችላለህ። ተሰናድቼ እጠብቅሃለሁ። ደስ እያለኝ አዝናናቼ አዘናክቼም አስተናግድሃለሁ።፡
  • ·         ብልህነት በልባምነት።


የዛሬው ዕድል ከበፊቱ በፍጹም ሁኔታ የተለዬ ነው። ቀደም ባለው ጊዜ ህብረት፤ ቅንጅት፤ አንድነት፤ ሰማያዊ፤ መኢህአድ በኢኮኖሚ አቅማቸው ብቻ ሳይሆን በሃሳብ በራሳቸው ውሳኔ ብቻ ለመንቀሳቀስ አጋጣሚ አልነበራቸውም። የውጩ ደጋፊ ሃይል ጥገኛ ነበሩ። የውጭ ሀገሩ ደጋፊ የበላይ በሆነ ስሜት መጓዙ ብቻ ሳይሆን፤ ሲከፋፈሉም መሬት ላይ ያሉት መከራቸውን በጋራ እንዳይስተናግዱ ደንቀራ ነበረባቸው። አሁን ግን የምንም ነገር ጥገኛ አይደለም ያኦህዴድ የበቃኝ መንፈሱ እራሱን የቻለ በራሱ የውስጥ ጥሪት ተቋም የፈጠረ ነው። „ልብ ያለው ሸብ።“

  • ክወና ለቅኖች ብቻ --- የምክንያታዊ አብዮት ህዋስነት ወይንም አስፈላጊነት።


ባዶ ተስፋ ታቅፎ መኖር ድል አይደለም። አጋጣሚዎች እስከ አሁን ልብ ሳንል፤ ከውስጥ ሳናዳምጣቸው፤ በችግሮች ላይ መሰረት ያለው ጥናት ሳናደረግ የችግሮች መንስኤ እንደ ተከደኑ በሚጀመሩ አዳዲስ መንገዶች ብቻ መጪ ማለት ብክንት ብቻ ነው የተተረፈው። መስዋዕትነቱንም አከበደው፤ አጨለመው። 

በመጀመሪያ ነገር የታላፉ የትግል ጊዜዎች ፍርጥር አድርጎ፤ ችግሮችን ከመነጋገር እንደ ዋዛ ይታለፋሉ። ለዛውም ደም የተገበረባቸው። በነባሮች ችግር ውስጥ መፍትሄ ያለተሰጡባቸውን ችግሮች እንደ ተሸከመን ነው አዲሱን የምንጀምረው። በሌላ በኩል የምንቃወማቸው ነገሮች በሊሂቃን መካከል ባለው የፖለቲካ ፍትጊያ እንጂ በተስፋችን ውጤታማነት መሰረታዊ አመክንዮች አይደለም። 

ስለሆነም አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ብልህንት የጎደለው ጉዞ ነበር የእኛ ትውልድ ያስተናገደው። ይህን መስምር ቀጣዩ ትውልድ ማስተናገድ ስለማይገባው ወጣቶች የሚያገኙትን አጋጣሚ በአግባባቡ ይጠቀሙበት እና ያስተዳደሩት ዘንድ በቅንነት መምከር ያስፈልጋል። አንድ ዕድላም ወቅት የሚሰጠውን የእናት ልጅም አትሰጥም። ፍጽምና ከማንም የለም። 

ፍጽምናን መጠበቅ ከተፈጥሮ ህግ ጋር መተላለፍ ይሆናል። በሌላ በኩል አንድ ጊዜ ያመለጠ ዕድልን መልሶ ለማግኘት የሚያስከፍለው መስዋዕትነት ዋጋውን መተመን አይቻለም። እድሉ ተመልሶ ቢገኝ እንኳ በመጀመሪያው እሸት አጋጣሚ በይዘትም በውጤትም አይመጣጠንም። 

ስለሆነም ቅን ኢትዮጵውያን ድጋፋችን ሆነ ተቃውሟችንም ምክንያታዊ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን የተጋድሎ ጊዜው በተራዘመ ቁጥር ጤነኛ የሥነ - ልቦና አቅም ያለው ማህበረሰብ መገንባት ከህልም ሊያልፍ እንደማይችል ልብ ልንለው ይገባል። 

በፍርሃት፤ በስጋት፤ በሞት፤ በዕንባ፤ በሰቀቀን ብቻ የተገነባ ትውልድ ውስጡን እያጣ የሥነ - ልቦና ተጠቂ መሆኑ ባለሙያ የሚያስፈልገው አይደለም። ሥነ - ልቦናው ያልተሟላ ትውልድ ደግሞ ሃላፊነቱን መወጣት አይችልም። የጠንካራ ሀገር ማገርም አይሆንም - ድፍረት ያነሰዋልስለዚህ መወሰን፤ መቁረጥ ያስፈልጋል። ትንቢት ከመጠበቅ በእጅ ያለውን ፍሬ በአግባቡ መጠቀም ይበጃል። 

ኔ እንደማስበው ከራዕያችን ፍላጎት ጋር አለመግባባት misunderstanding እንዲሁም የግንኙነት Communication ችግር ያለብን ይመሰለኛል። 

ይሄ ለፍላጎት ሆነ ለራዕይ መታመንን አቀጭጮታል፤ ስለሆነም ነው በፍጎታችን ውስጥ አለመግባባት እና የግንኙነት ችግር አጥንተን የማያዳግም መፍትሄ ለመማጣት የአማክንዮ አብዮት ያስፈልገናል የምለው። ይህ ካላስተካከለን መታመነን ለፍላጎታችን ማስታጠቅ አንችልም። 

ስለሆነም ወጣቶች የራሳችሁን የቤት ሥራ ለመስራት መትጋት ይኖርባችኋል። ለዛሬ ታዳጊ ወጣቶችም መሠረቶች እናንተ ናችሁ። ይህም ማለት የቀጣይ አደራ ባለድርሻ ናችሁ። 

·        ማስታወሻ እፍታ፣ ጠብታ፤ የወግ ገበታ፤ ቃና፤ ማዕዶት፤ መክሊት፤ የሎሬት ተስፋ፣ ውርሰ ጽናት ሚዲያ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በመመሪያ አጋፋሪነት የተጠቀምኩባቸው ሃይለ ቃሎች ናቸው። ስለሆነም እፍታ ሃብትነቱ የእኔ የራሴ ስለሆነ ነው በጥቅስ ያላስገባሁት። እንኳንስ እኔ ልዘርፍ ሲዘረፍም ያሳዝናኛል። „ህግ ተላላፊዎችን ጠላሁ“ ብሎ አስተምሮናል ነብዬ እግዚአብሄር ልብ አምላክ ዳዊት።
 
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።


እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።