ምጥን።

       ምጥን።
ከሥርጉተ - ሥላሴ(Sergute©Sselassie)
 06.03.2018 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ)

      „የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፤ 
እግዚአብሄር ደግሞ አካሄዱን ያቃናለታል።“ 
(ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱)
  • ·        መነሻ።
ጤና ይስጥልጥኝ የማክበረዎት አቶ ሰርጸ ደስታ፤ እንደምን አሉልን።
ቢያንስ ቪኦኤና ዶቼቪሌ እንዴት ዋሹን? ይቅርታ ይጠይቁን!! አዋጁ አልጸደቀም! (ሰርፀ ደስታ)

 ህግ ገዝቶት ለማያውቀው ማህበረ ፈርዖን ቁጥር ሳይሆን ሰው ስለመፈጠሩም ያልተቀበለ፤ ሊቀበልም የማይፈቅድ ስለመሆኑ በዚህ ጉዳይ ሃሳብ ለመስጠት አይደለም የዛሬው ጉዳዬ።

በሌላ በኩል ጉዳይ እኔን ስለማንሳተዎት ሳይሆን ፍላጎታችን የንፋስ ቤተኛ ስለሆነ ምጥን ማመጣጠን ያው ሴታዊ ተግባሬም ነው - የሽሮዋን ተክተክ ይሰቧት እንደ ማለት። ስለሆነም ዛሬም የምለው ይኖረኛል። በሽሮ ምጥን ያው አንታማም።
ዘገዬሁ መስል ሰለ ሰላምታው? ግን እንዴት ሰነበቱ ጸሐፊ አቶ ሰርጸ ደስታ? አስተያየተዎን ደስ ብሎኝ ነው ያነበብኩት። 

የዛሬ አይደለም አንባቢነቴ፤ የእርስዎ ጹሑፍ ታዳሚነቴ የጻፉትን ቢጽፉ በብራናዎት ላይ ለሙግት ትውር ብዬ አላውቅም። ያ ማለት በሁሉ ነገር ተስማምቼ አይደለም። የሚስማማኝን፤ የማይስማማኝን አነባለሁኝ። የማነበው እርስዎም የሐገሬ ኢትዮጵያ ነገር ግድ ስለሚለዎት ነው የሚጽፉት እንጂ እንደሌላው ቁጭ ማለት ይችላሉ። 

መጻፍ ወገብ ቁርጥ ነው የሚያደርገው። በዚህ ስሌት ስንሄድ እማነበው በአክብሮት ነው ማለት ነው። የእኔ ብዬ - ከውስጤ።

ከእርሶዎ ሃሳብ ተነስቼ የምንነሰትባቸውን የመተንፈሻ አውዶችን፤ የሚያስከትሉትን ቀውስ ከልብ አለማስገባትን በተያያዥነት አቀርባለሁኝ። አሁንም አቅም ለሚሆኑኝ ቅኖች ነው። የሚጥመን ለእኛ የለም እና። ሁሉም ቀናውንም አክለን እንደ ወልጋዳ ነው የምናስተናግደው። አማራ መሬት ላይ እንደ ኦህዲድ በቡድን ደረጃ ተስፋ የሚጣልበት አቅም ቢፈጠር ኖሮ መሬት ቀውጢ ይሆን ነበር። 

ከዚህም በላይ … በላይ … አንድ ብሄራዊ ጀግና ኮ/ ደመቀ ዘውዱን ለማንሳት ራሳቸውን የተላለፉ አማራዎች ሳይቀሩ ተስኗቸዋል። የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የዶር አንባቸው ፍልሚያም የሪሚጦ ያህል ክብር አልተሰጠውም። 

ምስጋናውም እንዲሁም በግለት ነው የተወራረደው። ደወሉ አቅጣጫው የሚነግረን የተደሞ እድምታ አለው። „ልብ ያለው ሸብ“ ይላሉ ጎንደሬዎች። ልብ ብለነዋል እንደ ማለት …  ከእንግዲህ ፈሶ የሚቀር የራሳችን አቅም የለም። ክብር ለሚገባቸው የአማራ አንበሶችም ክብር እንሰጣለን! ክብራቸውን መሬት ላይ የአቧራ ራት፤ የሴራው ቦንዳ የአቶ በረከት ቅበር ትራፊ ቀራሚ ሲያደርጉት ደግሞ እንጸዬፋቸዋለን።
  • ·        ስለምን እኔ የጹሁፌ አቅጣጫ ወጣ ያለ ሆነ?



የሚገርመዎት እኔ እግር ኳስ እጅግ እውዳለሁ፤ ግን ሁልጊዜ ለተሸናፊ ወገን ነው እማዳላው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደትም እንዲሁ ነው። ብዙ ሰው በአሉታዊ የተነሳበት የነፃነት ትግል ካለ የእኔ ብዬ እሟገትለታለሁኝ። የሚችለውን ካላደረገው፤ የሚችለውን የሚያደርገው የተሻለና የበለጠ ስለሆነ። ሃሳቡን ደግፌ አንድ ጊዜ ከገባሁበት በኋዋላ ግን ሃሳቤ በራሱ ጊዜ የደገፍኩት ባለሃሳብ ውድቅ እስኪያደርገው ድረስ እተጋለሁኝ። ስለምን? በሌላ ወገን ያለው ተቀናቃኝ ሃሳብ የእኔን የብዕር ማህበርተኛ እንዳይወስደብኝ አቅሙን መሰረት ማስያዝ ስላለብኝ። ደክሜ ነው እምሰራው። 

ሙግት ማገናዘቢያ እያቀረቡ በመትጋት ስለሆነ እጅግ ከባዱ ሃላፊነትን ነው እኔ የመረጥኩት። ስለዚህ ብችል የተቀናቃኝ ሃሳብ ማህበርተኛን ወደ እኔ የብዕር ማህበርተኛነት ማምጣት፤ በስተቀር ግን እኔ የሰበሰብኳቸው መንፈሶች በዛው ሃሳብ ውስጥ እንዲቆዩ፤ እንዲጸኑ ማድረግ ፈቅጄና ወድጄ የገባሁበት የብዕሬ አቅጣጫ ነው። 

ደግፌ የተሟገትኩልት ሃሳብ በኪዳኑን መሰረት ካላስኬደው አልምረውም። ተፋልሜለታለሁ እና ብራና ላይ። እርግጥ መከራው ብዙ ነው። ግን መከራ እና ፈተና፤ መገለልን ጨምሮ እጅግ መልካም ነገር ነው። ያለው ቀሪ ጊዜ ሁሉ ከፈጣሪ ጋር ይሆናል። ሰው እኮ ካልከፋው አቤት! አይልም። ይህ ደግሞ በራሱ አቅም እዬፈጠረ ሙቀት እዬሰጠ መንገዴን ይጠርግልኛል።

የጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራሜ ግን ከዚህ የተለዬ ነበር። መጸሐፍቶቼም እንዲሁ። በቀጥታ ከጦርነት ቀጠና ፈቅጄ አልገባም። የልጆች „ሐገር ማለት ምን ማለት ነው? ፍቅራዊነት ማለትስ?“ የአዋቂዎች በነፃነት አርበኞቼ ተጋድሎ ተኮር ነው ሥሰራ የነበረው። ኢትዮጵያ እስር ቤት የሚገኙ ወገኖቼ ለእኔ ነፃነት ሲሉ በፈርዖኖች እጅ እንደ ወደቁ አውቃለሁኝ። ጀግኖቼ ናቸው። 

በሌላ በኩልም ይመቸናል ባሉበት የሚታገሉትም ቢሆኑ የራሳቸው አስተዋጾ ስላላቸው ብዙም ሳልገፋቸው የእኔ ብዬ አቅም አዋጣለሁኝ። የጸጋዬ ራዲዮ እንደ ብራናው አይደለም ጸጥታ የሰፈነበት ነው። ለዘብ፤ ለስለስ ያለ ነው። ግን ብዙ ደቂቃ በሙዚቃ አይጠፋም። ስለነበር። ቢበዛ በጠቅላላው ከ8 – 10 ደቂቃ ነው።

 የመዝናኛ ሳይሆን የነጻነት ራህብ የትውልድ ህሊና ቀረጻ ተልዕኮው ነበረው። አጫጭር ግን በርከት ያሉ ቁም ነገሮች ይዳሰሱበት ነበር። ሙዚቃው አራሱ ተፈጥሯዊ ተኮር ስለሆነ እንደ ሜዲቴሽን አይነት ነው። ያው መከራው በረድ ሲል ልቀጥለው እችል ይሆናል። ስቴዲዮ የሚናፈቀኝ አንዱ የህይወቴ እርከን ስለሆነ። አሁን ለጊዜው የተለያዩ ነገሮች ነው የሚሠራበት። መከራና ችግር ሲመጣ ፊት ለፊት ሄጄ ግንባሬን አላጋጨውም። ዞር እላለሁኝ። ወጀቡ ሲያልፍ ደግሞ እጀምረዋለሁኝ።
  • ·        ምን ብዬ? ህም!


