ነገረ ዛለአንበሳ፤ ነገረ አልበሽር እና ዕድምታው

ነገረ የዛለአንበሳ 
       እና
      ዕድምታው
እንደ ሥርጉተ ዕይታ።
„ብዙ መከራ የተቀበለ ሰው ብዙ ትምህርት ይማራል።“
መጽሐፈ ሲራክ ፴፩ ቁጥር ፲፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02.01.2019
ከእማ ዝምታ - ተሲዊዝ



·       እንደ መግቢያ።

እንዴት አላችሁልኝ ቅኖቹ። ዝምታው ቀጥሏል። እሰከ ረፋዱ ድረስ የመኪና ጩኸት እንኳን አልሰማሁም። ኳኳ - ኳኳ  አደረኩኝ - በቀስታ፤ ደወሉን አልጫንም። በእጄ ነው እማንኳኳው።

ጉዳዬ ለጎረቤቶቼ አላችሁን ልል ነው እገረ መንገዴንም እንኳን አደረሳችሁ ልል? „አለን ደህና ነሽ ግቢ“ አሉኝ። ልጆች አሉን ስል ቀጥዬ ጠዬቅሁኝ። እነሱ ረበሹሽ ይሉኛል እዬተሳቀቁ እኔ ደግሞ የቤተ ክርስትያን ማህሌት የመስማት ያህል ደስ ይለኛል ልጆች ሲጫወቱ ሳዳመጥ። ልጆቼ ናቸው አትሳቀቀሙ እላቸዋለሁኝ - አዘውትሬ።

ጥያቄዬ ቀጠለ ትላንት ነበራችሁ? „ቤት ውስጥ ነበርን። ምናው አንኳኩተሽ ነበርን፤ አልሰማነሽም አሉኝ“ ሲሉ ጠዬቁኝ። ቀልጠፍ ብዬ አላንኳኳሁም ድምፃችሁ ስለጠፋብኝ ነው። „የስልክ ደወል እንኳን አለሰማሁም አልኳቸው።“ የእማ ዝምታ ነገር ሰውንም አደበኛ ነው እምታደርገው አብሶ እንዲህ የዓውዳ ዓመት ሰሞናት ጭር ነው። ዝጉም ሁለት ቀን። ዛሬም ጥር 2 ቀን 2019 ነው ሥራ የለም በገዳማዊቷ ሰፈር ከሆስፒታል እና ከድንገተኛ ክሊንኮች በሰተቀር ሱቁ ሁሉ ዝግ ነው። 

·       ጉዳይ - ለማዕልቲ።

ዛሬ እንደ ጉዳይ እማነሳው የዛለአንበሳ ጉዳይ ነው። ጉዳዩ ከጠቅላላው የኢትዮ ኤርትራ ከባድመ ጉዳይ ጋር በአንድም በሌላም የሚገናኝበት መስመር ቢኖርም፤ የአሁን የደንበሩ ጉዳይ ግን ለብርቱ ልባም ጥንቃቄ ነው ብዬ ነው የማስበው። በይፋ የህውሃት ሊቃናት የውጭ ጣልቃ ገብ አለበት ሲሉ የቋጠሩትን ተርተር ማድረጊያ ነበር። ሌላም የሱዳን ህዝብ እና ልበሽር ነፍሳችን ሲባልም ሌላም ዱላ ለኤርትራ ተልኮላታል። 

ለደህነንቱ ሰው ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ይህ ጠረን ግልጥ ነው። ካርታ ላይ ተቀምጦ ይፈተሻል፤ ይበረበራል፤ ይተነተናል። በሌላ በኩል የሌላ የከፍተኛ መኮነን የግድያ ሙከራም ሌላው ፓለቲካዊ ዕድምታ ነው። ቀጣዩ የት ላይ ሊያነጣጠር እንደሚችል ደወሉ አይጠፋም ለብልህ ፖለቲካ። 

ሌላው ሰው ያለነሳው ጉዳይ የአቶ ዳውድ ኢብሳ እና የህውሃት የጫጉላ ሽርሽር ለኤርትራ መንግሥት ምቾት አይሰጠም። ጓዳውን በጥልቀት የሚያውቁት አቶ ዳውድ ኢብሳ ከመቀሌው መንግሥት ጋር ፍቅር በፍቅር መሆን ኤርትራ ዓይን የመሸንቆርያህል ስለሆን እንዲህ በችልታ የሚታይ ጉዳይ አይደለም።

የአቶ ዳውድ ኢብሳ በግልጥ እና የጃውርውያን በስውር መንገድ የአብይን ካቤን ማሸመድመድ ህልም ማስፈጸሚያ መናህሪያ ብትኖር ዛሬ ትግራይ ናት። የአብይ ካቢኔ አከርካሪ ለመስበር እንደ አጋር የታዬው የህውሃት መሳፍንቶች ሴራ በመቀሌ ነው።

ኤርትራ ደግሞ የአብይ ካቢኔ መንፈሷን የመለሰ ድንግ ፍቅር በገፍ የቀለባት፤ በቅንነት ጥገት በቃኝ እስትል ድርስ ያከሰከሳት፤ መታመንን በአፍ በአፏ በእጥፍ ድርብ ያጎረሳት፤ ጤናዋን የመለሰላት ጤናዳማ መተባይ ከቶም በሌለበት በክብር ያቀመጣለት፤ የተዘጋውን የዓለም መንግሥታት እቃባ በጥበብ የገላገላት፤ የዓለም ሚዲያ አብነት ያደረጋት፤ ለሽልማት ያበቃት የተስፋዋ አንባ ነው።

