ጥሎብን መልካምነትን መጋፋት ነውና።
… ሰው ማበርከት አናውቅበትም፤ አልተሰጠነም፤ ጸጋችንም አይደለም። „ሰባት ሳምንት ትቆጥራለህ፤ መከሩን ማጨድ ከምትጀምርበት ቀን ጀምሮ ሰባት ሳምንት መቁጠር ትጀምራለህ።“ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፲፮ ቊጥር ፱ ሥርጉተ ©ሥላሴ 09.08.2018 ውዶቼ ያልተጠናቀቀው ጉዞ በሚመለከት ሊንክ እና አስተያዬታችሁን ለላካችሁልኝ የእኔ ጌጦች እጅግ አድርጌ አመሰግናችሁ አለሁኝ። ወጣ ያለም ሰለሆነ እንደ እናንተ ሌሎቹም ሊኖሩ ስለሚችሉ ትንሽ ልባል። የበጎ ፈቃደኝነት ወጣቶችን ገለጻ እንዳደረጉ ይህን እማ ሳተናው ላይ አግኝቼው አዳምጫዋለሁኝ። አገላለጹም ተሳታፊዎችም አዲስ ናቸው። ንግግራቸውም እጅግ ቀስሰተኛ የደከመው ነው። የውስጥ ደስታ በፍጹም ሁኔታ የራቀው ነው። እውን ያ አንበሳ ዶር አብይ አህመድ ናቸውን ያሰኛል? የተለዬ ነገር እኮ አላቸው? ይህ እርግጠኝነታቸው፤ ልበ ሙሉነታቸው፤ ድፍረታቸው፤ በራስ የመተማመን አቅማቸው፤ በመንፈሳቸው ውስጥ ታዳሚውን የማቀፍ የመሳብ ሃይላቸው ማግኔታዊ ነው እኮ። በእያንዳንዱ ቃል ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች እንዲሁ የሚታለፉ አይደሉም። የንግግር ክህሎታቸው እና ጸጋቸው ከተለመደው ውጪ ነው ግርማው። እንዲያውም ካነሳችሁትማ በዚህ ንግግር ውስጥ የሆነ የተቀሙት ነገር እንዳለ ይገልጻል አስተውላችሁ እዩት፤ የእኔ ግን ሌላ ነው ጭንቀቴ። አንደኛው ህልሜ ነው። ባዶ ወንበር እና የሌላ ፓርቲ ሊቀመንበር ግማሽ አካል ምን ማለት ነው ይሄ? ሌላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሴራ እና የኖርንበት መከራ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ እና የተስፋው ዘላቂነት ሁልጊዜ እክል ይገጥመዋል። ለግለግ ብሎ ወጥቶ እንዲታይ ተስ...