አሁን ባለፈው ጊዜ እኔ ለእርስዎ ስጽፍ እርስዎ ይቀበሉታል ብዬ አይደለም። እርስዎ የራስወት አቋም አለዎት፤ ነገር ግን የእኔ ሃሳብ ማህበርተኛ የሆኑ መንፈሶች በእርስዎ ጹሑፍ መንፈስ በጥርጣሬ ውስጥ ሆነው እንዳይሰረቁብኝ በማለት ነው። በሌላ በኩል እኔ እንደርስዎ እከሌ ስለጻፈው፤ እከሌ ስላደነቀው ወይንም እከሌ ስለደገፈው፤ ወይንም እከሌ ስላዋደቀው አልልም። ሁሉንም አዳማጥለሁኝ፤ ግን ልቦናዬ ውስጥ ያለውን ነው እምቀበለው። በለማ የጥናት እና የምርምር ተቋም በኦህዲድ ተኮር ጹሑፍ ላይ፤ የጸሐፊ ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ እና የእኔ መንፈስ ከአንድ ማህጸን የወጣ እስኪመስል ድርስ ተመሳሳይ ነው። 

እኔ አንድ ነገር ብሆን እንኳን እሳቸው አሉ ብዬ አስባለሁኝ። ልቤን ጣል የማደርገበት ጸሐፊ ቢኖሩ እሳቸው ናቸው። ቅን ናቸው። ነገሮችን በአውንታዊነት ነው የሚያዩት። ግልጽም ናቸው። ውጤቱን፤ ሂደቱን፤ ጥረቱን እውቅና መስጠታቸው በራሱ ውሳጣቸው ውስጤ እንዲሆን አድርጎታል። ዕንባን የማድመጥ ክህሎት አለበት። እንዲህ ዓይነት የሰከኑ ሰዎች ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል፤ ጀምላዊ የሃሳብ ቤተኛ ያልሆኑ።

የለማ መንፈስ ተወራሽ መሆን ያለበት የታሪክ ዐምድ፤ የዕውነት ቋት ነው። ቅርስ ነው፤ ትውፊት። አምልኮተ - ማዖዚም፤ ማርክዚዝም፤ ሌኒዝዝም፤ ስታሊኒዝም፤ አምልኮተ ማንፌስቶ ተሸንፎ „ኢትዮጵያኒዝም“ በውስጡ አቅም የበቀለበት አዲስ ዘመን ላይ ነን። ፈተናው የቀራንዮ የጎለጎታ ያህል ቢሆንም። የለማ አብይ መንገድ ሰዋዊነት፤ ተፈጥሮዊነት፤ ሞራላዊነት ነው። 

ይህ ደግሞ ለ21ኛው ምዕተ ዓመት የተመቸ የሥርዬት ቅዬሳ ነው። አሁን ተዋሾች አይደለንም። ዛሬ በውስጣችን አቅማችን እያደማጥን ነው። ለዚህ ነው እኔ የኤርትራ ሞግዚትነት አብቅቶለታል የምለው። ኢትዮጵውያን በራሳቸው አቅም ውስጥ አዲስ „እኛዊነትን ያዳመጠ ኢትዮጵያዊነትን እናድን“ ንድፈ ሃሳብ ቀምረው ደፍረው ጀመረውታል። 

„እኛዊነት“ ለመንፈስ ፍሬ ሲበቃ በዕድሜ ያዬሁትም አሁን ነው። በአለን የበቃ አቅም ውስጥ የበቀለ አቅም ለማግስትም በጀርኖዱ ነው። „ጽዮናዊነት“ በራሱ ስለራሱ ሆኖ ለድል የበቃው አቅሙን መሰብሰብ የሚያስችለው መንፈስ የኛዊነትን ሞገዳዊ ፍልስፍና መፍጠር በመቻሉ ነው። 

ምርኮኛ ትውልድ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ ከሥሩ ተጠንቷል። እናት ቤት ውስጥ ያላት ሚና ላይ ሊሠራበት እንደሚገባ ዶር አብይ አህመድ ሥሩን መርምረው፤ በሰለጠኑ ሐገሮች ያሉትን ብርቅዬ ኢትዮጵያ ልጆች አይተው ተስፋን ለማግኘት ተስፋ በነፃነት የሚያስብባት አዲስ ኢትዮ ዓለም መፍጠር ያስፈልጋል ነው የሚሉት። 

በአቶ ለማ መገርሳ በኩልም ቤት ውስጥ የሞራል ት/ቤት የመክፈት ሃላፊነት ወላጆች መክፈት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በግራና በቀኝ ባይወጠሩ ሃሳባቸው ጥልቅ ነው። ይህ እንግዲህ የኛዊነት ፍልስፍና በግብር ይወጣ በእለት ደራሽ ግጥምጥም የመጣ አይደለም። የሁለቱ ደም ተቀላቅሎ ሳይሆን ተዋህዶ የፈጠረው ህብር ነው የለማ መንፈስ። 

በሳይንሱ ሁለት የሃይድሮጂን ሞለኪዩልስ ከአንድ የኦክስጂን ሞለኪዩልስ ጋር ሲዋህድ ውሃ ይሰጠናል። የሁለቱ ውህደት ውሃን ይፈጥራል። ቀለሙም ውሃማ ነው። የለማ መንፈስ ይሄ ነው። ሥሙ ተፈጥሯዊ ውሃ፤ ቀለሙ ንጹህ ውሃማ፤ ሂደቱ ውስጥን በውስጥ ያዋህደ መንገድ መሪ።    
  • ·        ድካም ማለት ምንም የሆነበት የነፃነት ጥማት፤


ማደራጀት ለዛውም የመንፈስ ለውጤት በቅቶ፤ የሥነ - ልቦና አቅም መፍጠር የአንድ ጀንበር ተግባር አይደለም። ዋጋ ያልተሰጣቸው የኦህዴድ ወጣት መሪዎች ድካማቸው ምን ያህል ሰዓት እና ቀን እንደወሰደባቸው፤ እርምጃዎችን በወሰዱ ቁጥር በሚነቃንቀው የማይደፈር የዘረኝነት ሴል ምክንያት ምን ያህል በስለላ መረብ እንደተከበቡ እያዳመጥን ነው። ማደራጀት ህይወቴ ነው፤ የጋሜና የቁንጮ መነሻዬ የወጣትነት ህሊናዬ ነው።

 ስለሆነም አቶ ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ ልባዊነት የልቤን ያደረሰ የተጋድሎ ምዕራፍ ነው። ጥበቃ ታክሎበታል። አቅም የሚያዋጣው ሁሉ እንዲያዋጣ በትጋት እዬሠራሁበት ነው። 

ብዙ መንፈሶችን በጭንቀቴ በሃዘኔ አሰቃይቻቸዋለሁኝ፤ አሁን ደግሞ በመፍትሄው መንገድ ላይ አቤት! ማለት ግድ ይላል። ለሰማዩም ለምድሩም። እነኝህ እንቁዎች በማይቻል ሁኔታ ተችሎ ያዬሁት የብቃት መንፈስ አምጠው ወልደውልኛል። ለእኔ የምስራች ቀኔ ነው። ለዚህም ነው አሳሩ የበረከተው። 

ሁሉ ይታጣና ወደ ማይቀረው ረግረግ እንዲኬድ ነው ዘመቻው ሁሉ … ለአንድ የቃጠሎ ወንበር ይህን ያህል ውርክብ … ዕጣው እኮ የአናንያ፤ የአዛርያ፤ የሚሲያል ነው። ወደ ፋመው እሳት መወርወርና እሳቱን ተሻግረህ ተስፋን አሳዬን ነው። ለዚህም ጦር ተሰበቀበት።

በዚህ ውስጥ ታማኝነታቸውን ያጸኑት እነ ዬገዱአንቤንጉሱም ተጋድሎ ፈጽመውበታል። ይህ ቅንብር እና ጥበብ ስዋሰዋዊ ጥልፉ የእዬር ነው፤ በሰው እጅ ያልተሸመነ። ይህን በማቃለል የሚተጋው ነፍስ ማደራጀት እና ጥበቡ፤ ተልዕኮውና ወጤቱ፤ ውጤቱና ግቡ ጋር የተላለፈ ነው። ባለበት ቁሞ የሚጠበቅ ተስፈኛ ነው። በሌላ በኩል እግዚአብሄር አንዲህ ዓይነት አረጋጊ መንፈስ ሊፈጥር እንደሚችል የዕምነት ማነስም ነው - ለእኔ። ብክነት ትጥቃችን ስለሆነ እንጂ ዘመኑን ያደመጡ መንፈሶች ከዚህም ቀደም ተፈጥረዋል። ከእኛ በቀደመውም ዘመን ቢሆን። 

የሆነ ሆኖ ድርጅት ቢሮውም፤ መንፈሱም ሞባይል ላይ አይደለም አቅሉ የሚሰክነው። መሬት ላይ መንፈስን ከመንፈስ በእውነት እና በጸና አቋም እና ጥበባዊ አያያዝ በተከታታይነት የመገንባት አቅም፤ ከሚመሩት ከሚያደራጁት ማህበረሰብ ተሽሎ መገኘትን የሚጠይቅ፤ በጥረት ክህሎት ከዳበረ ህሊና የሚገኝ እንጂ በማይክራፎን ገብያ የሚታፈስ አይደለም። ንድፈ ሃሳብን መማር ይቻላል። ግን ንድፈ ሃሳቡን የምትዘራበት፤ የምታለማበት ማሳ ከሌለህ የጋን መብራት ነው። 

ይህም ብቻ አይደለም ያገኘኸውን መንፈሳዊ ሃብት የአማራር እና የአስተዳደር ጸጋው ከሌለም ሲሳዩ የሌላ ይሆናል። የማደራጀት መንፈስ ሰው ለሰው እንጂ በስልክ ሽቦ አይወራረስም። ኑሮውን ኖረህ ነው ጣዕሙ የሚገኘው። ኑሮውን አድምጠህ በሙያ ገብ ዓይን አይተህ ነው ጠረኑ የሚጠጋ። እሳቱንም አብረህ ተገርፈህ - ተቀቅለህ ነው የእኛ የምትባለው። 

ይህ ሲሆን ችግሩን ሲመስጥህ መፍትሄው ይበራልሃል። ይህ የለማ አብይ መንፈስ ለእኔ ከሰማይ የወረደ መና ነው። ደክሜበታለሁኝ። የደከምኩበት ነገር እስከመጨረሻው ድረስ እታገልለታለሁኝ። እነኝህ ዕንቁዎች ሃብትነታቸው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የፓን አፍሪካኒዝም የምህረት መንገድም ናቸው። ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት በስሜት ሳይሆን በበሰለ እና በሰከነ ጥበብ የህሊና አቅም መመከት የሚችሉ የጭንቅላት ባለ አዱኛ ናቸው። የማናፍርባቸው! አንገት የማንደፋባቸው!
  • ·        ተስፋዬ እና ተስፋው፤ 