ስለዚህ በሁለት በተጣመረ ቢላዋ ይህን ካቢኔ ለመዘረር የተነሱ ዳውዳውያን፤ ጃዋርውያን ከህውሃት ጋር መደመር የራሷ ጉዳይ ነው ለእትጌ ኤርትራ። ምክንያቱም ሁለቱን በአንድ ላይ ለማንጠፍ የተሰናዳ መዶሻ ሞሆኑን ተመክሯዋ ይነግራታል። ለዚህም ነበር የተጋሩ ሊቃናት አፈጸጻም ላይ ወርደው ሌላ ነገር ሲመዛዙ ብልሁ ከቁንጮው በመነሳት በድፍረት ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ያለመውን በፍቅር ያዋዋለው።

ኦነግ ዘህውሃት የኢትዮ ኤርትራን ስምምነት እንደገና ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት ሌላው ስልታቸውን መቀያሳቸው አይቀሬ ነው። በስል ገብተው ለመነቅነቅ። የግጭቱ መንስኤ ቦታ ደግሞ ባድመ ነው። ባድመ ደግሞ በህውሃት ማንፌስቶ ማህበርተኞች እኛ እንጂ ሌላ ሊወስነበት አይገባም ባዮች ናቸው። 

ስለዚህ የአልጀርሱ ስምምነት ሂደትን ለማጠልሽት በዚህም በዚያም ልክ ጅጅጋ፤ ደቡብ፤ ቤንሻንጉል፤ ጭልጋ ላይ እንደሠሩት ሴራ ሰርገው በመፈጸም በአብይ ካቤኔ እና በኤርትራ መንግሥት የማፈራቀቅ የጥርጣሬ አዬር ሽውታ ለመፍጠር አይተኟትም። በጣምራ።

የኤርትራን መንግሥትን በኩዴታ፤ በብክል፤ ኢትጵያ ላይ እንደሞከሩት የማያደርጉበት ምንም ምክንያት የለም። በሌላ በኩል ለኤርትራ ህዝብ ልዩ ልዩ ጥሪ የመቀሌው መንግሥት በተደጋጋሚ ሲያቀርብ ከራርሟል። ይህም ሌላ ጥሪ አለበት።

ከቻልን አንድ ሆነን የወል ጠላታችን አማራ እና ኦሮሞን እንዘርር ካልቻልን ደግሞ ትግራይ ትግርኝ ለመመስረት እንቅፋት የሆነውን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን በትረ ስልጣን ተባብረን እናበርክክ ነው። በጎረቤት ሱዳንም የህዝብ አመጸ ነበር ከሰሞናቱ። አሁን እንኳን ህዝባዊ ታገድሎው ተገላግሏል። ይህም ሌላ የስጋት ቀጠና ነው ለኤርትራ መንግሥት፤ ባይሳካለትም ከዚህ ቀደም ህውሃት ሳይሞክር ይቀራል ተብሎ አይታሰብም።
 ያ አልሳካ ሲል ነው በነበረው ተቀባይነት ሉላዊውን መንፈስ ያሸፈተው በኤርትራ ላይ እራሱ ህውሃት ነው። „የወጋ ቢረሳ የተወጋ“። 

ህውሃት እራሱ የሚመራው መንግሥት ኤርትራ ላይ ከተፈጠረ የ100 ዓመት ህልሙ ዳግሚያ ትንሳኤ ይሆናል። ይህ ደግሞ ለኤርትራ መንግሥት አይጠፋውም። ልብ ለልብ ለመገናኘት ይህ ትውልድ ቢያልፍም አይመጣም በታምር ያ ምኞት የትግራይ ትግርኝ አገር። ዓለምን ፊቱ እንዲያዞር ያደረገ የፖለቲካ ተጋድሎ በዚህ በግርግር ገጠመኝ እንዲህ በቀላል ለድርድር የሚቀርብ አይሆንም። 

ወደ ቀደመው ምልስት ሳደርግ ወጣቶች የኤርትራ ንቅል ብለው ነው ወደ ኢትዮጵያ የጎረፉት። ቀጣዩ ደግሞ መቃብሩ ህውሃት እንደ ለመደበት አቶ ጌታቸው አሰፋን የመሰለ በኬጂቢ በሲአኤ ሳይቀር ደማቅ ዕውቅና ያለው አቅመኛ ይህን ፈንቃይ ቡድን አዘጋጅቶ ኤርትራ አስርጎ በመስገባት መነቀነቅ ሆነ ህዝባዊ አመጽ ማስነሳት አይቀሬ ነው። 

እንቅልፍ የለም አሁን መቀሌ ላይ ሁለቱም መወገድ አለባቸው ተብሎ ተሰልቷል። ለዚህም ነው ከኦነግ ሠራዊት ጋር እነ ታገሩ አብረው የነበሩት። ለዚህ ለጣማራ ተልዕኮ መሰናዶ።
ህውሃት በደመነፍስ የሚጓዝ ድርጅት አይደለም። በር ሲዘጋ በመስኮት፤ መስኮት ሲዘጋ በጣሪያ፤ ጣሪያ ሲዘጋ በምድር እንደ ተፈጥሮው መቆፈር አመል ነው።

