አሜሪካኖች „ምን እንርዳችሁ“ ማለታቸው ተደመጠ።
አሜሪካኖች የመከላከያ አቅማችሁን ለመገንባት „ምን እንርዳችሁ“ ማለታቸው ተደመጠ። ድንቅ ውበት። "የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል" ምሳሌ ፲፮ ቊጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 17.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · መነ ሻ። https://www.youtube.com/watch?v=h-tSeJBvBho #EBC እንደዘገባው። „ኢትዮጵያና አሜሪካ በወታደራዊው መስክ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ“ · መቅድም። ውዶቼ ጭብጡ ላይ አይደለም የእኔ ጉዳዬ። ጉዳዬ የአብይን ሌጋሲን ለማስቀጠል የአሜሪካ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት የሚገልጸውን ክፈል ብቻ ለማዬት ነው እምሻው። ስለዚህም በዚህ ዘገባው ውስጥ ቀልቤን የሳበው ታማኝነትን ለማስቀጠል ታማኝ ሆኖ መገኘት ስለመጠዬቁ ፍሬ ሃሳቡን ማግኘት ይቻላል። ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ በባዕለ ሲመታቸው ካደረጉት አንኳር ቀልብ ሳቢ ጉዳይ ላይ ስለሴቶች ያላቸው ልዩ ምልከታ፤ ውጭ ስለምንኖረው ኢትዮጰውያን ያላቸውን ናፍቆታዊ ራዕይ እንዲሁም በኢትዮ ኤርትራ የፍቅራዊነት ሂደት ላይ ያላቸውን የተስፋ ጥሪ ገልጠው ነበር። ይህን ሦስት ማዕቀፍ አትኩሮት የሰጠ ልዑክ ነው አገረ አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የላከው። አሜሪካን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵውያን ፈቅደው እና ወደው አዲሱን የኢትዮጵያ የተስፋ በር በክብር ጥሪ አድርገውለት አቀባበሉን በአማረ እና በሰመረ ሁኔታ ከውነውታል። ይህ ደግሞ ፈሶ አለመቅረቱን ነው የዛሬ መረጃ የሚጠቁመን። በሌላ...