ልጥፎች

ከጃንዋሪ 29, 2020 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ጁቪተር ላይ ይሆን የሚኖሩት? (ጠና ያለ ሙገት)

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። የተመላላሹ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ   እልፍኝ - ጁቢተር ይሆን? የመሪነት ኃላፊነቱስ አዳራሽ አዳሽነት ይሆን - ይሆን?! (ሙግት)   „አንተ ምን ጥቅም አለህ ---- ? ኃጢያት ሠርቼ ከማገኘው ይልቅ፤   ኃጢያት ባልሠራ ኑሮ ምን እጠቀማለሁ? ብለህ ጠይቃኃልን።“ (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ 35 ቁጥር 3) ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። 28.01.2020 ·        ጠ ብታ። እንዴት ናችሁ ቅኔዎቹ የአገሬ ሃብቶች። አልኳችሁ ቀኑ ውሽክ ብሏል። ምን ይደረግ እንዲህ ዘመን ሰጥ ቀለጤ እና ቀበጤ ጠሚር ሲኖረን። በረከት ይባል መርገምት አይታወቅም። ይህ ጹሑፍ ታግቶ ቆዬ። ሁለት ሞጋች አመክንዮች ስለገጠሙኝ። አንደኛው „እኛን ውሰዱ እና እህቶቻችን መልሱልን“ የሚል የወጣት ወንዶች ርህርህና እስከ አጥንቴ ስለተሰማኝ ያን አስቀደምኩኝ። ሁለተኛው ደግሞ „ሳናውቅህ ስናውቅህ“ የሚል የመጸሐፍ ያህል ህሊናዬን ሞገተኝ በ28.01.2020 ከ30 በላይ በተለያዩ ከተሞች   በአማራ ክልል ከተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች የገዘፈ መልዕክት ሆኖ ስላገኘሁት እሱን አስከተልኩኝ። በእነኝህ ሁለት ጹሑፎች ምክንያት ይህኛው ጹሑፍ ማዕቀብ ተጥሎበት ቆዬ። እኔ የሲዊዝን ቀደም ባለው ጊዜ አውሮፓ ሰልፎች ሲካሄዱ ነበር እምዘግበው እንጂ የአገር ቤት ሰላማዊ ሰልፎችን አልዘግብም ነበር። ለዚህ የተሰማሩ መደበኛ አምደኛ ጦማርያን ነበሩ በቀደመው ጊዜ። አሁን ወደ አያቶቻችን ቀዬ ሳይሉ የቀሩም አይመስለኛም ብራና ላይ ብዙም አላያቸውም። ምንን እና ማንን ስንታገል እ...