ልምዱም ተመክሮውም ደግሞ የግራ ርዕዮት ነው። የግራ ርዕዮት ደግሞ አውቀን እንተው ካላሉ በዛ የተመረቁት የፖለቲካ ሊቀ ሊሂቃን ሁሉ ኢንትሪግ የሚሰለጠንበት ሙያ ነው። ግራ መቆሚያው ፒላሩ ኢንትሪግ ነው።

ስለዚህ እትጌ ኤርትራ ጣምራውን ህልሟን ከጨዋታ ውጭ ያደረጋትን አቅም ለማክሸፍ ነገረ ዛላአንበሳን እንዲህ በመቁንን ማድረግ የህልውናዋ ጉዳይ ነው። ሙሉ ለሙሉ ተዘጋም አይደለም እንደ ዘገባው ፍንጭ - ፍተሻው ጠንከር አለ ነው።

ልቅ ነበር። ልቅነቱ የኤርትራ መንግሥት ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ለሰጠው ክብር እና ፍቅር ሲባል ነበር። ለውጥን ለራበን ደግሞ የኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ ሰላም መሆን አንድ ተጨማሪ አፒታይዘር ነው። ይህ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ዙሪያ ግድያው ኩዴታው ሁሉ የከሸፈበት ዋነኛው ሚስጢር የኤርትራ እጅ ስለሌበት ነው። ይህንም ፖለቲከኞች ሲያነሱት ሰምቼ አላውቅም። በጣም የውስጥ ሰላም እማገኝበት ፍሬ ነገር ቢኖር ይህ ነው። ስጋት የለብኝም።

የኤርትራ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር የፈጠረው ሰላም አንድ ለውጡን መሰረት ያስያዘ ትልቅ አምክንዮ ነው። ሞተርም ነው። ብዙ ሳቦታጆች እና ሴራዎች ናቸው አከርካሪያቸው የተመታው። የግልቢያ ጉዞ አልነበረም። የልብ ለልቡ ሃዲድ በመዘርጋቱ የአብይን ነፍስ አቆይቶልናል። ለለውጡም ትልቅ መከታ ሆኖልናል። ለዚህም ፈጣሪያቸነን አብዘተን እናመሰግናለን። 

ጠ/ሚር አብይ አህመድ የመጀመሪያው የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ደህንነት የነበራቸው ህሊናዊነት እና ታማኝነት እሳቸው አንድ ነገር ከሚሆኑብኝ እኔ ባልፍ ይሻል ነበር ብለው ነበር የነገሩን ስሜን አሜሪካ በነበረው ጉብኝታቸው። ህውሃትም አያርፍም ነበር። ኦነጋውያንም እንደዚሁ።

የሚገርመው ኦነጋውያን አሁን እነሱ የበሉበትን ወጪት ሰባሪ ሆነው እዬታዬ ነው - ለኤርትራው መንግሥት ለጉሮሯቸው እና ለመጠጊያቸው። ሙልጭ አድርገው ክደውታል። ለአሁኑ ከተገባው በላይ መንጠራራት እና መፏለልም የተገኘው ከዛ ስለነበሩ ነው። እርግጥ ነው የኢትዮጵያ መንግሥት ሆነ የውስጥ መስመራቸው ለእነሱ ከተገባው በላይ መንጠራራት ጉልህ ድርሻ አብርክቷል።

የሆነ ሆኖ ያው አማፂ በሚለው ፈሊጥ እንጂ አንድም የሉላዊ ሚዲያ ስማቸውን ሲያነሳው ተደምጦ አይታወቅም ነበር አቶ ዳውድ ኢብሳን። አሁን በቢቢስ ወግ ደርሷቸው የጦር አዣዣቸውን ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ብቻ አሁን ከኤርትራ አንጡራ የመንፈስ ጠላት ጋር እንዲህ እነ ኦነጋውያን የፍቅር ጽዋ ሲያነሱ ላይ ሌላ አዲስ ጥቅረሻማ ታሪክን ኦነጋውያን ያጎናጽፋል። መታመን ሲርቅ ድልም አብሮ ይራቆታል። 

ከሁሉ በላይ የኢትዮ ኤርትራ ሰላምነት ዋነኛ ተጠቃሚው አማራው ነው። በዚህ ላይ ብዙ ጽፌአለሁኝ። በኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት ላይ ቀደም ባለው ጊዜ አንዳንዳን ያልተገቡ ነገሮችን እያንጠለጡሉ የሚጽፉ ጋዜጠኞች ነበሩ። ለነገሩ ልምዱም ዕድሜውም ተመክሮውም ያን ያህል ስለነበረ ገለባ ገለባውን ነበር ሲገሰግሱ የነበሩት እንጂ በኢትዮ ኤርትራ ሰላም መሆን አብሶ ጎንደር፤ ከጎንደርም ስሜን ጎንደር ልዩ ሐሴቱ ነው። ልዑል እግዚአብሄር ከሰማይ የወረደ ነው የሚመስለኝ እኔ ይህን ሳስብ። እምቆስልባቸው በርካታ ጉዳዮች ስለነበሩ። 

