ልጥፎች

ከኖቬምበር 23, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአማራ እረቀ ሰላማ እንዴት? ከእነማንስ ጋር??? #ሚስጢረኛችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት!

ምስል
  የአማራ እረቀ ሰላማ እንዴት? ከእነማንስ ጋር??? እንዴት አደርን? የቅኔ አድባራት እንዴት ውለው አደሩ ይሆን? እነ ማህበረ ቅንነትስ እንዴት አላችሁልኝ??? #ሚስጢረኛችን #ኢትዮጵያ #ብቻ #ናት ! "የቤትህ ቅናት በላኝ።"       ይህ ጥያቄ ከ32 ዓመት በላይ ተቀንቅኗል። አማራ እንደ አማራ የጠላውም፤፦የሚጠላውም፤፦የሚያሳድደውም፤፦የሚያወግዘውም፤ ያፈናቀለውም፤፦ያሳደደውም፤ መኖሩን የቀማውም፤ ጋብቻ የከለከለውም፤ በጉርብትና ፊት የነሳውም፤ በግብይት ያገለለውም አይደለም ማህበረሰብ፤፥ተቋም ቀርቶ ግለሰብም የለም። ልብ እና ኩላሊት የሚመረምረው አምላክ አላህ ያውቀዋል። የእኛን ቅንነት እና ገራገርነት። ስለዚህም አማራ ሊታረቅም ብሎ አቤቱታ የሚቀርብለት ግለሰብ፤፥ተቋም ማህበረሰብ የለውም። ይልቁንም ከሙሉ የህሊና ካሳ ጋር ሊካስ የሚገባው የአማራ ህዝብ ነው። በዳዮቹ መበደላቸውን አቁመው ይቅርታ ጠይቀው ሊክሱት ይገባል። የመንፈስ ካሳ። ውሃ በቀጠነ ማቱ የሚወርደው በአማራ ላይ ነው። ነፃ አውጪወች ሲደራጁ የማኒፌስቷቸው ጭብጥ ፀረ አማራነት ነው። ስለዚህ ይህን ጭብጥ ቢተውት ተቋማቸው የሁሉም ይፈርሳል። እርቀ ሰላሙ ይህ እና ይህ ብቻ ይሆናል።   ህወሃት ሙሉ 47 ዓመት ሚዲያው ሊቃውንቱ ዛሬም ፀረ አማራ ዲስኩር ነው። ጦርነት የከፈተው የ፬ኪሎው ኦነግ ሆኖ ዛሬም ናዳ የሚለቀቀው በአማራ ላይ ነው። ኦነግ ፬ ኪሎ የንጉሦችን ንጉሥ የአጤ ሚኒሊክን ቤተመንግሥት በአማራ ትጋት እና ሙሉ ድምጽ አግኝቶ ዛሬም አማራ ላይ ዛሩ እንደተደረረ ነው። የከተማ ተቋማቱ፤ የጫንካ ክንፋ ውግዘቱም ምንጠራውም አማራ እና ጠረነ አማራ ብቻ ነው። የኦነግ ሊቃውንት የላንቃቸው ጠበለ ጣዲቅ ይህው ፀረ አማራነት ነው። ተማሩ አልተማሩ አንድ አይነት ማት ይ...