ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 18, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

በእምዬ ሲዊዘርላንድ፤ ዙሪክ ክፍለአገር፤ በዙሪክ ከተማ በራዲዮ ሎራ የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ራዲዮ ከተመሰረተ ዛሬ #መስከረም 18.2025 ልክ ፲፯ (17) ዓመቱ። ተመስገን። አሜን።

ምስል
  በእምዬ ሲዊዘርላንድ፤ ዙሪክ ክፍለአገር፤ በዙሪክ ከተማ በራዲዮ ሎራ የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ራዲዮ ከተመሰረተ ዛሬ #መስከረም 18.2025 ልክ ፲፯ (17) ዓመቱ። ተመስገን። አሜን። #ምንጊዜም ኢትዮጵያ!   "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።"      ይህ ቀን ለእኔ ልዩ ነው። ይህ ቀን ለእኔ ትርጉሜ ነው። ይህ ቀን ለእኔ ሚስጢሬ ነው። ይህ ቀን ለእኔ ከእናት አገሬ ጋር ቃሌን በማዘውተር የማስርባት ዕለቴ ነው። ምንጊዜም #ኢትዮጵያ !   የጸጋየ ድህረ ገጽም በተመሳሳይ ዓመት ሰኔ 18 ነበር የጀመርኩት። በቲም ይሠራ ስለነበረ መቀጠል አልቻለም። የእኛ ነገር እንዲህ እና እንዲያም ነውና። ዛሬ የአባይ ሚዲያ ያለበትን ደረጃ ተመልከቱት። በተመሳሳይ ዘመን ነው የበቀሉት። ዛሬ አባይ ሚዲያ ቢጠሩት አይሰማም። አጋዥ ያገኜ ሚዲያ የት እንደደረሰ ተመልከቱት። መዝኑትም። ያ ብሩክ፤ ትሁት ሰው አክባሪው ባለቤቱም የአይቲ ባለሙያ ስለሆነ ጥገኝነት የሙያ አላስፈለገውምና። አስቀጠለው። እንኳንም ቀናው።    የሆነ ሆኖ የጸጋየ ራዲዮን ብቻየን ስለምሰራው #ህልውናው ቀጥሏል። የጸጋዬ ራዲዮ በጭምቷ በእምየ ሲዊዘርላንድ፤ ዙሪክ ክፍለአገር፤ ዙሪክ ከተማ በተናፋቂው እና በተወዳጁ፤ 24 ሰዓት በሚተጋው #በራዲዮ #ሎራ በ97.5 መካከለኛ ሞገድ በወር ሁለት ጊዜ በዕለተ ሃሙስ የቀን ቅዱስ #ከ15 .00 እስከ 16.00 እንደ አውሮፕውያኑ ሰዓት አቆጣጠር በአማርኛ ቋንቋ ይቀርባል።   ይህን ተግባር ስደተኛ ካንፕ ውስጥ የምትኖር አንዲት ባተሌ ስትወጥን በባከነ ጊዜ የሚባዝን መንፈስ ራዲዮ ፕሮግራሙ #ተከሰሰ ። የሚገርማችሁ ከዚህ ቀድሞ ሌላ ክፍለ አገር ሄጄ በነፃ ስሰራም ኃላፊዬ ተከሳ ነበር። ከሳሾቹ የእኛው ጉዶ...