የተጋድሎ አመክንዮ ምን ይርበዋል?
የዛሬ የተጋድሎ አመክንዮ የተቃኜበት የፀጋዬ ራዲዮ መሰናዶ ይህን ይመስል ነበር። ላይፍ ላይ ላልተከታተላችሁ ቅኖች። ሁለት እርማት አለኝ ወጣቱ ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ተለቋል እኔ መታፈኑን ነበር የዘገብኩት። መሰናዶው ቀድሞ ተሰናድቶ ስለሚላክ። ሌላው አቶ ታገሰ ጫፎን አቶ «ታደሰ ጫፎ» እያልኩ ሰርቸዋለሁኝ። ለግድፈቴ ይቅርታ እጠይቃለሁኝ። ታደሰ የሚለው ሥም ሁልጊዜ ከአፌ ይገባል። ጭካኔያቸው ወደ ሰባዕዊነት ይቀዬር ይሆን፧ ከሌሎች ሚዲያወች የተለዬ አቅጣጫ ስለምከተል፤ አሰልቺ የሆነ ድግግሞሽ የለበትም። የጸጋዬን ራዲዮ ለዬት የሚያደርገውም ይኽ ለዬት ያለው ተፈጥሮው ነው። የዘገዬሁት የአሳቻው ጠቅላይሚር ወግ እስኪሰክን ነበር። ማለፊያ መሰናዶ ነበር። ትጨምራላችሁ እንጂ የምታጡት ነገር አይኖርም። https://www.lora.ch/programm/alle-sendungen?list=Tsegaye አርኬብ ላይ ለማድመጥ ለምትሹ ደግሞ ሊንኩ ይህ ነው። ምሽቱ አጽናኝ እንዲሆን እመኛለሁ። ደህና አምሹ፣ ደህና እደሩልኝ። አሜን። አክባሪያችሁ።