ኦህዲድ እንደ ድርጅት አቅሙ ሙሉ ነው ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ አቅጣጫ የመምራት ችሎታ አለው ብዬ በጽኑ አምናለሁኝ። ኦህዲድ ዕድሉን ቢያገኝ እንኳን ቡቃያው አስብሎ የተስፋ ማህደር ይሆን ዘንድ እተጋለሁኝ። ፊርማ አለበት። ቢሆን፤ ቢሳካ፤ ጎደለ የምለውን፤ ክፍተት አለበት የምለውን አስተውሳቸዋለሁኝ። 

እኔ ቢሆንልኝ ብዬ የምመኘውን፤ የማስበውን፤ ዓለምዓቀፍ ማህበረሰቡን ያስጨነቁኩበት፤ ያስጠበብኩበት፤ ጓደኞቼን ሰላማቸውን የተሻማሁበት፤ ሀኪሞቼን ሳይቀር ያሳሰባቸው ነገር ስለሆነ ትንፋሹ እክል እንዳይገጥመው በቅንነት ሎሌው አና አገልጋዩ እሆንለታለሁኝ። ገረዱ። በሁሉም አቅጣጫ ነው ትጋቴ። የሚገድበኝ ሆነ የሚያስረኝ ነገር የለም። 

እኔ እኮ የማኒፌስቶ ማህበርተኛ አይደለሁኝም። ወደፊትም አልሆንም! ብቻ ሞት እና ጭንቀት ከኢትዮጵያ እናቶች ይወገድልኝ። የህዝብን ድምጽ፤ መከራ፤ ጥያቄ የሚሰማ እረኛ ይገኝልኝ። „ሰው“ መሆንህ ብቻ ይበቃኛል የሚል ሙሴ አምላክ ይፍጠርልኝ። በነገራችን ላይ ቅኖችን አገኛቸዋለሁኝ፤ ስለሰው ልጅ የመሰረዝ ዘመን የሚጨንቃቸውን አሰስባቸዋለሁኝ - በትጋት። የቅን ሃሳብ ማህበረተኞች አሉኝ። በሌላም ሁኔታ ማደመጥን ለተቀበሉ መንፈሶች ሁሉ በትጋት ቀን እና ሌት ነው የምሰራው። 

ምክንያቱም እኔ ለነጻነት ትግል ሠረገላ ይቅርብለት የማልል ከመሆኔም በላይ ወስጤ የሚነድበት የኢትዮጵያ እናቶች ወህ የሚሉበት ዘመን ናፍቆተኛ ነኝ። ረዘመ የመከራ ጊዜው። ስልቹነት ከመጣ ሁሉም ልምድ ያለው ሁሉ ትቶ ሊቀመጥ ይችላል። በዛ ላይ አይዋ ሞትም አለ …

በር ሲከፈት የነፃነት ተስፋዬ በወርቅ ይዘምዘምልኝ እንደሚሉት አይደለሁኝም። በማረተ በርም ቢሆን ፆታ ሳይለይ ህጻናት፤ አንዲት እናት፤ አንዲት ሴት ልጅ፤ አንዲት ሚስት፤ አንዲት አክስት፤ አንዲት ሴት ጓደኛ፤ አንዲት እጮኛ ትንፋሽ ያግኙ። ይሄ ብቻ አይለም ዛሬ ሲያልፍ ቀጣዩ ባለተራ ተጠቂ እንዲኖር አልሻም። 

አቁቶ የሚጠብቅ የቂም ውርርስ እንዳለ ልብ እላለሁኝ። አንድ ቦታ ላይ ይህ የበቀል ሱቅ በደረቴ አዟሪት መቆም አለበት! ለዚህ ደግሞ ግራና ቀኝ በመጣደፍ ላይ ያሉት የኦህዲድ ቲም፤ አቶ ለማ መግርሳ እና ዶር. አብይ አህመድ እንኳንስ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ የአዲስ ምዕራፍ ከፋችነት በሙሉ ልቅና ተነሳስተው ቀርቶ፤ ዝቅ ባለም ደረጃ ቢሆን ሂደቱ መከታተል መደበኛ ሥራዬ ስለሆነ እቀጥላለሁኝ። 

ፊርማዬ የት ቦታ፤ በዬትኛውም ሁኔታ አለ። ስለ እነሱ ምስክርነት ስሰጥ በፍጹም እርግጠኝነት እና በታማኝነት ነው። እንደማያሳፍሩኝ ብቻ ሳይሆን እንደሚያኮሩኝ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ - ዕዱሉን ካገኙ። ተናግሬማለሁኝ። ሜሮን ነው ለእኔ ኮቴያቸው ሁሉ። 

ኢትዮጵያኒዝም በውስጡ ያቄመ ሁሉ አንድ ስንዝር በእድገት መንፈስ አይራመድም። ሃሳቡን ሊያስበው ይችላል በመራመድ፤ ግን በእርቃን ሊሆን ይችላል፤ በመንፈስ አቅም ቤተኞቹ የጀማሪ ያህል ናቸው። መሰብሰብ አይችሉም። በዬፌርማታው ክፍተቱ ይንጠባጠባል … ከዚህ ቅዱስ መንፈስ መውጣት መቀነስን እንጂ መጨመር ክፍሉ አይሆንም።  

የማከብረዎት ጸሐፊ አቶ ሰርጸ ተዚህ ላይ አንድ ነገር ትዝ አለኝ ሁልጊዜ ፕ / ኢሳያስ አፈወርቂን አያቸዋለሁኝ፤ የሐገር መሪ ናቸው። ድሎቱን ባይፈልጉትም ማለቴ ስርቆትን ቢጸዬፉትም፤ ከማንም በተሻለ ደልቷቸው መኖር ያስችላቸዋል - ቦታው። ቦታው የሰጣቸው ክብር ግን ግርማ ሞገስ አላጎናጸፋቸውም። ወዝ የለውም። መነፈሳቸው ብክነት ላይ ነው። ጠረኑ አሁንም ድንግዝግዝ ያለ ነው። 

በቃ የኤርትራ መሪ መሆናቸው ብቻ እንጂ የአንድ ጦማሪ ያህል እንኳን የመንፈስ ሞገስ የላቸውም ወይንም የውስጣቸውን ደስታ ልናዬው አልቻልነም። ሲስቁ አይቻቸው አላውቅም። ፎቷቸውን እትም አድርገው ቢመለከቱት ሁልጊዜ ድንኳን ውስጥ እንደ ተቀመጡ ነው። ያጡት ነገር አለ። የነጠሉት አዳኝ መንፈስ። የመን እንደዛ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፋ ሰጥታ ይደላት መስሏት ነበር። አልሆነም። በእጥፍ ዕዳውን አወራርዳዋለች። ሱማሌም በእኛ ዕድሜ ያዬነው ነው። የተበተነ መንፈሱን ታቅፎ ነው ያለው። 

ደቡብ ሱዳንም ህጻናትን እዬዘረፈ አሁንም ጥጉ ኢትዮጵያ ናት። ሄሮድሰ መለስ ዜናዊም ሆኑም የቤተክርስትያናት ጭንቅላት በሰሞኒት የሆነው ሁሉ የሰማይ መብረቅ ነበር። ኢትዮጵያዊነት መንፈሱ የማይደፈር የጸጋ ስጦታ ነው። በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ያሉ ንጥረ- ነገሮች ሰው ሰራሽ አይደሉም። መስህቡ ማግኔት አለው። ጥልቀቱ ዲካ የለውም። 

በፍቅሩ ውስጥ ያለው ጥግ ጥንግ ድርብ ነው። ሰው ኢትዮጵያዊነትን መንፈስ ሲጎናጸፍ ሙቀቱ ከተለመደው ውጪ ነው። ይህን ደግሞ በአቶ ለማ መግርሳ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ብቻ ማዬት ይቻላል። ዘመን የሰጣቸው ናቸው አቶ ለማ መገርሳ። ትልቅ ጆሮ ከትልቅ ልቦና ከማይገፋ የህሊና ብጡልነት ጋር የሰጣቸው ባለመክሊት ናቸው። ወደ እኛ መጡ፤ ልባችን ከፍተን ፍቅርን ጎዝጉዘን መንፈሳችን ሳንሰስት ሸለምናቸው። ሚስጢሩ ግን ኢትዮጰያዊነት ብቻ ነው።  

የለማ መንፈስ ብቻ ሳይሆን ለማ እራሱ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ህይወት የምርምር ማዕከል ነው። አዬን እኮ ያ ምስኪን ህዝብ ደሙን የገበረበት ሰማያዊ ፓርቲ ሁለት ሊቀመናብር አሉት - ዛሬ። ሟቾች ቃል ኪዳናቸውን ሰጥተዋል። 

ግን አደራ ተብልቶ አዲስ ፓርቲ ደግሞ መመሥረቱን አዳምጠናል። ለሌላ ግብር የጎጃም እናት ማምረቻዋን ታሰናዳ - የፈረደባት። ለማ የጥናት እና የምርምር ማዕከል ግን እንዲህ አይደለም። ውስጡ ምን እንዳለው? ምን እንደሚችል? ምን እንደሚያስፈልገው? ዘመን ምን አደራ እንደጣለበት ከፈጣሪው የተሰጠው ውሃ ያልነካው ተልዕኮ አለው። ውሃ ልኩ በ እንቁላል ውሃ የተገነባ ነው። ይህን መንፈሱ ያውቃል። ኢትዮጵያ የጎደለባትን የአቅም ስስነት የእኔ ብሎታል፤ አስጠግቶታል። 