ከፋኝ ያለው ሁሉ እዛ እዬሄደ ይመሽጋል፤ በግራ በቀኝ ጎንደር ለ50 ዓመት ነደደች። የነደደችው በመዋለ ሃብታት ብቻ አይደለም በትወልድም ጭምር ነው ብክን ብላ ወና ሆነ የቀረቸው። ለግለግ ብሎ የወጣ ትውልድ የላትም - ጎንደር። የኤርትራ መንግሥት ከትግራይ ጋር ግንኙነቱ በልክ ቢሆን አማራ በበዛ ሁኔታ ይጠቀማል። በጣም ነው የሚጠቀመው።  የአማራ መንፈስ ገዢ መሬት ላይ ይሆናል። ረቂቅ ነው። 

በአንድ ቃለ ምልልስ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ እንዳሉት ግንኙነቱ ጎንደር ወደ ኤርትራ ያደላ ነው። ወሎም እንዲሁ። አብሶ ጎንደር የበለጠ ግንኙነቱ ከኤርትራ ጋር ጠንካራ ነበር። እነ አባባ እረፍት የሚሄዱት በጋ ላይ ኤርትራ ነው የነበረው።

ሌላው በዚህ አዲስ ግንኙነት የንግድ እንቅስቃሴ ከፍ ማለቱን በተለያዬ ዜና አዳምጬ ነበር ደንበር አካባቢ። ንግድ ጥሩ ነው። ኤኮኖሚ አልባ ፖለቲካ የለም። ነገር ግን ከሁሉም በላይ ህልውና ይበልጣል። ለኤርትራም ለኢትዮጵያም፤ ከኢትዮጵያ መንግሥትም ለአማራ ህዝብ ይህ የመንፈሱ መሪጊያ ጉዳይ ነው። የመቀሌውን ምንግሥት መታበይን እግረ መንገዱን መልክ ያስይዛል።

ሌላው ጥሬ እቃው ከመላ ኢትዮጵያ ተጭኖ ምርቱ ደግሞ ተመልሶ በውድ ዋጋ ይቸበቸባል። ኢፌርት ካለ ጥሬ ዕቃ ካለ የገብያ ማሳ ሃሳቡ ባዶ ነው። ይህን ተሸክማ የኖረችው ኢትዮጵያ እዬተኮረኮመች በበዛ ጭነታዊ ቀንበር ነበር። አሁን የኤፈርት ቀንበር ኤርትራ ላይ ለማራገፍ ሃሳቡ ሰፊ ነበር። አሰብ ወደብን ጨምሮ ቁምጥ የተባለበት ወሳኝ ጉዳይ ነበር። 

ህውሃቶች ከታላቋ ትግራይ ህልም ውጪ ሃሳብ የላቸውም። የሚገረመው እነሱ የኢትዮ ኤርትራን ሰላማዊ ግንኙነት ሳይሆን ትግራይ እና የኤርትራን ሰላማዊ ግንኙነት ብቻ ነው የሚመኙት። ግን የጉም ሽንት ህልም ነው።

ሰው ሁልጊዜ አይሳሳትም። ለወግ አብቅቷቸዋል ሻብያ። ከአቅማቸው፤ ከወረዳቸው ከብቃታቸው በላይ ሁሉንም ዕድል የሸላማቸው ሻብያ ነበር። የረባ ውጊያ እንኳን አላደረጉም ነበር እነሱ ከኢትዮጵያ ሠራዊት ጋር። ወደ ማህል ጉዞም የነበረው የኢህዴን ጦር ተጋድሎ በተጨማሪም ኢሠፓ ውስጥ የነበረው ኢንትሪግ ነው ለድል ያበቃቸው።  

ብቻ ረጅሙ ጦርነት ኤርትራ ምድር ላይ የነበረው። ነፍሳቸውን አውጥተው የመጣል ይህል ነበር ክህደታቸው ለሻብያ። አሁን ሁሉን ሆነው እንዳሻቸው እስከ ልጅ ልጆቻቸው በኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት ፈንጭተው ጊዜው ሲያልቅባቸው ደግሞ ፈለጓት ኤርትራን ለዛውም የኢሳያሳን ካቢኔ አይደለም። እሱን ጥለው ሌላ ነው ምኞታቸው። 

እዛውም ተወካዮቻቸው አሉ ከፕሬዚዳንቱ ቢሮ። ብቻ በል ገብቶ ብልህነት ልባቸውን ጎመደው። ሌላው የትግራይ የኢንደስትሪ ፓርኩ እና የአሰብ ወደብ መከፈት ለትግራይ መሳፍንታት የኢኮኖሚም የፖለቲካም የመታበይ ቁልል አንባ ነበር። 

ጠቅላላ የዛላንበሳ የደንበር ሁኔታ በልክ መሆኑ ለኢትዮጵያ መንግሥት ትንፋሹን እንዲሰበሰብ ቢያግዘው እንጂ የሚጎዳው አይሆን። አሁን ላይ ለአብይ ካቢኔም ኤርትራ መንግሥት ደጀኑ ነው። ለለውጡ ለራሱ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ካቢኔ መቀጠሉ ይጠቅማል። በሂደት ዘለግ ያለው የፖለቲካ ትርፍ ሲሰላ ደግሞ ምስባክም ሊኖር ይችላል። አደቡ ከተገኜ። የተሻሉ በርካታ ፍሬ ነገሮች ይኖራሉ። 

