ልጥፎች

ከኦገስት 2, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዓለም ዓቀፍ #ሸላሚ ድርጅቶች ይህን ትጋት፤ ደግነት በትህትና ልግስና በትዕግሥት የደግነት ተግባር ሲጎመራ ምን ያደርጉ ይሆን???

ምስል
  ዓለም ዓቀፍ #ሸላሚ ድርጅቶች ይህን ትጋት፤ ደግነት በትህትና ልግስና በትዕግሥት የደግነት ተግባር ሲጎመራ ምን ያደርጉ ይሆን???   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)          ለትውልድ የሆነ #መሰጠት ። ለአደራ ያበቃ #አጽናኝነት ። ባለ አሻራ #አይዟችሁባይነት ። ድንቅ - የሚያስቀና - የሚመስጥ ሰብዕና። ዕጣ ነፍስ #በይቻላል መንፈስ ችግርን የመጋፈጥ ልዩ ተጋድሎ። አንድ መጸሐፍ ይወጣዋል። የፕለይ ፀሐፊወች ይህን የዕውነተኛ ታሪክ ጭብጥ ትዘሉት ይሆን???   የእዮር #መሰጠት ። ዓለም ዓቀፍ ሸላሚ ድርጅቶች አሜሪካ እና ካናዳ ያሉትም የኢትዮጵውያን ተቋማትም ይህን ብቃት #ባሊህ ይሉት ይሆን ወይንስ #ያገሉት ??? እምናዬው ይሆናል።   አብነትትነት ይህ ነው። #አሻራ ይህ ነው። የአገር #ካስማነት ይህ ነው። #የትውልድ መሆን ይህ ነው። #ሰዋዊነት ይህ ነው። #ተፈጥሯዊነት ይህ ነው።     እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መክሊት ይዞ ይወለዳል። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #ጥሪ ይዞ ይወለዳል። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መልዕክት ይዞ ይወለዳል እላለሁ። መፃህፍቶቼ ላይም አበክሬ እገልፀዋለሁ። ይህ ጥሪ፤ ይህ ለደግነት ፖስተኝነት፤ ይህ ችግርን ተቋቁሞ ለመፍትሄው የመምራት የማስተዳደር ብቃት እንዳይሰወር ስለምሰጋ ነበር እንደዛ እምተጋው።    እንዲህ በጥሪ ልክ ሆኖ መገኜት #መታደልም - #መመረቅም - #መሰጠትም ነው። አንድ ሰው ይህን ያህል ችግርን የመቋቋም አቅም ከዬት አገኜ? #ከእዮር #አደባባይ ። #ቅንነት የሰራው #ደግነት ነው።    ሁሉም ለአንዱ ፦...

አማራ ሆይ!

  አማራ ሆይ! አማራጭ ፈልግ። የዛሬ 8 ወር የነገርኩህ እዬሆነ ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02/08/2021   ሰውዬው አትሌቶችን እንኳን ደስ አላችሁ ይላሉ። ይህ ጥሩ ነው። አይከፋም እርድ ላይ ላሉ ወገኖች ግን ሽሽት ላይ ናቸው ምን ይሻላል? ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02/08/2021  መሪ አልባ ነበልባል የሆነ፣ ቋያ የሆነ ብሔራዊ ስሜት መዳረሻው የት ይሆን? ጭምት ሊቃናት፣ ከዬትኛውም ድርጅት ጋር ያልነበራችሁ ደናግላን እባካችሁ ተለመኑን? ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.08.2021   ንዴት ናችሁ። እምዬስ? ማንም ይሁን ማንም ኢትዮጵያን ከሰረቀ አክ ሊባል ይገባል። እሺ። ደህና ዋሉልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02/08/2021  

#አመድ አፋሹ አማራ … መጨረሻህ ናፈቀኝ …02/08/2021

  #አመድ አፋሹ አማራ … መጨረሻህ ናፈቀኝ … ከአቶ ሳልማን ማህመድ ፔጅ የተገኜ። ውዶቼ ዛሬ ከተለመደው ውጪ ነው እምሳተፈው። ባለመቻል። የሆነ ሆኖ የምችለውን ማድረግም መልካም ነው።   አቶ ሳልማን እንዲህ ይሉናል። ሳልማን የእሷ ፍቅር የሚባሉ ወዳጅ ነበሩኝ እኒህ አዲስ ናቸው፣ አፋርኛ ሥም ነው …… "እነሆ ጀግንነት. . . ከሃራ እስከ አላዉሃ ያልተነገረለት ግድል _ የህወሓት ወራሪዎች ራያ ቆቦ ወረዳን በሸፍጥ ከተቆጣጠሩ በኋላ ያቀኑት ወደ ሀብሩ ወረዳ ነበር። እዛ ደግሞ የሚጠብቃቸው ሽርጣሙ ፣ ረመጡ ፣ ባለ አንድ እግራው የሀብሩ ሶዶማዎች ነው። የሃራ እና አከባቢው ህዝብ ጠላት እየመጣ መሆኑ መረጃ ሲደረሰው ፈፅሞ ከተማውን ጥሎ አልሸሸም ፣ ከተማውን ድረስ እስኪመጡም አልጠበቀም ፣ የመከላከያንም ሆነ የአማራ ልዩ ሀይልን እርዳታ አልጠየቀም. . . .   ይልቁንም ከተማውን ከከባድ መሳሪያ ድብደባ እራሱንም ከባርነት ለማትረፍ የውጊያ ቀጠናውን ከሀራ ከተማ ወደ ሰሜን 3 km ወጣ ብሎ ቦታ ይዞ ጠበቃቸው እንጂ። - ""ታሪክን ይሰሩታል እንጂ አምጠው አይወልዱትም"" እንዲሉ ሃራን ለመያዝ የመጣውን #ሁለት_ሻለቃ የጠላት ጦር በሶስት ቀን ውጊያ አፈር አበሉት።    ይህኔ ሃራን መያዝ ጉም እንደመጨበጥ የሆነበት የጠላት ሀይል ወደ ሃራ ሊያደርገው የነበረውን መስፋፋት በመተው ወደ አላውሃ ፈረጠጠ ጀግኖቹ ግን ጠላት ሸሸ ብለው ወደ ቤታቸው አልተመለሱም ይልቁንም እግር በእግር ተከትለው አላውሃ አከባቢ ሲደርስ አጋዥ ሀይል ያገኘው ፈርጣጭ የልብ'ልብ ተሰምቶት ፍርጠጣውን አቁሞ ፊቱን አዙሮ አንድ እግራዎቹን ገጠመ እንደ ሀራ ሁሉ አላውሃም ጠላትን ከዳችው የሞተው ሞቶ የቀረው ጠላት ""ወዲ ሽርጣም አይተኻአለን...