ንግሥናውን ትቶ ገዳም የገባው ቅዱስ ላሊበላ መንፈሱ ነው። እያለው፤ እዬቻለ ሙሉና ብቁ ስለሆነ በራሱ ውስጥ ራሱን ሆኖ ለመኖር መሆንን በተግባር የተረጎመ የትውልድ ታላቅ ተቋም ነው የለማ የምርምር ተቋም - ፈርጥ። በዚህ ዘመን ከግል ኢጎ የተፋታ ድንቅ ፍጡር! በአቶ ለማ መገርሳ ውስጥ ያሉ ረቂቅ ሊታዩን ያልቻሉ ልቅናቸው እንኳንስ ለዛሬ፤ ለዘመናት ኢትዮጵያን ከመከራ ባርነት ለዘለዓለም የሚያወጣት የልብ አንባር ነው። 

ስለዚህም ሞት ቢያስፈልግም እሞትለታለሁኝ - እኔ ለማውያን ነኝ! ትግሉን ቆርጬ ገብቸበታለሁኝ። ድምጼንም አቅሜም እስከቻለው ድረስ እስከ ጥግ ድረስ ሄጄ የሚሆነውን አደርጋለሁ። አድርጌያለሁም። ትናንትም ያኖረኝ የሎሬቱ ታቦት ነው፤ ወደፊትም የሚኖረኝ የሎሬቱ መንፈስ ነው። ከሎሬቱ ጋር የከተመ የውስጥ ብርሃኑ ብቻ ይበቃል።

የማከብረዎት ጸሐፊ አቶ ሰርጸ ስለ አንስታይ ያነሳሁት እርሰዎን አልነበረም። „ሂሳቡ ቀላል ነው“ ብለው እንዳልጻፉ እርስዎም ያውቃሉ። ቃሉም እርዕሱም የእርስዎ ንብረት አይደለም። ስለ ፍልስፍና ካነሱ ዘንድ አንዲት የባቄላ ፍሬ ከ10 በላይ ፈላስፋ ሊኖራት ይችላል - የጥናት መስኩ ክትር የለውም። 

ስለ ሥሯ፤ ስለ ቅጠሏ፤ ስለ ፍሪያዋ አንቀልባ፤ ስለ ቅርንጫፏ አበቃቀል፤ ስለምትበቅልበት የአዬር ሁኔታ፤ የመሬቱ ንጥረ ነገር፤ ከጽንስት እስከ ውልደት እስካለው የቆይታ ጊዜ፤ ስለተቀናቃኙ አረም፤ ተምች፤ ስለ ቆባው፤ ስለ አዲሱ ዕንቡጥ፤ ስለ ቁመቷ፤ ስለስፋቷ፤ ስለ ዕንቡጡ ወደ ፍሬ የሽግግር ጊዜ፤ ስለ ሙሉ የእድግና ብቃታዊ፤ ማዳቀልም ሲኖርም የተለዬ የጥናት ቤት ነው። 

ጊዜ ስለሆነም የለማ ኢትዮጵያን ያጠናበት፤ የተጠበበት፤ ከውሳኔ የደረሰበት፤ ዲዛይን ያደረገበት መንገዱ በቀላል 1+1= ሁለት አይደለም ነው ፍሬ ነገሩ። ፈተናውንም ያወቀዋል፤ የልቤ ብሎ ፈቅዶ ግማዱን ተሸክሞታል። የቀራንዮ አርበኛ ነው። 

ከተኖረበት ቀርቶ ወደፊት ከሚታሰበውም በላይ እሩቅ ህሊና ነው … ኢትዮጵያዊነትን ተመራምሮ መድረስ አይደለም የምርምር የቤት ሥራ እንዳለብን እራሱ አናውቀውም፤ ብናውቀውም አንቀበለውም፤ ብንቀበለውም ዕውቅና አንሰጠውም። 

ስለምን? እኛ የእኛዊነት ስላልሆን። በውስጣችን ያለው „እኛዊነት“ ሲሶ፤ እርቦ፤ እኩሌታ፤ ወይንም የተፋቀ ነው። ቢያንስ ሰላሙን ሰጥተነው እንቅፋት መሆናችን ቢቀር አፍሪካውያን፤ የዓለም ጥቁር ህዝብ ተስፋቸውን ጥግ እንዳያገኝ መቀናቀኑን፤ መፎካከሩን፤ ማጥላላቱን፤ ብንታገስልት እንኳን ምንኛ ዕድለኛ በሆነ ነበር፤ የሚስጢራት ዓምደ ከድንቅነሽ - ጊዮን ዲካውን መለካት አይቻልም ኢትዮጵያዊነት። 

ከኑብያ የደካ ማዳጋስከር ይዞ ጁቢቲ ሲታከል መጠነ ሰፊ ነው። በ አፍሪካ ጸሐይ የማትጠልቅባት መንፈስ ያለው ዲታ ባለ አዱኛ ነው። ሲሳዩ ረቂቅ፤ ረቂቅነቱ የመንፈስ፤ መንፈሱ ተፈሪ! በግብር ይውጣ ልቡን ማግኘት ፈጽሞ አይቻልም።   
  • ·        እኛ ከምን ነን? ማለቂያው የማይታወቅ የፍላጎት ጉድጓድ ….


ይህን የማከብረው እና አዘውትሬ የምከታተለው BBN የአቶ ለማ መገርሳ የኢትዮጵንያዚም የምርመር ማዕከል ልቅና ሲያገኝ የሰራው ነው። ወደ 200, 000 በላይ አድማጭ ታድሞበታል። ምን ያህል የተሰበሰበ መንፈስን በፋስ ያለርህራሄ እንደበተነው መመልከት ይቻላል። አቀራረቡ ስልታዊ እና በረቂቅ ሴራ የተቀለመ ነበር። በቀጥታ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ያለ ጠመንጃ የተዋጋ። 

አቀራረቡ አሁን ከተፈታ ደግሞ የበለጠ ቀልቤን እዬሳበው የመጣው ጸሐፊ ኡስታዝ አህመዲን ጀቢል የጤና ጉዳይ እረመጥ በሆነበት ወቅት ከእሱ ፎቶ ምስል ጋር፤ እንዲሁም መንፈሳችን አብሮ እንዲታሰር ከፈቀድንላቸው „የድምጻችን ይሰማ“ ቤተኞች ጋር ነበር የተቀነባበረ ነበር። አቤት! ያንት ያለህ የእኛ ጌታ ከፍላጎታችን ጋር ምን ያህል እሩቅ ነን - እኛ? ያሰፈታቸው የውሳኔ አቅም እኮ የለማአብይ ገዱአንቤ የመንፈስ ተጋድሎ ነው፤ እንጂ ድምጻችን ይሰማ ተጋድሎው አሁን የአደባባይ አይደለም።

https://www.youtube.com/watch?v=FqzoTUA4V8E  „News Analysis: Hidden Truth About Lemma Megersaበዚህም ጸንቶ BBN አልቀጠለም። ያን ነፍሰኢትዮጵያዊነትን ሱስ ነውን“ ያስገኘውን የመንፈስ ተረጋጊ እርጋታ ከታገለ በኋዋላ ደግሞ አሁን የኦህዲድ ማዕከላዊ ኮሜት የስልትና የስትራቴጂ ጥበባዊ ለውጥ ሲያደርግ ደግሞ ዶር አብይ አህመድ ፊት ለፊት ሲያመጣ ሌላ ጓዝ ይዞ መጣ። ጊዜም ታሪክም እንዲመረምረው መተዉ ይሻላል። 

„BBN Presents Jawar Mohammed | Lemma Megersa | Oromo | Amhara | EPRDF“ መጨረሻ የሌለው የሰው መንፈስ እረፍትን ቀማኛው ጦሮ በየትኛው የፍላጎታችን አንቴና ይረካ እንደሆን አይታወቅም። ህም! እርካታ አልኩኝ? ይሄ ለባለ ዕድሎች የአቅም ጥበቃ ህሊናዊ ወታደሮች ይሁን ለታደሉት ሐገሮች፤ ተሳስቼ ነው ይቅርታ፤ እንዲያው ብጣቂ ትንፋሽ የሚገኝበት። 


እኛ ባለን መመካት የሚሳነን ገደቢሶች ነን። ኢትዮጵያዊነት እንግዲህ እንዲህ ነው። ወጀቡም፤ ጦሮውም፤ ሞገዱም፤ ነበልባሉም፤ አሳተ ጎመራውም እንደዬሁኔታው የሚፈራረቁበት። ምስኪንዬ።

·        ቀጠናው።

ኦህዲድ በጦር ቀጠና ውስጥ ስለመሆኑ ሊገባን ቀርቶ 43 ዓመት የኖረው ችግር ሁሉ እፍ ብሎ በአንድ አፍታ እንዲጠፋ ውጥር አድርገን ፋታ ነሳናቸው። በሥራቸው ላይ እየደረደርን ሰንገን ያዝናቸው። አዋከብናቸው። 

የኦነግ መንፈስ በራሱ የፈጠረው እና በደረግ ጊዜ ይሁን በወያኔ ሃርነት ትግራይ ሳቢያ ሆኖ የቆሰለው ሁሉ፤ በዚህ ሂደት የዘረ - አማራ፤ ኮንሶ ጥፋት እና ንቅለት ታክሎ መራር ዘመን ነው። የአሁኑ የኢትጵያ ሱማሌ እና የኦሮሞ ጉዳይም ትኩስ ቁስል ነው። 

ይህ ሁሉ ሆኖ የዚህ ሁሉ ችግር መፍትሄ አምንጪ የተስፋ ጨረራዊ ጮሪት ጀማሪ መሆናቸው ሊያስመሰግናቸው ሲገባ እንዲያውም የ43 ዓመት የፈተና ግግር አምጪና አመንጪ ሁነው ተወገዙ። በዬተራ ተወረፉ። አንዱ ቁማር ሲላቸው፤ ሌላው ከዱን ወዘተ … ፈጣሪዎቹ በነፍሳቸው ተቀምጠው።

