ልጥፎች

ዕውነትን መወገን ትውልድን ያንጻል። ለእውነት ቀጠሮ አያስፍልጋትም!

ምስል
ቋንጣ። „ምን እንኳን በለስም ባታፈራ፤ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፤ የወይራ ሥራ ቢጎድል፤ እርሾችም መብልን ባይሰጡ በጐችም  ከበረት ቢጠፉ፤ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ እኔ ግን  በእግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤ መዳድኃኒቴ አምላክ ሐሤት  አደርጋለሁ።“ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ፲፯ እስከ ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ  28.11.2018 ከገዳማዊቷ ሲወዘርላንድ። ·       እ ፍታ። ሴት ልጅ ሁነኛ ክንድ ሳይኖራት ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ መጀመር እኔ ባለኝ ተመክሮ እንደ እብደት ነው እማዬው። መከራ ብቻ ሳይሆን መኖርን የሚቃማ አሳር ነው። የማ ቆጨው በራስ ውሳኔ ስለሚሆን ብቻ ነው እንጂ ነገር ሴት የፈተና ተፈጥሮ ነው ያለው።  እንዴት አደራችሁ ዋላችሁ አመሻችሁ ውዶቼ አዱኛዎቼ። መቼም  ለኢትዮጵያ ሴቶች አዲስ ዘመን ቦግ ብሎ ብሩኽ ሆኖ ወጥቷል - ዛሬ ላይ። „ለእግዜር አይቀርበት ለሰው አይቀርበት ሰሌ ከሰራው ቤት እኛ ገባንበት“ ይላል የጎንደር ሰው ሲተርት። ገና ተወዳድራ ብታሸነፍ ተብሎ አንዲት ነፍስ ስንት ፍዳ ተከፈለ። ስንት መከራ ታዬ። ሥሟን የሚያነሳ የሚዋሳም አሳሩን ከፍሏል፤ ዕውቅናው ተቀባይነቷ እዬጎላ ሲመጣ ይህቺ ሽንብራ ከሰነበተች ዓይነት በሴራ ደቦ ከፖለቲካ ትግል የተገለለች ቅን ነፍስ እነሆ ዛሬ  የኢትዮጵያ አሉ የሚባሉትን የፓለቲካ ድርጅቶች ሊቀ ሊቃውንታትን ጉባኤ ከጠ/ሚሩ ጀምሮ የስብሰባው መሪ ሆና ጉብ አለች። ቅብዐ ያለው ነፍስ እንዲህ ነው። የፈለገው ነገር ቢገደብ፤ አጥር ቢሰራ፤ ክትር ቢበጅ ቅብዕ ካለ አይቀሬ ነው። ቅኖችም እንዲህ ሲገኙ መገናኛውን በቅኔ ዘጉባኤ ይቃኙታል እንዲህ ...  አሁን የዛሬ ዓመቱን ጉግስ ላሰበ ሰው ዛሬ የክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳን

ተመክሮ ለመከረው ክብር ይገባዋል!

ምስል
ብስለት። ተመክሮ ለመከረው ክብር ይገባዋል! „ቀን የሚያመጣው ምን እንደ ሆነ አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ።“  መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ከሥርጉተ©ሥላሴ 27.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ሊሂቃኑ የኢትዮጵያን የምሥራች ቀን ተገኝች ክብርት ትናፍቅሽ ሲባል አስከዛው ድረስ ነው እያሉ በሚመጻድቁበት ማግስት ትናንት አቶ ሌንጮ ለታ አንድ ቁም ነገር ላይ እርገት አድርገዋል።  ከዚህ ቀደመም የሸግግር መንግሥት አያስፈልግም ብለው ፊት ለፊት ወጥተው የሞገቱ ነበሩ፤ የዶር መራራ ጉዲና ህሊና የተጽዕኖ ፈጣሪዎችን የአንድነት መንግሥትን አዲስ ሽል ይዞ ብቅ ሲል፤ ሌላውም የሽግግር መንግሥት አሁኑኑ በማለት መለከቱን ሲነፋ አሳቸው ግን ግን አያስፈልግም ብለው ነበር አቋም የያዙት። ወደ አገር ሲገቡም  አጀብም፤ ጭብጨባም፤ ስልፍም አላስፈለጋቸውም እዩን እዩን  አላሉም እንደ ማለት። በዛው ሰሞናት ደግሞ ከአህዱ ራዲዮ ጋር ውይይት ሲያደርጉ ስለምን ያን ያህል ወጣት በባዶ እጁ ሲረግፍ ያልነበረ ድረጅት አሁን ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ ግርም ብሏቸው የት ነበር የዳውድ ኢብሳ ሠራዊት  ያን ጊዜ ወጣቶቹ ሲያልቁ በጥይት ሲቆሉ ሲሉ ተደምጠዋል።  በአህዱ ራዲዮ ቃለ ምልልስም ምርጫው በተያዘለት ገደብ ይከውን ብለው ግን መከወኑ አሁን ያለው ለውጥ ህጋዊ እውቅናውን ለማስገኝት ቢሆን የሚል ዕድምታ ነበረው እሳቤያቸው በቅጡ ከተፈተሸ። ትናንት ደግሞ ልብ ያለው ነገር ገልጸዋል፤ ራሳችን በ እርጋታ እሰክናደራጅ ድረስ እኛ በመጪው ምርጫ አንሳተፍም ለውጡ መሠረት እንዲይዝ እንተጋለን ብለዋል። ደፋር እርምጃ ነው ።  ደፋር እርምጃ ነው እምለው በምርጫው አለመሳተፋቸውን አይደለም። ምርጫ ለመሳተፍ የተመዘገቡት ፈሪዎች ናቸው

