ልጥፎች

የራስነገር።

ምስል
የራስ ነገር ። „አንተ በህይወት ሳለህ አእምሮህም  ሳለች ግብርህን አትለወጥ።“  መጽሐፈ ሲራክ ፴፳ ቁጥር፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 04.01.2019 ከእመ ዝምታ - ከሲዊዘርላንድ። መቅድም። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? የራስነገር። የራስነገር ብዙ ነው። የራስነገር ሁለመና ነው። የራስነገር ሁለንትና ነው። የራስነገር መስታውት ነው። የራስነገር ሰውኛ ነው። የራስነገር ተፈጥሮኛ ነው። የራስነገር መ ሆን ኛ ነው። የራስነገር ቢሆንም ባይሆንም ቢያምርም ቢከፋም ብቻ የራስነገር የራስ ነው። አፍንጫው ደፍጠጥ ከንፈሩ ነፋ፤ ፊቱ ከስከሰከስ ቁመቱ አጠረ፤ ሰውነቱ ደንበል ትክሻው ጠበብ ያለው የራስነገር ከሆን ደስ ይላል ይወደዳል። የመቻል ትሁቷ እህቴ አጭር ወንድሟን እሰከ ነፍሷ ነው የምትወደው። የትዳር አጋር ግን ምርጫዋ ረጅም ነው። እሷ እራሷ አጭር ናት። በዛ ላይ ባርቾ ናት። አጠር ያለ የትዳር አጋርነት ጥያቄ ቢያቀርብ ሁለ ነገሩ ቢስማማት ግን ላትፈቅድ ትችላለች ዘለግ ያለ ስለምትሻ።  ለወንድሟ ግን ቅድመ ሁኔታ መስፈርት አይወጣለትም የራስነገር ስለሆነ ጌትዬ አባትዬ ትለዋለች። እሱን ሳታይ፤ ትንፋሹን ሳታዳምጥ ውላ ማደር ጭንቋ ነው። እህቴ ወንድሟን እንዲህ ነው  የምትጠራው አብዬ ጌታዬ አባትዬ ቁልምጫው እንክብካቤው ልክ የለውም።  ሌሎቻችን ትርፍ ነን። እሱን የመሰለ ሰው በምድር የተፈጠረ አይመስላትም። ጋብቻ ላይ ሲመጣ ደግሞ ቆንጆ ወንድ ነው ምርጫዋ። ወንድሟ ደግሞ አሜሪካዊውን ስሚዝ ነው የሚመስለው በቁመት እንዲያውም ከስሚዝ አጠር ይላል። ስለምን ወንድሟን መረጠችው ሲባል የራስነገር ስለሆነ። የራስነገር ተወዳጅ፤ ተፈቃሪ ነው። ·        ስለራስነገር ሲሰላ።

ነገረ ዛለአንበሳ፤ ነገረ አልበሽር እና ዕድምታው

ምስል
ነገረ የዛለአንበሳ         እና       ዕድምታው እንደ ሥርጉተ ዕይታ። „ብዙ መከራ የተቀበለ ሰው ብዙ ትምህርት ይማራል።“ መጽሐፈ ሲራክ ፴፩ ቁጥር ፲፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.01.2019 ከእማ ዝምታ - ተሲዊዝ ። ·        እንደ መግቢያ። እንዴት አላችሁልኝ ቅኖቹ። ዝምታው ቀጥሏል። እሰከ ረፋዱ ድረስ የመኪና ጩኸት እንኳን አልሰማሁም። ኳኳ - ኳኳ  አደረኩኝ - በቀስታ፤ ደወሉን አልጫንም። በእጄ ነው እማንኳኳው። ጉዳዬ ለጎረቤቶቼ አላችሁን ልል ነው እገረ መንገዴንም እንኳን አደረሳችሁ ልል? „አለን ደህና ነሽ ግቢ“ አሉኝ። ልጆች አሉን ስል ቀጥዬ ጠዬቅሁኝ። እነሱ ረበሹሽ ይሉኛል እዬተሳቀቁ እኔ ደግሞ የቤተ ክርስትያን ማህሌት የመስማት ያህል ደስ ይለኛል ልጆች ሲጫወቱ ሳዳመጥ። ልጆቼ ናቸው አትሳቀቀሙ እላቸዋለሁኝ - አዘውትሬ። ጥያቄዬ ቀጠለ ትላንት ነበራችሁ? „ቤት ውስጥ ነበርን። ምናው አንኳኩተሽ ነበርን፤ አልሰማነሽም አሉኝ“ ሲሉ ጠዬቁኝ። ቀልጠፍ ብዬ አላንኳኳሁም ድምፃችሁ ስለጠፋብኝ ነው። „የስልክ ደወል እንኳን አለሰማሁም አልኳቸው።“ የእማ ዝምታ ነገር ሰውንም አደበኛ ነው እምታደርገው አብሶ እንዲህ የዓውዳ ዓመት ሰሞናት ጭር ነው። ዝጉም ሁለት ቀን። ዛሬም ጥር 2 ቀን 2019 ነው ሥራ የለም በገዳማዊቷ ሰፈር ከሆስፒታል እና ከድንገተኛ ክሊንኮች በሰተቀር ሱቁ ሁሉ ዝግ ነው።  ·        ጉዳይ - ለማዕልቲ። ዛሬ እንደ ጉዳይ እማነሳው የዛለአንበሳ ጉዳይ ነው። ጉዳዩ ከጠቅላላው የኢትዮ ኤርትራ ከባድመ ጉዳይ ጋር በአንድም በሌላም የሚገናኝበት መስመር ቢኖርም፤ የአሁን የደንበሩ ጉዳይ ግን ለብርቱ ልባም ጥንቃቄ ነው ብዬ ነው የማስበው።