ለመሆኑ ከ43 ዓመት በፊት አንዚህ ወጣቶች ተወልደው ነበርን? ቢወለዱስ ለአቅመ አዳም ደርሰው በድርጊቱ ተሳታፊ ነበሩን? ህሊና የሚባል ነገር እኮ አለ። አንድ ጊዜ ይመስክሩ ፍ/ቤት ሂደው በማለት ወዮ! አቦ በቀለ ገርባ አንድ ነገር ይሁን እና እሳቱ ይነዳል የሚል ዛቻ ነበር። እነሱ ከዛ ሲኦል ድርጅት ወያኔ ሃርነት ትግራይ ጭንቅ ጋር በደህነንት ተከበው ልጆቻቸው ት/ ቤት አቁመው 18 ቀን በአራት ኪሎ የቤተመንግሥት የአድዋው ጦርነት ላይ ይፋለማሉ፤ እኛ ከዚህ መንፈስ የሚሰነጥቅ ፋስ ይዘን ሃሳብን እንተረትራለን። 

ኦነግ እኮ ሠራዊቱን ይዞ ገብቶ ነበር። ሞጥሮ ይዞ ሞትን ሞቶ፤ መታሰርም ካለ ተቀብሎ ድል ማድረግ ሲገባ የሺህ እናት ዕንባ የፈሰሰበትን ያን ሁሉ መስዋዕትነት ጥሎ ወጣ። ታሪኩን በአፍጢሙ እራሱ ደፋው። ተገፍቶ ወዘተ … 

ምንጥርሶ ቅብጥርሶ አይገባኝም። ያ ከሆነ ድጋሚ ስለምን አገር ቤት ገባ? ተገፍቶ ነውም ቢባል እንኳን? አሁንስ? ኦህዴድ ተወዶለት ቀይ ምንጣፍ ተነጥፎለት ነውን? „ከበሮ በሰው እጅ ሲያዩሽ“ ይህን ያህል ጉሩቦ ለጉሮቦ ተናንቆ እዬቀለጠ ጧፍ ለመሆን የወሰነው በስቃይ ወስጥ ሞትን ፈቅዶ ነው? ሞትን እያዩት እዬመጣባቸው ነው ይህን ሁሉ ተጋድሎ ያደረጉት።
 
የኦንጋውያን መሥራቾች የዘሩት ዘር፤ መብቀሉን፤ ሠራዊት መሠለፉን፤ መተካቱን ሲያረጋግጡ ስልትና ስትራቴጅ ቀዬሩ። እዛ ግን ሚሊዮን ነፍስ አልዳነም። በኢትዮጵያዊነት ጸበል አልተጠመቀም። ኦህዴድ እንደ ቡድን በግልና በጋራ በመልካም ሐገራዊ መንፈስ በሚችሉት አቅም ልክ እጥብ አድርገው ብስጭቱን፤ ቁጣውን አለስልሰው ኦነግ/ ወያኔ/ ሻብያ መሬት ላይ የበተኑትን መርዛማ የልዩነት ግንብ ጥሶ የወጣ አህቲነት ፈጥረው ሰብሰብ አድርገው በኪዳን አዋውለው የማይበገር አቅም ፈጠሩ፤ የህዝብ ተጋድሎ ብቁና ብልህ መሪ ካለገኘ እንጨት ተለቅሞ ማሰሪያ ከሌለው እዛው ጫካ ውስጥ እንደመቅረት ነው።

ተጋድሏቸው መስዋዕትነቱ ባክኖ እንዳይቀር ታሪክን ለማቅለም ነው። ውጊያ ላይ እኮ ነው ያሉት። ለዛውም የእኛን መንፈስ ሁሉ አባብለው ቤተኛ አድርገው። ከዚህም አልፈው ኑ ተፎካከሩኝ፤ ብትችሉም አሸንፉኝ፤ የበለጠው የተወደደው ጠቃሚው ሃሳብ ለአንዲት ኦሮምያ ይባትል፤ ታሪካዊ ወቅቱን ብቻችን መጸሐፍ አንጽፍበትም፤ የሁላችን ይሁን አሉ - እነ አባ ቅንዬ። 

ትውልድ እናትርፍ፤ ሀገራዊ ራዕዩን እናሳምረው፤ ለወላጆቻችን ኩራት እንሁን አሉ። ኑልን። ፍላጎት ብቻ ግብ ስለማይሆን፤ መንገዱ ሳንክ እንዳይኖረውም በርቀት አስልተው መሠረት ለማስያዝ ህጋዊ ሥልጣን ያለው አካል ማዕከል ላይ መፍጠርን በጥልቅ ግንዛቤ እና ጥበብ ተጠበቡበት። ጠርተው፤ ጋብዘው እንዲታሰሩባቸው፤ እንዲንገላቱባቸው አይፈልጉም። 

አገር ውስጥም ያሉት በአቅማቸው ሙሉ እንዲንቀሳቀሱ ብረት መዝጊያ ክናድ ያስፈልጋቸዋል። እነሱ ስላሉ፤ ስለወሰኑ ብቻ የሚሆን ነገር የለም። ግማዱን ያወቁታል። እንኳንስ ለተፎካካሪ ለእነሱም በጦርነት ቀጠና ውስጥ ነው ያሉት። ይህን ደግሞ በእጃቸው ባለው ሥልጣን በተከበሩት ዶር. ነጋሶ ጊዳዳ ህይወታዊ ዙሪያ ላይ የሠሩት በቂ እርምጃ አለ። 

ካለምንም ቅድመ ሁኔታ 30 ሺህ ነፍስ ከካቴና ጋር ተፋቷል። ለዚህ እነሱ ሲተጉ ሌሎች ደግሞ „ለማ“ ካልሆነ ሞተን እንገኛለን ሆነ ጨዋታው። አቅም፤ ድካም፤ ልፋት መስዋዕትነት ሁሉ ከዋጋ የሚገባ አይደለም። ሌሎቹ ካልተቀበሉት አንድ ለማ ምን ሊያደርግ ይችላል? የለማ መንፈስ ጉልበታም የሆነው ማሳው ስለተመቸው ነው።

 አርሲያዊ ጥጉም ሌላ ላይ ተኮፈስ። ፈጣሪ ደግ አምላክ ነው ዘመን የፈቀደው ነገር ስላለ እሱም እርቃኑን እንዲህ በአደባባይ ሲቀር አሁን ደግሞ ጨዋታው ተቀዬረ። እኛ እንዲህ ነን። ሲቀናን ቀና ማለት የሚሳነን። የትውልድ ብክነት የልቅና መሰላል አድርገን በመርኽ ደረጃ የተቀበልን። የባሩድ ስንቅ ሰውን ያህል ፍጡር ሳንታክት እንዲቀርብ የምንፈቅድ።
  • ·        የማከብረወት ጸሐፊ አቶ ሰርጸ ደስታ፤


http://www.satenaw.com/amharic/archives/50821 የለማ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት ለአገርና ሕዝብ አደጋ ነው! (ሰርጸ ደስታ) ለማ ወደ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት መጣ ማለት በእኔ እምነት የተጀመረው ትግል ተመልሶ ወያኔ እጅ ሊገባ እንደሚችል ሥጋቴ ነው፡፡ እውነታው ዛሬ ላይ ጠቅላይ ሚኒሰቴሩ ምንም አይነት ሥልጣን እንዳይኖረው ወያኔ ሥልጣኑን ሁሉ ቆላልፋ እንደያዘችው ለአፍታም ቢሆን ሊዘነጋ አይገባም፡፡“ 

ከሥር ማን አለ? ማን ይመክታል አይደለም። የለማ መንፈስ እንደ ተለመደው የሶሻሊዝም ጉዞ በአንድ ዓይኑ የሚጓዝ መሰሎውታል። ከፈቀዱ አይደለም ማዕከላዊ ኮሜቴው እያንዳንዱ ዕጣ ነፍስ ወጥ መስመር እና መንፈሱ ምን ያህል ገዢ እና ውህድ እንደሆነ መመርመር ነው። የለማ መንፈስ የጀርባ አጥንት የአብይ መንፈስ ነው። ለሁሉም ሃላፊነት በመንፈስም በአካልም ዝግጁ ነው። 

ወላዊ መሰናዶው አራት ዓይናማ ነው። በሌላ በኩል ግን የፈቀዱት ኦሮምያ ያለው መንፈስ እንዳይበርድ „አቶ ለማ መገርሳ ከዛ ይሁን ነው። የጠ/ሚሩ ቦታ ሌላ ሰው ቢሆን ይሻላል ነው።

“ ይህን እኮ እራሳቸው አቶ ለማ መገርሳ „ዲዛይነር“ ሆነው በውስጣቸው በከተመው ረቂቅ ጸጋ ፈጽመውታል። ይህ ከሆነ በኋዋላ ደግሞ ሌላ ጹሑፍ ጻፉ። እኔ የመጀመሪያውን ዘልዬ ነበር በሁለተኛው ላይ የሰራሁት። ታደሚው ማያያዝ ብቻ ሳይሆን ተወራራሹ ሃሳብ በወጥ መንገድ አይቶ “ዱባ እና ቅልን አበቃቀሉ እዬቅል“ ስለመሆኑ ይመዝነው ዘንድ ሁለተኛውም እንዲህ ይላል። http://www.satenaw.com/amharic/archives/51605ማስጠንቀቂያ ለዶ/ አብይ አህመድ! (ሰርፀ ደስታ)

