አቤ ጎቤ ህያው ነህ!
የጥቃት ማርከሻው አቤ ጎቤ ህያው ነህ ! ( ሥርጉተ – ሥላሴ ) ከሥርጉተ – ሥላሴ፤ ከጭምቷ – ሲዊዘርላንድ። (16.02.2018) „ የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። “ ( ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱ ) የውስጥነት ማርዳ፤ የመሆን አንባነህ፤ ደመሙቅ ሳተና ውለታ ብዙነህ። አንተ የእኛ ቤዛ የክብር ቀለም፤ ቀስተዳመና ላይ ህላዊ ለምለም። ደምህ ተቆጥቶ ሲጠራህ ጫካው፤ ቃልን አዋውለህ በነፍስህ ጠለፍከው፤ ኪዳንን አድርሰህ ሰማዕትን ሸለምከው ። መከታ የሆንካት ለዛች የዕንባ ዕንክብል፤ አለሁልሽ - ም፤ ያልካት የችሎት አንበል። አንተ የእኔ ጌታ ! ያራራይ መዝሙር፤ አንተ የእኔ ጀግና ! የግዕዝ ገበር። ጥቃትን ያወጣህ የዕዝል ቀንዲል፤ ተምሳሌት አባት የተግባር ሰብል። የኔታ ልበልህ የደምጥሪኝ ግሥ፤ አባ ጎቤ ታጠቅ የአንበሳ ልሳን። በሥምህ ድል ይሁን ትውልድ ይቀስስ፤ ደምመላሽ ተፋሲል የኲራት ቆሞስ። እንደ ጠፋ አይቀርም፤ አንደ ጨለ...