የአብይ ካቤኔን በጅዋጅዊት ለመጣል ለሚተጉት ለህዝቃኤላውያን፤ ለጃዋርውያን፤ ለዳውዳውያን፤ ለማህበረ ህውሃት ይህ የዛለ - አንበሳ ጉዳይ በልክ መመጠኑ እትጌ ኤርትራ ይህን መወሰኗ እንጥሽት ውቸውን ነው የሚያፈሰው።

ሚዲያ ሁሉ ከፍተዋል እኮ እዛ ኦነጎች። አሁን የቀረው የቅማንት ሚዲያ ብቻ ነው። ለቅማንትን የአቶ ጃዋር ሚዲያ በስፋት ሽፋን እዬሰጠው ነው። ይህን በጣምራ የክሽፈት ጉዞ ሲደመጥ የአቶ ንጉሱ ጥላሁን ከቤተ መንግሥታቸው አስነስቶ አቶ ጃዋር መሃመድን ለመቀበል አዲስ አበባ ድረስ ያስጓዘው ዕድምታ ፍቺው የተገኘ ይመሰለኛል። ሸር ጉዱም ባክኖ ቢና ጢናው ወጥቷል።  


ለቅድስት ኦርቶዶክስ ብጹዕን አልተደረገም ያ እርምጃ። "ሁሉንም ፈትሹ የሚጠቅመውን ምረጡ" ነው ቃለ ወንጌልም የሚለው። በሁለት ግንባር የኤርትራ መንግሥትን ሰላም በመንሳት፤ የአብይ መንግስትን ሰላም በማሳጠት ለሚያሴሩ የሴራ ማህበርተኞች የሃሳብ የመሸጋገሪያ ድልድያቸው ሙት መሬት ላይ ነው የተነጠፈው በዚህ በዛለ አንበሳ የደንበር መቁንነት ድንገተኛ ውሳኔ።

 ሌላው መረሳት የሌለበት ጉዳይ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድም በሙያ ደረጃ የደህንነት ሰዎች ናቸው። ይህን ሰው አስቦት አያውቅም። ይህ በራሱ ቀመሩ የአቶ ዳውድ ኢብሳ እና የህውሃትን አዲስ የማተራመስ መርሃ ግብር የመደርመስ ዘመቻ ይመሰለኛል እራሱ የሁለቱ መንግሥት ዝምታ የመንፈስ ፈንጅ ነው። መረጃው አልተዝረከረከም። ቀዳዳ አልከፈተም። ልባም ፖለቲከኞች እንዲህ ናቸው። ማሸነፍ ሚስጢር መጠበቅ ነው።

በዚህ ማህል ያለው የህዝብ ለህዝቡ የፍቅር ግንኙነት ነው። ይኸው እኛ የትም ሆነን ፍቅርን ለአገራችን እንቀልባለን። ስለዚህ ሁሉም በያለበት የሴራው ድር መልክ ይዞ በቁጥጥር ስር እስኪውል ወይንም ነጥሮ ወጥቶ ራሱን እንደ መንግሥት ይፋዊ ዕወጃ የትግራይ መሳፍንታት እስኪያደርጉ ድረስ፤ ወይንም የተሻሉ ሰውኛ ሰዎች እንደ ጅጅጋው እንደ አፋሩ የህውሃትን ወንበር እሲከረከቡ ድረስ እርጋን  እዮባዊነትን ሰንቆ መጠበቅ ነው። 

ለነገሩ „ የገነባት አገር ካለከበረችን የምታከበረን አገር እንገነባለን“ እኮ ተብለናል። መቀመጣሉ ቅልጣኑ በዛ። ኢትዮጵያ ለማለት እንኳን አይደፍሯትም። እሷ ለእነሱ ያደረገችውስ? ተዘርዝሮ ያልቃልን ብራናው ይበቃዋልን? ተሸክማቸው ነው የኖረች። በቁሟ ዘነዘናዋ መቅረቱ ይሆን የተገነባችበት ሚስጢር ወይንስ ልጇቿ ዘር እንዳያአፈሩ  በሽቦ ፍዳቸውን መብላታቸው። ወይንስ አካላቸው በግፍ መዘልዘሉ።

ሁሉም ይሆናል። የአዬር በረራ አለ ኢትዮ ኤርትራ ለመገናኘት። ሌላው አስደሳቹ ነገር አሰብ ላይ የተሰራው ጥበብ ልክ እን ጅጅጋው ነው። የአፋር የፖለቲካ ድርጅት እና መንግሥት ኢትዮጵያን ውስጧ ያደረጉ ቅኔያዊት ክብርት ወ/ሮ አሻ መሃመድ ነው አሁን የሚመሩት። 

ስለዚህ አሰብ ላይ የነበረው የህውሃት ማንፌሰቶም ግብዕቱ ስለተፈጸመ አፋር ለተሟላ የነፃነት ተጋድሎውን መንፈሱን ከአብይ ካቢኔ ጋር ማድረጉ ልብ ልክ ነው። በጎንም ስኩኑ የዶር ኮንቴ ሙሳ እርጋታ አለ። እኔ በተለዬ ሁኔታ ነው አምወዳቸው ዶር ኮንቴን ሙሳን። እላፊ አይሄዱም። ስክን ያሉ ናቸው። በአንድም በሌላም አያስከፉነም። ቁጥብ ፖለቲከኞች እኔ ግጥሜ ነው። ስለምን አንጀታችን የሚቆስልበትን መስመር ስለማይከተሉ። በዛ ላይ አክሰሱ ላላቸው ታዳጊዎችም ህሊና መልካም ነው ጠንቃቃ መሆን።  

