እቴ ሆይ!
እቴ ሆይ! ከሥርጉተ ሥላሴ 14.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) „ሕዝቤ ሆይ ና ወደ ቤትህ ግባ።“ (ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፭ ቁጥር ፳) እቴ ሆይ! ሙሽሪት እሸት አማራችቱ እቴ ሆይ! ቅዲስቲት ፍቅር ናፋቂቱ እቴ ሆይ! ህብሪቱ የዕምነት እልፍኝቱ እቴ ሆይ! ፍቅርተ የማተብ ርቱ እቴ ሆይ! ቀዳሚት የመሆን ሊቂቱ እቴ ሆይ! ቅኒቱ የዘመን ፍቱኒቱ እቴ ሆይ! መቻል ነሽ የሥርዬት እትብቱ። ...