„ከአንዳንድ የኦሮሞ ወንድሞቼ የሚነሳው አስተያየት አብይን እኔም እንድጠይቅ አስገድዶኛል፡፡ ልብ በሉ እነዚህ ጠያቂዎች በኦሮሞ አክራሪነት ከምናውቃቸው ናቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ ያለው ነገራቸው ግን እኔም የምጋራው ሥጋት ሆነ፡፡ አብይንም በግል ከመጥላት አይመስልም፡፡ እኔም ወደ ኋላ የአብይን ንግግሮች ከለማ ጋር ሳስተያይ ያላቸው ስብዕና የተለያየ ነው፡፡ አብይ የግል ፍልስፍናውን ብዙዎች እንዲያደንቁለት አስቦ እየተናገረ፣ ገበያ እየሰበሰበም እንዳይሆን ሰጋሁ፡፡ ለማ እንደዛ አደለም፡፡ ለማ ጋር ቁጭት አለ! ለማ ጋር ከምርም የሕዝቦች የድሮው ትዝታ አለ! ለማ ጋር የማያሻሙ በግልጽ ራሱ የፈጠራቸው ለሕዝብ ወኔና ጉልበት እንዲሁም አንድነት መድሀኒት የሆኑ ፍልስፍናዎችን ነው የምንሰማው፡፡ ለማ የሚያወራውም ተጠንቅቆ አደለም ሕሊናው ያመጣለትን እንጂ፡፡ ይህ ደግሞ በእርግጥም ለማ ከልቡ አንደሆነ አናያለን ብቻም ሳይሆን በተግባርም ሲጋፈጥ ብዙ ጊዜ አስተውለናል፡፡“

እንደገባኝ ጸሐፊ አቶ ሰርጸ ደስታ አቶ ለማ መገርሳ ኦሮምያ ይያዝልን ከሆነ ኦህዲድ መልሶታል። ዶር. አብይ አህመድ እንዳሉ ስላልተቆጠሩ ማስጠንቀቂያው አስፈላጊም አይደለም። አልነበረም። መንፈሰዎት ኦሮምያ ላይ ብቻ ብርት መዝጊያ የሆነ ሰው ያስፈልጋል ነውና - የተነሱበት መቅደመ ሃሳብ መሰረት ይዟል። 

የጠቅላይ ሚ/ሩ ቦታ ከዬትኞቹ የአቶ በረከት የሴራ ቤት ማህበርተኞች የተሻለ ሊሆን እንደሚችልም በድፍኑ ነው የተዎት። ይሄ በራሱ መንፈሱን ሙሉ አያደርገውም። በሌላ በኩል የለማ መንፈስ እጣ ነፍሱን ነውም እያሉ ነው። በቃ አንድ ነገር ቢፈጠር ቀጥ ይላል አይነት። ይሄ ለነጻነት ፈላጊው ሥነ - ልቦና የአሸናፊነት ስሜት ተጫኝ ነው። በሥነ ልቦና አሁን ያለውን የለውጥ መንፈስ ተሸናፊ ያደርገዋል። በፊትም ለእርስው ዶር አብይ አህመድ አጀንዳዎት አልነበሩም። ዶር አብይ አህመድ ወረዳ ተወረወሩ፤ የትም ሄዱ ምንም ነው። 

ኦሮምያ ላይ አቶ ለማ መገርሳ እንዲሆኑ አልመዋል ያለሙት ሆኖለዎታል። በቃ። ይሄው ነው። ድሮም ኦህዲድን እንደ ቡድን ጥንካሬው ለመመዘን ዕምነት አልነበረዎትም። ዕውቅናም አልሰጡትም። ይህ ግን መብት ነው፤ እኔ የምሰጠዎት ወይንም የምነፍገዎት አይደለም፤ ሰው በመሆናችን የምናገኘው ጸጋችን ስለመሆኑ ጠንቅቄ አውቃለሁኝ። 

የእኔ ግዴታ ደግሞ አብይለማ፤ ለማአብይ አንድ ልብ ውስጥ የተፈጠሩ እና በወጥ ደማዊነት ውስጥ የሰከኑ ናቸው። የለማ መንፈስ ሲባል አብይን አግልሎ እነ አዲሱን 
አቅፎ እንደሰራው እንደ BBN ተዛነፍ እሳቤ አይደለም። መንፈሱ በ እያንዳንዱ ቅን ንጽህና ውስጥ ሰርጾል እንኳንስ በአካሉ። 

እነሱ ብቻ አይደሉም የኦህዲድ አካሉ ከሶሻሊዝም መንፈስ በእጅጉ የወጣ ያፈነገጠ ነው። ተፈጥራዊነትን ነው የማይበት። ሀገራዊ ሃላፊነት ለመረከብ በመንፈስም በህሊናም ሙሉ መሳናዶ በወል አለው ባይ ነኝ። ጥንካሬው ቡድናዊ ነው። ብቃቱም ቡድናዊ ነው። ብርታቱ ቤተሰባዊና ወጥ ነው። ፍልስፍናው ዘመን አሻጋሪ ነው። ተስፋነቱ በአስተማማኝ በሁለገብ እና በሁልአቀፍ መሰረት የተገነባ ነው። አንቱ ነው። ቅኔ ነው።

„ግን አንድ ነገር እንድታውቂልኝ የምፈልገው፡፡ አንቺ ስለወደድሽው ትክክል ነው ማለት አደለም“ የማከብረዎት ከዚህም ላይ ትልቅ ግድፈት አለ። እኔ ኢትዮጵያዊነት መንፈሱ ድርጁ መሆኑን ነው የምወደው፤ በሌላ በኩል ይህን ቢያነቡት መልካም ይመስለኛል። „ቅብዕ“ የእግዚአብሄር ነው። ይህ ቅብዕ የእኔ ወይንም የሌላ ውሳኔ አይደለም። 

እምነቱ ካለዎት። ለዚህም የጻፍኩት ከዚህ አለ። እኔ በፍጹም ከሹም ሽረት ጋር የተያያዘ አይደለም ጉዳዬ። ጉዳዬ የመተንፈሻ ቧንቧ ብቃቱ ሙሉዑነት ላይ ነው። የሆነ ሆኖ በሥልጣን ጉዳይተጻፈውን http://www.satenaw.com/amharic/archives/51388 „ምነው እግዚአብሄር ተረሳ?“ የሚለውን ጹሑፌን ቢያዩት ይገልጥለዎታል። ከፈቀዱ። ይህ ማለት ግን ዛሬ ኢትዮጵያ መሬት ላይ ብቁ መንፈስ እንዳለ ሙሉ ዕምነት አለኝ። እዳሪ የሚያስጠብቅ ምንም አመክንዮ የለም። ቀሪው የፈጣሪ ሥራ ነው።

„የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ደግሞ አካሄዱን ያቃናለታል።“

ከሆነም ከቤተ - ፈርዖን፤ ከቤተ የሥጋ ፈቃድ ጸያፍ ማህበርተኞች፤ ከቤተ ጸረ ሰው እና ዘር መንጠሪዎች እንዳይሆን ሱባኤ አይደል አሁን? ይጸለይበታል። እራሱ ለዚህ ቦታ ይህ በኢትዮጵያ ሥም የሥጋ ገብያ ኪዌስክ ማህበርተኛ መንፈስ መታጨቱ፤ ኢትዮጵያዊ ክብሯ ንጽህናዋ እንዲህ ሲላሽቅ የሀገሬ ኤሉሄ ያሰኛል። ተኝተህ በለኝ የለም። ሥነ - ምግባሩ ሊሰሙት ከሚዘገንን መንፈስ ጋር እናት ሐገሬ ኢትዮጵያ ባትነሳ እመርጣለሁኝ።

እኔ እኮ „ጣና ኬኛን“ ያዘከረ አቅም ነው መነሻዬ መድረሻዬም። ያ መንፈስ ለእኔ እንደ አልባሌ የተወረወረ አልነበረም፤ የ አብቹ መንፈስ ወራሽነቱን ከውስጤ አዳምጬዋለሁኝ። … ሰው ህልሙን ባልጠበቀው ቀን እና ጊዜ ሲያገኘው ከደስታ በላይ ሐሴት ነበር። አማራ ለሆነ ሁሉ ዛሬ ያለው ወጀብ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ በላይ በሁሉም አቅጣጫ ራሱን እያጋለጠ ስለመጣ ዘብ መቆም ግድ ይለኛል። 

የማጠፋት ቅንጣት ደቂቃ የለችም። እኔ አይደለሁም ለዛ መከረኛ መሬት ላይ ያለሁት „ኢትዮጵያዊነት ሱስ“ ብቻ ነው ያለው። ጋሻውም መከታውም፤ መመኪያውም ተስፋውም ለተገፋው፤ ሐገር አልባው ማህበረሰብ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ መዳኛ መከላከያ ሚኒስተሩ፤ ጠበቂው አረጋጊው ነው። ስለዚህ ከፈጣሪ በታች ሊሆን በሚችለው ሁሉ ተጋድሎዬ ይቀጥላል። የሎሬቱ ታቦትም አለኝ አብሮኝ።  

·        የጫና ውትድርና።
አሁን ጫና መፍጠር ሥራዬ ተብሎ ተይዞ ነቀምት ላይ የኦህዲድ የደም ዝውውር መስመር መቋረጥ እንዲኖረው ሆኗል። ለወያኔ የብቅላ ድውለት ተመቻችቶ ያ መከረኛ ህዝብ የሰው ልኳንዳ ቤት ተከፍቶለታል። 1,000, 000 ህዝብ አውላላ ሜዳ ላይ ፈሶ፤ ካለትዳር፤ ካለቤተሰብ፤ ካለትምህርት፤ ካለወላጅ የቀሩ፤ በምግብ እጥረት፤ በወሊድ፤ ተገዶ በመደፈር ስንት መከራ ላይ ያለ ወገን እያለ፤ መንፈስን አረጋግቶ በስልት እና በዘዴ መጓዝ ወይንስ ተጨማሪ መርዶ ማምረት? 3000 እስረኛስ ተመልሶ ይግባ ከዛ የምድር ሲኦል? ያን ያህል ቀን እና ሌት ነርባቸው እስኪበጠስ የሠሩት ተግባር ሁሉ ባለቤት አልባ ፈሶ እንዲቀር አንዲህ ታደመበት? ትልቅ የታሪክ ግድፈት። 

ሥልጣኑ ቢኖር ከቶ ከዚህ በላይ ተጋድሎ ይደረግ ነበርን? አሁን ለዛች ለወ/ሮ ታደሉ እህት፤ አክስት፤ ጓደኛ ማን ይድረስላት? አቀጣጠልን በቃ … ሞት በድል፤ ካቴና በዲል ለአራዊት የቁርሾ ማወራረጃ። አውሬው የፈለገውን አወረስነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ፈቅዶ እና ወዶ የፈታ ይመስል መልሶ ከዛ ሲኦል ለመግባት መታገል። አይገባኝም። አንዲገባኝም አልሻም።
  • ·        አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማንን አልሞ ይሆን?


የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እኮ እንደ ሥርጉተ ለኦህዲድ፤ ለቲም ገዱ አንዳርጋቸው፤ ለዶር አንባቸው እና ለኮ/ ደመቀ ዘውዱ ነው። የሞት አዋጅም አይደለም ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ አልተፈጠረም ነው የሚለው - መንፈሱ። ለዚህ ሰው ለሚባለው ፍጡር ደስታ ትጋት ካለ ከመዳፌ ውስጥ ነህ ነው። 

ያን ጥሶ ሰዎችማ አለን ብትፈልጉም ግንባራችን፤ ቢያሻችሁ እግር ከወርች ለካቴና ይሄውላችሁ ብሎ መሪ፤ ምልክት፤ ተስፋዬ የሚባል አካል ስለህግ ጥብቅና አብነት ነው የሚባል መንፈስ ሄዶ ከመትረዬስ ጋር ግብግብ ፈጠረ። ወሸኔም ተባለ። አላስፈላጊ መስዋዕትነት መፍቀድ? ምን ይባል? በዚህ እነሱ የቀሩትን ለማስፈታት ይተጋሉ ሌላ ተጨማሪ ሞት፤ ሰቆቃ፤ እስራት፤ አፈና፤ ግድያ የመንፈስ መረጋጋት ቀረመት። 

አውሬው ኦህዲድን ለሚያጨናንቅለት ዶላሩን ያፈሳል። ይህን ማስተዋል የሚባል የት ሄድክ ተብሎ ቢጠዬቅ ምን ሊመልስ እንደሚችል አይታወቅም። በጭንቅና በቀውጢ ወቅት ሌላ ስልተቢስ እርምጃ። 

አዬሩ እራሱ ቁጡና ብስጩ ነው። ቀድሞ ነገር አኮ አሁን ያን ያህል ዘመን ተኑሮ ሱሪ ባንገት የሚገባም አይደለም፤ አይደለም እስር ቤት አንድ ቀን ኢንተርኔት ካልታዬ መረጃውን ለማሰባሰብ ያቅታል - ብዛቱ ይውጣል። 

እና ከእስር የተለቀቀ መንፈስ ማጥናት፤ ማድመጥ፤ መመርመር፤ በተደሞ ጸሎት ማድረስ የምስጋና ጊዜ ሁሉ ያስፈልጋል። ሰው መሆንን የሰረዘው ህግ ባይወጣ እንኳን የመጀመሪያው ሆኑ ቀጣዩ ስክን ብሎ አካባቢን ማጥናት፤ መመርመር ያስፈልጋል። ስክነት። አቀባበል የሚፈይደው ደስታ ቢኖርም በተከለከለ መንገድ ተሂዶ አይደለም።

 የሚፈይደው ነገር ወቅቱን ያደመጠ አቅም እና አቅል አምጦ ወልዶ አቅም ሆኖ ለወጣው መንፈስ የአቅም ጥሪት ለመሆን በቅንነት መሰናዳት ነበር የሚያስፈልገው። በስተቀር ወጀቡ … የሚምረው የሚያተርፈው የለም። ለወጀብ ህግ አልተሰራለትም። እናትን፤ ልጅን፤ ሚስትን ነጥሎ አያጠቃም መንገዱ ላይ ያገኘውን ሁሉ ይጠርጋል። አደበ ከተቆመጠ።

„የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ“ የተባለ ይመስል ጥድፊያ፤ ውጥረት፤ ለሰሚውም እጅግ ግራ ነው። እነሱ ላይ ተጨማሪ ጫና፤ ተጨማሪ የቤት ሥራ፤ ተጨማሪ ሰቀቀን፤ እሳት እንዴት ይፈጠራል። የተፈቱ እስረኞችም እኮ በኦህዲድ እና በገዱአነቤ ጫና ነው። መልሶ ለማስገባት ለሰከንድ አውሬው የማይደራደርበት ጉዳይ ነው። 

ነገ እኮ ኦህዲድ የሆነ ሁሉ ለእንደገና ስደት፤ አስራት፤ ሞት፤ የበቀል ገጀሞ ሊዳረግ እንደሚችል አላስተዋልነውም? ምንአለብን እኛ የሙሽራ ልብስ እና የሚዚ ልብስ እናማርጥ - ዘመናዮች። እዛ የቀሩትስ እሳት ይለቀቅባቸው ምን ይሁን በእጃችን ምን አለን? እዬባሰ ሲሄድ አኮ ክንፋ የደህነነት ማዕከል ያሉትን ሁሉ በጀምላ ሊጨርሷቸው ይችላሉ። ተፈጥሮና ፈተናው ታይቶም ካልገባን ሌላ መምህር መቅጠር አያስፈልግም።  
  • ·        የማከብረዎት ጸሐፊ አቶ ሰርጸ ደስታ


ይህን የእኔ መንፈስ የተቀበለውን በዚህም ዙሪያ የደከምኩበትን የሃሳብ ማህበር አገናባብ ንፋስ እንዳይገባው፤ የእኔ የመንፈስ ማህበር ይሄም አለ ብሎ በጥረጣሬ እንዳይመለከተው መልስ መስጠት ግድ ይላል። ይሄው ነው የማከብረዎት። በተረፈ እንኳንም እርስዎን ልጅ ቢኖረኝ የእኔን ሃሳብ ተቀበል ብዬ አላስገድደውም። „ዱባ እና ቅል አበቃቀሉ እዬቀል“ ስለመሆኑ አውቀዋለሁ እና። ይሄው ነው። 

ይህ አምለጥፈው ሊንክም ለእርስዎ አይደለም። የእርስዎን ሊንክም ሆነ የBBN ስለጥፍ ሚዛኑን የሚያስጠበቅልኝ ማመሳካሪያ ማቅረብ ግድ ስለሆነ ነው። ይህ የመጨረሻዬ ነው። ይቀበሉም፤ ይውደዱም አይደለም። መብትም የለኝም። ያለኝ መብት ለራሴ ብቻ ነው። እርስዎም ሥርጉተን እንደ ሰርጸ እንደ እኔ ሁኚ ማለት እንደማይችሉት ሁሉ። 

እኔ የእናቴ ልጅ የለም። ግን እንደ እርስዎ የሐገሬ ሰቆቃ ህመሜ ነው። ትውልድ እንደዚህ በዬቀኑ እዬባከነ እንዴት ነገ ይታሰብ? በሌላ በኩል ቀደም ብዬ እንዳነሳሁለዎት የእኔ የመንፈስ ማህበረተኛ ወደ እርስዎ እንዳይሄድ መከላከል አለብኝ። 

ማጥቃት ባይቻልም አቅሙን አጽንቶ በሃሳብ ውስጥ ማቆዬት የተከላካይነት ተግባር መከወን ግድ ይላል። አቅም አቅም ነውና። በተረፈ መልካም ጊዜ እንዲሆንለዎት በድጋሚ እምኛለሁ። አልመለሰብትም።  ይኑሩልን። ደህና ይሁኑ።    
  • ·        ለቅኖች።


ይህን ሊንክ ከላይ ለጥፌያዋለሁኝ። አሁን ደግሞ ደግሜዋለሁኝ። እጅግ የማከብራችሁ የሀገሬ ልጆች „በአንድ መንፈስ ሁለት ፍላጎት“ ስለሆነ ከላይ ያነን ለማጠዬቅ ነው የተለጠፈው። በዚህ ምክንያት ጥግ ያጣውን መንፈስ ለመሰብሰብ፤ ማህል ላይ ቀርቶ የቱን ልምረጥ ያለውን መንፈስ ተስፋ ቆራጭነቱን ስታስቡት ደግሞ ያማል። ቁስለት!


የሆነ ሆኖ ከዚህ ደግሞ ደግሜ የለጠፍኩት ዶር. አብይ አህመድ የተነጻጸሩበት ሁኔታ ገራሚም ብቻ ሳይሆን እንድንመረምረው ግድ ስለሚል ነው። „ሰው“ አይደለህም ለማለት ትንሽ ነው የቀረው።

https://www.youtube.com/watch?v=tSKRWiXexSU

BBN Presents Jawar Mohammed | Lemma Megersa | Oromo | Amhara | EPRDF


በዚህ ውስጥ አጠቃላይ እድምታው፤ ከጠያቂው ሙግት ሳይገጥመው እንደልቡ የሃሳብ ጅረቱ ፈርሿል እንደ ልቡ። ስለሰብዕና አቅመ ቢስነት፤ ስለወትድርና ዕውቅት ባዶነት፤ ስለ ህዝብን የመምራት እና የማስተዳደር ድህነት፤ ስለህዝብ ተቀባይነት ወናነት፤ ስለ ህሊና ልሙጥነት የተጠቀሰ አለ። 

ለእኔ አቶ ለማ መገርሳ ይሁኑ ዶር አብይ አህመድ እንደ ቀለማቸው ልዩነት ሳይሆን አንዱ ያለውን ከሌላው ጋር በዝንቅነት ሳይሆን በውህድነት መስተጋብራዊ ሃይል የፈጠረ ታላቅ የሥጦታ ቋንቋ ነው የሁለቱ አካል ተ- አምሳል ጉዞ። ያው በዚህ ቃለ ምልልስ ከሰውም ደረጃ በወረደ ሁኔታ የተሰጠው ትንታኔ ፍርድና ዳኝነት የህሊና ስለሆነ አዳምጡት - በትህትና። እናንተው ዳኙት።“ታዋቂ“ አይደሉም ነው። 

