!ዳግማዊ አባ ኮስትር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የማን ናቸው?
!ዳግማዊ አባ ኮስትር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የማን ናቸው? ! „አንተ በህይወት ሳለህ አእምሮህም ሳለች ግብርህን አትለወጥ።“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴ ቁጥር ፳፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 05.01.2019 Sergute©Selassie ፍቅር በፍቅር! · ከእመ ዝምታ ከእናቱ ሲዊዝ ዋው ሻሾ ፍጥነቱን ጨምሯል ዛሬ የታደለ ቀን ነው። ሻሾን እወደዋለሁኝ እንደ አድዮ ነው የማዬው። በቃ በዚህ ከቀጠል ነገ ነጭ ስጋጃ ለሰንበት ሙሽራ አንጥፎ ይጠብቃል ማለት ነው። ግን ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? · ወግ ቢጤ …. ሰሞኑን አንድንድ ዜናዎች ከዚህም ከዚያም ሲወርቡ ደፍሬ መጻፍ አልቻልኩም። የጠራ መረጃ በግራ በቀኝ ማግኘት ስለነበረብኝ። አቶ ንጉሡ ጥላሁን የጠ/ሚኒስተር ጽ/ቤት የፕሬስ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው እርግጥ መሆኑን ዛሬ የበለጠ አረጋግጫለሁኝ። ስለሆነም በዚህ ዙሪያ የምለው ይኖረኛል። · አቶ ንጉሡ ጥላሁን የማን ናቸው? ለመሆኑ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የኢትዮጵያ? - የአማራ? - የጉራጌ? - የኦሮሞ? - የዜግነት? - የዞግነት? ከቶ - የማን ናቸው። እንደ ሥርጉ ሥላሴ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የራሳቸው ብቻ ናቸው። እድግመዋለሁኝ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የራሳቸው ብቻ ናቸው። ለሁሉም መስመር ደግሞ ሊንክ አገናኝ ድልድይ ናቸው። ለውጩም ለአገር ውስጡም። ዘለግ አድርገን ስንሄድበትም ከዚህም ያለፈ ይሆናል። ወደ ሌላ ዓለም ይዶለናል። ለጊዜው በቁጠባ ይያዝ ... እንዲህ ዓይነት...