የኤርትራ ኢትዮጵያ ጉዳይም በዚህ በተቀደሰው መሰመር ይከወናል ። የሚቀደመው የባድመ ጉዳይ ሳይሆን የእትጌ ኤርትራ የህልውና ሰላሟ ጉዳይ ስለሆነ አሁን እንደ ቀደመው በመያዣነት ለሁሉም የፖለቲካ ፍላጎት መረብ የነበረው የነገረ ባድመ ጉዳይ 
ለፕ / ኢሳያስ አፈወርቂ አመዛኙ የልቅና ጥበብ የሚጣፋቸው አይመሰለኝም።

እንደ ህውሃት የተደገመበት ይመስል እንደሚያብትተው፤ ጠበልም እርጫ እርጫ እንደሚያስፈልገው መሽቶ በነጋ ቁጥር „ህገ መንግሥቱ ተጣሰ“ አቡነ ዘመሰማያት እንደሆነው የሚሆን አይመሰለኝም ነገረ ባድመ ለኤርትራ መንግሥት። ከወትሮው በተለዬ በፍጹም ጥበብ የሚካንበት ይመስለኛል። በዚህ የሰላም ጉዞ እትጌ ኤርትራ ያተረፈችው የመንፈስ ሃብት ተዘርዝሮ አያልቅም። ትውልድን በፍቅር ማገናኘት። ትፍስህትም ጸጋም ነው።

ማህበረ ህውሃት በግንባራቸው ላይ „ህገ መንግሥቱ ተጣሰን“ ቢወቀሩት እንመክራለን። ሰውም እያነበበው እዬደገመው እንደ ድርሳን ውሎ እንዲያድርላቸው። የኤርትራ መንግሥት ግን ነገረ ባድመን ሚስጢሩን የደረሰበት ይመሰለኛል። ብልህነትም ይኸው ነው። ብቃትም ይኸው ነው። መሪነት ጥበብ እና መቅደምን ሲሆንበት ያረካኛል፤፡

ሐሴትን ማግኘት የቻለበት ዘመን የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ መንፈስ ይህ ዘመን ይመሰለኛል። ባለፈው ጅማም ጉንደርም ባህርዳርም ላይ ሳያቸው ኮብለዋል አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ወዛቸው ግጥም ብሏል። እኔ እውነት ተናጋሪ ብባል ሳቃቸውን አላውቀውም ነበር። አሁን ግን ፍልቅልቅ ነው ያሉት።

ሌላው ከልብ ሊደመጥ የሚገባው በኽረ ጉዳይ ዶር አብይ አህመድ የፖለቲካ ነጋዴ አለመሆናቸው ነው። ቅንነታቸው እራሱ ደንበር የለውም። ሰው ማመናቸውም ልክ አልተሰራለትም። 

ይህን እሳቸው በተለያዩ ጊዜ ጠ/ሚር ከመሆናቸው በፊት ያስተላለፏቸውን ንግግሮች ውስጥ ብተመረመሩት ታገኙታላችሁ። የተለዬ ሰናይ ገጽ እና ልቦና ነው ያላቸው። መንፈሳቸው ጤናማ ነው። እዩት ከዚህ ላይ ገፃቸውን፤ የቢሮ አደረጃጃታቸውን፤ የፍካታቸውን መጠን ጠቅላላ የዝግጅቱን ሁኔታ ስትቃኙት እሳቸውን በመንፈሳቸው ውስጥ ሆናችሁ ማዬት ትችላላችሁ ... 

https://www.youtube.com/watch?v=RLBOF9AO0Aw&t=447s

ባለቅኔው ጠ/ሚር ዶር አብይ አህመድ አዎንታዊ ምናበኛ ናቸው። በጣም ብዙ ነገራቸው ይመስጠኛል። ቅን ሰው እወዳለሁኝ እኔ። ለኤርትራም ህዝብ የሚመኙት በኢትዮጵያ ልክ መልካሙን ሁሉ ነው። ብሩኽ ናቸው። ኢትዮጵያ ከቀስት ትድን ዘንድ ልዑክ ናቸው ዶር አብይ አህመድ

ለእኔ ባለፈው ዓመት እንደጻፍኩት ብሄራዊ ቀኔ ናቸው። የፖለቲካ ሊሂቅ ሆኖ ቅን ሰው ማግኘት ታምር ነው ለእኔ። ስፈልገው ሰመኘው ስሻው የነበረ ጉዳይ ነው …  

  • ዘመነ አልበሽር እና ዕድማታው።

ሌላው ከዚህ ጋር ተያይዞ ላነሳው እምሻ ዘመነ አልበሽር የመምሸት ነገር - ጉዳይ ሌላው የህውሃት ማንፌስቶ የሞት ዜና ነው። ስንት ድንኳን እንደሚጣል አላውቅም መቀሌ ላይ። የሬሳ ሃሳብም መገነዣ ቹቻ - ሰኔል  - ሳጥንም እንዲሁ … የሚሊዮን ህዝብ ዕንባ እዛ ባዶ 6 የተከዘኑት መከረኞች ዕንባ ሌላም ሌላም ያመጣል። የሁሉንም ነገር ግፍ ካሳ ከፋይ ፈጣሪ አለና።

