ልጥፎች

ከኦገስት 17, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የቧልት ብልት!

ምስል
የቧልት ብልት! „እውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል?               ወተትን ለተው ወይስ ጡት ለጣሉ ነውን?“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፰ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 17.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። መፈራረጃ እንደ በር፤ ይግርሙኛል የሰሞኗቱ ጉዳዮቹ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ለውጡ እንዳይቅለበስ ምንትሶ ቅብጥርሶ ይሉናል … የተፎካካሪ ፓርቲዎች ደግሞ ለውጡን ስለማስቀጠል ይነግሩናል፤ የለውጡ መሪ መንፈሱ የት አለና ለውጡ የሚቀጥለውስ የሚቀድመውስ?   ቁልጭ ያለው ዕውነት እኮ አንጃው እና ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቀልብሶ በምስል እየተፍነሸነሸ ነው። ለወያኔ ቧልት ደግሞ እጅ ነሺዎች ሆናናል። ደጅ ጠኚዎችም። አሁን እውነት ጠፍቷቸው ነው ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ለውጡ እንዳይቀለበስ ምንትሱ ቅብጥሮሶ የሚለኑ? እንዴት ነው ማተብ የሚባል፤ ኪዳን የሚባል የለምን? ቅደስት ተዋህዶም ቤተክርስትያኔ ስቃይ ውስጥ ናት እና የህግ ጥበቃ አልተደረገለኝም እያለች ነው። ያው ያተራመሰው ወያኔው ስለሆነ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ አቤቱታው ወደ መቀሌ ቢላክ መልካም ነው። ወይ ደግሞ ለእነ ሳጅን በርከት ስምዖን ጁንታዎች፤ እዛው ቤተ መንግሥት አዲስ ሴራ ላይ ለተጠመዱት ለእነሱ ቢሆን ይሻላል። አባ ቅንዬማ ካቴና ውስጥ ናቸው፤  ወዱቼ አዱኛዎቼ ጥቂት በምልስት እና በቅኝት አብረን እንሁን እላለሁኝ ...  ቧልቱን በብልት በብልቱ ለማየት እነዚህ ሊንኮች በሚመለከት የቤት ሥራ ልስጣችሁ እና እዩዋቸው - ጥያቄ ግን በትሁት መንፈስ ነው። ነፃነት የተቀማው አንበሳ በሁለት ሳምንት ውስጥ ስንት ተግባራትን መከውን ሲችል አስረው ይዘው ፍዳውን ያስከፍሉታል።  እሱን ለምስል ልክ እንደ

የጸጋ ስግደት ለሳጅን በረከት ስምዖን የሴራ መረብ¡

ምስል
እንቀኛኝ። „በዚያ ቀን ይህ ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘመራል፣--- የጸናች ከተማ አለችን፤ ለቅጥር እና ለምሽግ  መዳህኒት ይኖርበታል“ ከሥርጉተ©ሥላሴ 17.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።                 የነፃነት ፍላጎታችን ሆነ መሰናዷችን በዚህ                         የቢሮ አያያዝ ይታያል።                       ¡ እናምራለን አይደል? ¡   ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንድምን አላችሁልኝ። መቼም  የእኔን ጹሁፍ የምትከታተሉ ቢያንስ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ይሆናል ብዬ አስባለሁኝ ስለ አብይ ሌጋሲ የሞት ፍርድ ሆነ እገታ። እና አሁን ባልታወቅ መንገድ ላይ ስለመሆናችን። ለነገሩ የሳጅን በረከት መንፈስ ድል ላይ ነው ያለው … ትንሽ ገጭ ገው የነበረው ከጃውርውያን ነበር እሱም በክስምት እንደ ክስምት … ·       ወያኔ ይውደቅ እንጂ … ይህ በነፃነት ፈላጊው „ ወያኔ ይውደቅ“ እንጂ ሌላው ችግር የለውም እራስን ሳይደራጁ፤ ሳይሰናዱ መንበር ላይ የማስቀመጥ እንደ አንድ አይዲኦሎጂ የተወሰደ ጉዳይ ነበር።  አንድ የበሰለ ንድፈ ሃሳብ ወይንም አንድ የጠነከረ የመንፈስ አቅም፤ ወይንም አንድ ሶሊድ የሆነ አካል ሳይኖር ነው ወያኔ ስለመወድቁ ብቻ እንሰበው ሌላው ገብስ ነው የጅሎችን ሞቶ ተሸከም የኖርነው።  ሊቃናቱ የፖለቲካዎቹ ማለቴ ነው ላም እረኛ ምን አለ ብለው ጆዋራቸውን ነካክቷቸውም አያውቅም። ሊቆቹ እነሱው ብቻ ናቸው። ሌላው ደግሞ ዱዱማ … ዱዳም ፤ ስለሆነም ነው „ወያኔ ይውደቅ እንጂ“ ሌላው ምንም አይደለም ሳይሆን ምንም እንዳይሆን ምን መሰናዶ አለ ቢባል አንዲት ቀን ሰብሰብ ይሉና የሽግግር ሰነዱ ይሄውና ነው። ወይንም ደግሞ ከ እከሌ ድርጅት ጋር እንዲህ የ