የአማራ ሊሂቃን ጉዞ ወደ አሜሪካ ወቅቱ አይደለም።

ምስል
መሄድ እንዳለ አለመመለስም እንዳለ ማሰብ ብልህነት ነው። „አለንጋ ለፈረስ፤ ልጓም ለአህያ  በትርም ለሰነፍ  ጀርባ ነው። አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል፤  ለሰነፍ እንደ  ስንፍናው አትመልስለት።“ መጽሐፈ ምሳሌ ተግሣጽ ፳፮፫፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ  27.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።   ሞት የትም ቢሆን አይቀርም የሚሉ ይኖራሉ? ዝቅ ብሎ ወጀብን ማሰለፍ ደግሞ ከሞትም ይታደጋል፤ ወደ ሞት ቆርጦ የሚገሰግስው አንድ አጥቂ ብርጌድ ይሁን ሻለቃ ገዢ መሪት ላይ የሚሟተው ሆነ ጉድብ የሚሰራው ሞትን ለመገደብ ነው። እንዴት ናትችሁ የኔዎቹ ውዶቼ? ሰሞኑን አንድ ዜና ሽው አለኝ። የኢትዮጵያ የተስፋን መንገድ በፈቃደኝነት እና በልበ ሙሉነት እንዲሁም በማይናወጽ ዕጹብ ድንቅ ታማኝነት በተጫማሪም የግል ኢጎን በፍጹም ሁኔታ በመርታት፤ ቃላቸውን ሳያጥፉ ብሩሁን ዘመን ከመሩት ኢትዮጵያዊ ሊሂቃን ውስጥ ሦስቱ ሥላሴዎች ወደ አሜሪካ እንደሚያቀኑ አዳምጫለሁኝ።  አቶ ደመቀ መኮነን፤ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው እና ዶር አንባቸው መኮነን። ይህ የግብዣ ቅደመ ሂደት በእንሱ ፈቃድ ወይንስ በሌላ ጋባዥነት ሙሉ መረጃውን አላውቀውም። ብቻ የኢትዮጵያ ኢንባሲ በአሜሪካ ከሰሞናቱ መግለጫ እንደሚሰጥ እያዳመጥኩኝ ነው። ለምን እንዳስፈለገ ባይገባኝም፤ ያስፈለገበት ምክንያት እና ተጨባጩ ሁኔታ ሊገናኝልኝ ባይችልም እኔ እምለው ነገር ግን ልቅምቅም ብለው አሉ የሉም የሚባሉ የአማራ የህልውና ታገድሎ አድምጭ መንፈሶች የህሊና መቅኖዎች እንዲህ በጉዞ ሊታደሙ ሲታሰብ  ከፊት ለፊቱ፤ ከጀርባው፤ ከጎኑ ከ ኋ ዋላ፤ በደረቱ ምን አለ ብሎ ማሰብ ይገባል ባይ ነኝ። ምክንያቱም በፖለቲካ ጨዋታ ውስጥ መታመንም ማመንም የጊዜ የቦታ የሁኔታ ጉዳይ ስለሆነ