Sudanese opposition groups issue declaration for regime change
WEDNESDAY 2 JANUARY 2019

እርግጥ አንድ አዲስ የመንግሥት ለውጥ ሲመጣ ለሁሉም እኩል ነው የሚሆነው። ምን አቋም እንደሚከተል ስለማይታወቅ። ነገር ግን አፍሪካን አንድ ለማድረግ ለሚተጋው ለአብይ መንፈስ መደናገጥ የሚፈጥር አይሆንም።

የኢትዮ ሱዳን ግንኙነት ሲበራ እና ሲደበዝዝ ዘመን ቢያሰቆጥርም አሁን ባለው ቅንኛ መንፈስ ግን አዲሱ ለውጥ ቀጠናውን ሰላማዊ ለማድረግ የአያያዝ ጥበብ ስላለው ብዙም የሚገደው አይሆንም። የደቡብ ሱዳን እና የስሜን ሱዳንም ጉዳይ እልባት ያገኝ ይሆናል። ይህል ሌላ የፖለቲካ ትርፍ ነው ለቀጣናው። "ቸር ተመኝ ቸር እንድታገኝ።" መቀሌ ግን „ሎንግ ሊብ አልበሸር“ ባለ ወር ባለሞላ ጊዜ ውስጥ እንዲህ እና እንዲያ መሆን እጅግ የፈጣሪ ጥበብ ለኢትዮጵያ ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ ያሳያል። ጸሎት ይረዳል።


ሌላ ጉዳይ የአቶ ዳውድ ኢብሳ እና ዶር ደብረጽዮንን ያጋባው ሚስጢር ጸረ ኢትዮጵያ ፍልስፍና ነው። በኢትዮጵያ ይቀኑባትል። ዶር ለማ መገርሳ ይሁኑ ዶር አብይ አህመድም እንዲህ ፍዳቸው የጠናው ኢትዮጵያን ማክበራቸው ብቻ ነው።

https://www.youtube.com/watch?v=2b9-2qocMsc

Ethiopia - Dr Abiy Ahimed ትፈርሳለህ እንጂ ኢትዮጵያ አትፈርስም HASAB MEDA


የሆነ ሆኖ ህውሃት ዘንድሮ በለስ አልቀናውም። ትዕቢተኛው አቶ አባይ ወልዱ ያመጡት ጦስ ገናም መለመላ ያስቀራል። መለመላውን የቀረው ህውሃት ብቻ አይደለም ያን ትዕቢት የደገፉ ያበረታቱ እንደ ጸሐፊ አቶ አስራት አብርሃም ያሉትን ጨምሮ። 

ለዛውም ሰማዩ በዝምታ ስላለ ነው እንጂ ሰማዩ ደግሞ ቁጣ ከላከ ከለላም አይኖርም። ተከሳሽም አይኖርም። ቁጣው ምርኩዝን ለሰኔል ወይንም መታበይን እንደ ጥፋቱ የሚያስተነፍስም ይሆናል።

  • ህም!

ሌላው ግርም ያለኝ እዛ ያለው የኢትዮጵያ ሰራዊት ለቆ ለመውጣት ሲል በነዋሪዎቹ ታገደ መባሉ ነው። ህግ እዬጣሱ እኮ ነው ህገ መንግሥት ተጣሰ የሚሉት። አንድ የአገር ሠራዊት የራሱ ህግ፤ የራሱ አማራር፤ የራሱ  እዝ ሰንሰለት ራሱ የግዳጅ ፈሊጥ አለው። በሌላ በኩል ሠራዊት የማዕከላዊ መንግሥት እንጂ የአንድ ክልል በዚህ ሂድ በዚህ ተመለስ የሚለው አይደለም። ብቻ  የሰራዊቱ መኮንኖች ጥበብ ወድጀዋለሁኝ በእርጋታ መያዛቸው። ለነገሩ መረጃ አቀባዮች ከውስጥም ስርክራኪ አያጠፋም። ለሌላ ተጨማሪ መደራደሪያ። 

አንድ ነገር ተፈጥሮ ቢሆን ስሞታው አገር ምድሩን ያካልል ነበር ለሚሉት ወገኖች እንሱ እኮ ቀምጣሎች ናቸው። "የማይገርፉት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል፤ አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው" ነው የእነሱ ነገር። በዚህ ሲያፈርሱ ውለው ያድራሉ በዚህ ደግሞ ተነካን ይላሉ።

በጣም ዘመናዮች ናቸው። የትም ቦታ ህዝብ ይረሸን፤ ህዝብ ይጨፍጨፍ፤ ህዝብ ይራብ ይጠማ ጉዳያቸው አይደለም። ቅጭጭ አይላቸውም። ኦርቶዶክስ ስትደፈር እንኳን ጉዳያቸው አይደለም። አንዲት ነገር ብጣቂ የካብ ድርድር ከፈረሰ ግን ኡኡታ ነው። እኔ ኡኡታ በሆነ ባልሆነው ሲንኳኳ የማውቀው አሮጌ ቆርቆሮ ብቻ ነው።



የፈለገ ቢደረግላቸው አይረከሙ አይጠግቡምም። ቁልምጫው በልክ ማድረጉ ይበጃል። ይህም ነው እነሱን ልክ ያሳጣቸው። በድለውም፤ ገፍተውም፤ ወንጀለኛ ተባባረውም ስለ እነሱ እኛ እንጮኽላቸዋለን። እነሱ በጦፉ ቁጥር አብሮ መዝለል አይገባም።