እንኳንስ ለኢትዮጵያ የተባባሩት መንግሥታት ያውቃቸዋል - በክብር። ከሁሉም ጥሞናን የሚፈተተነው „ተክለ ስብዕና የሌለው“ ይላል። እኔ ፈላስፋ ዘረ-ያቆብን ተኩ የምላቸው ኢትዮጵያዊው የህሊና የአዎንታዊነት ተመራማሪ አብነት ዶር ምህረት ደበበ ጋር ለመሥራት መፍቀድ በራሱ የሰውነትን ማንነት መለኪያውን አልፎ የሚሄድ ጽድቅነት ነው - ለእኔ። ሌላም አስተዳደር እና ርህርህናውን የሚገልጥ ማመሳከሪያም አክላለሁኝ።  
  • ·        ማገናዘቢያ መቋሚያዎች።


Ministry of Science and Technogy(MOST), Leadership and Motivation Program

·         የኢትዮጵያዊነት ግርማ ሞገስነት።

https://www.youtube.com/watch?v=tkq-GB1mEWo&t=94s

Ethiopian news | dr abiy ahmed outstanding speech| ethiopian news today| youtube ethiopian news

·         ርህርህና እናመሪነት ክህሎት።

https://www.youtube.com/watch?v=8Z6HexcMHGU

Ethiopia - Dr Abiy ከላይ ስትሆኑ በዛ መነጽር ብቻ ታች አትመልከቱ

 

ሴቶች እና ውስጣቸው፤

https://www.youtube.com/watch?v=AHyuaT4mqz4&t=111s

Ethiopia Dr abiy የሰዉ ልጆች ልዩ ብቃት ክፍል አንድ

·         ኢትዮጵያ እንደገና መወለድ መንገድ

https://www.youtube.com/watch?v=k07ZojV5DXg

Ethiopia - ….ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች! ትለወጣለች!

·         ልምድ እና ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ።

  • ·        ባገኘው?


… እንዲያው „ቸር ተመኝ ቸር እንድታገኝ“ አይደለ ብሂሉ ፈጣሪዬን ባገኘው እምጠይቀው ፖለቲከኛውን ወጣት ጆዋር መሃመድን ስለምን እንደፈጠረው እጠይቀው ነበር - አማኑኤልን? በመልካም ውስጥ ፈተና፤ በፈተና ውስጥ መልካምነት የሚገናኙበት መስመር እንዲኖር አስቦ ይሆን እላለሁኝ? ወይንስ በጨለማ እና በብርሃን ውህደት የሚፈጠር አንድ ተፈጥሮ የሁለቱ ዲቃላ የሆነ ሦስተኛ ነገር ሽቶ ይሆን እላለሁኝ፤ ወይንስ በደስታ እና በሃዘን በትራጄዲ እና በኮሜዲ ውህደት የሚፈጠር ሦስተኛ ተውኔት አስቦ ይሆን እላለሁኝ። አንድ ላይ ተዋህደው በሚፈጥሩት ተውኔት ማህል ሰውን እናዬው ዘንድ ፈቅዶ ይሆን እላለሁኝ። 

የንግግሩ ፍሰት እና ንዝረት ሙቀቱ እዬጨመረ ሲሄድ፤ ምቱና አቅጣጫው በራሱ ሥም - የለሽ በሆነ ሁኔታ እታደምበታለሁኝ። ባገኘው የእኔን አማኑኤል ምክንያታዊ አቋሙን ፈጣሪዬ እንዲነግረኝ አጥብቄ እጠይቀው ነበር። እሱም ፍጡሩን ሲፈጥረው ካወቀው ነው ታዲያ? ለዚህም ነው በአሉታዊ የሚነሱበት ሃሳቦችን እንኳን እንዲህ ለማለት ፈልጎ ነው ብዬ ከማቃናት በስተቅር በሚያደርገው ነገር ሁሉ ብስጭት ዝር የማይልብኝ። የማልጽፍበትም። 

ምክንያቱም / ምክንያታዊ አመክንዮዎ ለእኔ ግብረ- ምላሹ በሃሳቡ ቀውስ ውስጥ ዘው ብዬ እንዳልገባ በድንበር እንድከታተለው ብቻ ሆኛለሁኝ። ካልተገደድኩኝ ሥሙን ማንሳት ራሱ አልሻም። ጠልቼው ግን አይደለም። ቢሆንማ አላዳምጠውም ነበር። 

ብቻ በወጣቱ ውስጥ ማወቅ እምፈልገው ሰብዕና እንዳለ ይሰማኛል። ይሄ „የስሜት ውጣ ውረድ ወጥነት፤ የሃብ ቋሚነት ዝልቅነት፤ የራዕይ ተከታታይነት እና ግባዕቱ“ የሚባል ሰብዕና ይመስለኛል የምፈልገው በታናሽ ወንድሜ ውስጥ - እርግጠኛ ባልሆንም። በእሱ ዙሪያ በአውንታዊ ይሁን በአሉታዊ የሚወጡ ጹሑፎች እራሱ ባለቤትም/ ባለቤት ያልሆነም ስሜት የለኝም - ሳነበው። ቀለም የለውም ስሜቴ። 

ስለምን? እኔም እራሴ አላውቀውም፤ አንዳንድ ጊዜ ልጄ ቢሆንስ? መስመራችን በምን ይዘረጋ ነበር? አዲስ ቋንቋ ፈጥረን እንግባባ ይሆን የሚል ስሜት ሁሉ ያድርብኛል። የሰውን አፈጣጠር ትርጉመ - ብዙነት በጥልቀት ያሳዬኛል - ይመስለኛል። ግን ስለምን ይሆን? አላውቀውም - እኔው።  
  • ·        መውጫ።


ወገኖቼ ስሜት እና ወጀብ፤ ወጀብ እና ተስፋ የኖሁን መርከብ አቅጣጫ የመምራት አቅም እንደ አገኙ እንዳይለጉት፤ አቅጣጫውን በውል በወልም ማድመጥ፤ ማስተዳደር እና መምራት የሚቻለው ውስጣችን ያለውን ውስጥ ለማወቅ ጥረት ስናደርግ ብቻ ነው። ህሊና ሚዛኑ የተሟላ ይሆን ዘንድ ማገናዘቢያዎችን የእኔ ብሎ መመርመር ያስፈልጋል።

 የትውልድ ውርርስ ቅብብል በተረጋጋ እሳቤ እና በሰከነ አዕምሮ መመራት እንዲቻል ራስን መስጠት ግድ ይላል። ኩርዲሾች ማንነት አላቸው ግን ማንነታቸው ለእነሱ ብቻ እንጂ ብናኝ የእኔ የሚሉት ማረፊያ ብትን አፈር የላቸውም። ቁራጭ መሬት የላቸውም። ማንነታቸውን የሚገልጡ ተቋማት የላቸውም። 

ብናኝ ብትን አፈር ስሌላቸውም ነፍሳቸው ባተሌ ነው - የባዘነ። ሥነ - ልቦናቸው እጅግም የተጎዳ ነው። ጋዜጠኛ የኩርድሺ የነጻነት ታጋይ የራዲዮ ሞደሬተር ጓደኛ አለችኝ። ስትራምድ እዬባነነች ነው፤ አንድም ቀን በስክነት አይቻት አላውቅም። መንፈሷ በቀውጢ ውስጥ ነው። አንድ ቀን ቁጭ ብላ መንፈሷን ለማድመጥ አትፈቅድም። ብክን ብላለች። ስለዚህ ስጠይቃት ለዚህ ትክክለኛው ቦታዬ „መቃብር ብቻ ነው“ ነበር ያለችኝ።

ይህን ሳስበው የኩርድሽ ህዝብ መንፈስ ምን ያህል በመኖር ውስጥ ሥነ - ልቦናው መቃብር እንደሆነ ሳስተውለው ተሰቃዬሁኝ፤ አሳቀቀኝ። ኩርድሾች በተለይ ሴቶች እጅግ ስመጥር ጀግኖች ናቸው። ጫካ ውስጥ የሚሰሩት ገድል ከዬትኛው ፕላኔት ነው የመጡት ያሰኛል። ዛሬ … ዛሬ እዬደከመኝ ቀረሁ እንጂ በዝግጅታቸው እገኝ ነበር። አርበኝነታቸው ትጋቱ፤ ቀለሙ፤ ጥንካሬው ደማቅ ነው። የሆነ ሆኖ የእኛ ዕጣ ፈንታ ይህ እንዳይሆን እስከ አሁን በተለያዬ ጊዜ ፈዋሽ መንፈሶች ተነስተው ድጠን፤ ሰባብረን ሞት ሰንቅን ኖረናል። ዕንባን ተወዳጅተን ኖረናል። 

መራራ ሃዘን ተቀላቢ ሆነናል። ሐገር ያጣን እለት ደግሞ ከመራራው ሁሉ የበለጠ መራራ ይሆናል። እንሰብ! „እናት አባት ሲሞት በሐገር ይለቀሳል፤ እህት ወንድም ሲሞት በሐገር ይለቀሳል፤ አክስት አጎት ሲሞት በሐገር ይለቀሳል፤ ሐገር የሞተ እንደሁ ከዬት ይደረሳል“ አባቴ በልጅነቴ በዝምታው ውስጥ ጥሶ የሚወጣ ሞገዳማ ቃለ ህይወት ነበር። ዜማውም፤ ግጥሙም ደራሲው ማን እንደሆነ ግን አላወቅም። መልዕክቱ ግን መጸሐፍ ነው። በዚኽው ይከወን። ጨረስኩኝ።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

„ሁላችንም አድገን አልጨረስንም!“
„ከማከብራቸው ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ከኢትዮጵያ ተመራማሪ ሳይንቲስቶች ጉባኤ ከተናገሩት - የተወሰደ።“
የኔዎቹ ኑሩልኝን ደስ ብሎኝ ሸልሜያችሁ ወደ ሌላው ብራና መጭ ልበል …
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።