ልጥፎች

ከኖቬምበር 29, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ኑሯችን ኮንፓሳችን እና ካንፓሳችን ነው! መለመላ ያሰቀረ ሙግት - ተደመጠ በዋልታ።

ምስል
የህሊናን ቁመና መለመላ ያሰቀረ  ሙግት። „እግዚአብሄር፤ በጸሐይ ጮራ እንደ ደረቅ ትኩሳት፣ በአጨዳም ወራት እንደ ጠል ደመና ሆኜ በማደሪዬ  በጸጥታ ተቀምጬ እመለከታለሁ ብሎኛልና። ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፲፰ ቁጥር ከ፬ እስከ ፭“ ከሥርጉተ©ሥላሴ  29.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። በማለዳ የመጀሪያው ጉዳዮ ኢትዮጵያ እና አብዩ እስተ ሌጋሲው እንዴት እንዳደሩ ማረጋገጥ ነው። አንዳንድ ቀን ከንጋቱ 5 ወይን 6 ሰ ዓት ላይ ሁሉ አያሁኝ መረጃ። ምክንያቱም በዚህ በሸር በዘለበ የፖለቲካ ፍልስፍና ቀኑንም ሌሊቱንም አላምነውም። ስለዚህም ከአዬሁ፤ ካጣራሁ በ ኋዋላ የምስጋና ጠሎቴን አድርሼ ወደ ዕለቱ ውሉዬ ጉዞ አደርጋለሁኝ ማለት ነው። ዛሬ ደግሞ አንድ ሙግት አዳመጥኩኝ በቀደመው አጠራር የእኛ ልብ ውስጥ በነበረበት ወቅት  ከአብርሽ ጋራ። በ አሁን ደግሞ ከአቶ አብርሃም ደስታ ከ አረና ትግራይ ለሉአላዊነት ዴሞክራሲ ሊቀመንበር ጋር የዋልታ ቴቮዥን ሞጋች ጋዜጠኛ ጋር የነበረውን ውይይት ከውስጤ አዳመጥኩት። ዋው! ድንቅ ነበር። „አብርሽን“ ይህን በመሰለ የነጻነት አርበኝነት  እናውቀው የነበረው። https://www.youtube.com/watch?v=FmeGfeOaM_I&t=5s Ungerecht (injustice) neue አንድም ጹሑፍ ጽፌ ነበር የሁለት አገር ስደተኛ የሚል ዘሃበሻ ላይ ወጥቶልኝ ነበር፤ ይህ አጭር ፊልም ደግሞ ብዙ የሎቢ ተግባር የተከወነበት ነበር። ·        ወግና ቅኝት ተ ልዕልት ትዝብት ጋራ በቀለበት። አሁን ወደ ቀደመው ምልሰት ይሁን ከወንድማዊ ዕሳቤ ወደ የፖለቲካ ድርጅት መሪነት ሰለሆነ...