የሰው ልጅ ለሰው ማዘን አለበት። በቀን 600 ወገን አፈር ለብሶ አፈር ሲሆን  ለእነሱ ጉዳያቸው አይደለም። የፍንድሻ ቀናቸው ነው። ተዉ ማለት ያባት ነው። 700 ሺህ በሳምንት ከቀዬው ሲፈናቀል ወርቅ እና ጨርቅ መታያ ነው። እምንጮኸው እኛ ለእነሱ ነው። እነሱ ግን ስለግፍ፤ ስለበደል፤ ስለ ዕንባ፤ ስለመገለለ ህዝባችን አገራችን ብለው አንዲት ሰከንድ በ27 ዓመት ሙሉ አብረውን አልቆሙም።


„ወንጀሎኞቼ አይነኩ፤ ገዳዮች አይነኩም፤ ዘራፈውም ወረራውም፤ ነዲዱም የተገባ ነው ባዮች ናቸው“ ግፍ የጥማት ማርኪያቸው ነው። የወያኔ ሃርነት ማንፌስቶ ወንጌላቸው እና ቁራናቸው ነው ያመልኩታልም።


እኛም አብዝተናዋል። በቁስላችን ላይ ሆነን ለእነሱ እንጨነቃለን እንጠበባለን። ይልቅ እኔ እምለው ከትግራይ ውጭ የሚኖሩ ንጹሃን ተጋሩ የመኖር መንፈሳቸው መታወክ የለበትም እንጂ እዛ ያሉት ሞትን፤ ፈንጅን እዬረገጠ ነው የአማራ እና  የኦሮሞ ወጣት በቃኝን አምጦ የወለደው። እነሱም ከክንብንናቸው ገለጥ ብለው ይፋለሙት የራሳቸውን አካል እና አምሳል - ነፃነት ከሳኛቸው።


እንደ በፊቱ መሳፍንቶቻቸው የሰውን ልጅ እንደ ብረት አቅልጠው ቀጥቅጠው እንደሚያፈርሱት ዘመን ግን ደግመው አያገኟትም። ሊሂቃኑ በሙሉ በዚህ መንፈስ ውስጥ ነው ያለው። ለማዘናጊያ ነው ህውሃትን ተቃዋሚ ነን የሚሉት። አንድ ዕጣ ነፍስ ቢኖሩ አቶ ገብረመድህን አርያ ብቻ ናቸው። የተረፈው ዘመድ ከዘመዱ ነው የበላይነቱን ይፈልጋሉ፤ ግፉም ይመቻቸዋል። የጓዳው ምክክር ይህ ነው።


የሆነ ሆኖ መከላከያ ሠራዊቱ ዛሬም ያ መታበይ ቀጥሎ መታገቱ የመታበዩን ጣሪያም አይቸበታለሁኝ። በአንጡራ ሃብት ደረጃ ኢትዮጵያ ከትግራይ ምን ይሆን የምታተርፈው? „ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል“ ይላሉ ጎንደሮች፤ ቅኖች ደግሞ ስላሉ እነሱን እንዳይከፋቸው እንዲሁ ሸብለል አድርጌ ልተዎው።



ሌላው የትግራይ እድገት እና የኤርትራ ዝቀተኛነት አብሮ ይነሳል። ይህ „የራሷ ሲያርባት የሰው ታመስላለች“ ይሆናል። በማያገባን ጉዳይ ጅዋጅዊት ባንጫወት መልካም ነው። የራሳችን ገመና እና ችግር እስኪ እንጨርሰው። ይህ አቅምን ስንበትን ውለን የምናድረውን ነገር እስኪ እናስታርቀው ነፃነት ከሚበለው የመኖር ህልውና ጋር። ምን ያህል የገዘፈ መከራ ፈጣሪ በጥበቡ እንገላገለን እራሱ አልገባንም። 

·       ሲጠቃለል።

 የዛለአንበሳ ጉዳይ በሚመለከት የኤርትራ መንግሥት መግለጫ አልሰጠም ሲባል አዳምጫለሁኝ። የኤርትራን መንግሥት አታውቁትም። ውሃ በቀጠነ እኮ ሚዲያ ላይ አይወጣም። በጣም አደብ የገዛ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥትም ይህን መከተሉ የተገባ ነው። መንግሥት ሁሉንም የመናገር ግዴታ የለበትም

በሌላ በኩል ይህ ጉዳይ ከብዙ ሁኔታ ጋር የተያዬዘ ነው። የዓለም ህዝብ ህሊና እኮ ሆኗል ሂደቱ። የኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ አጀንዳ በገዘፈ መልኩ በአብነት ደረጃ የሉላዊ ዓለም ጭንቅላት ሆኗል። ስለዚህ በግራ ቀኙ በጥንቃቄ መያዙ መልካም ነው። ወድጀዋለሁኝ። የሚሆነው ሁሉም ለመልካም ስለሆነ ተመችቶኛል። እራሱ የኤርትራ መንግሥት እንደ ቀደመው ጊዜ ባድመን‘ እንደ ትልቅ ኢሹ እንደማያደርገው ነው ለወደፊት። ስለምን? ለጥበብ!

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።  


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።