ልጥፎች

ከጃንዩወሪ 25, 2020 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች /ከቢቢሲ የተጋራ/

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። „አቤቱ ሰውነቶቼን አሁንም ለአንተ ሰጠሁኝ።“ (መጽሐፈ ጦቢት ምዕራፍ 4 ቁጥር 12) ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 25.01.2020 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች   እንዴት ናችሁ ቅኔዎቹ የአገሬ ልጆች ደህና ናችሁ ወይ? እኔ ደህና ነኝ። ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ዛሬ ወሳኝ ነጥብ አንስቷል። ስለ አዲሱ ኮሮና በሽታ። ጤናችሁም፤ ደህንነታችሁም አጀንዳዬ ስለሆነ እነሆ ሼር አድርጌያለሁኝ። እናንተምስ ሳትደክሙ መልዕክቱን ሼር አድርጉት።   „በቻይናዋ ዉሃን ግዛት የተከሰው ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውጪ ወደ በርካታ አገራት እየተዛመተ ይገኛል። አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይዋን፣ አውስትራሊያ በሽታው መታየቱን ሪፖርት ካደረጉ አገራት መካከል ይገኙበታል። የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይዛመት እየወሰደ ስላለው እርምጃ እና ስለ ቫይረሱ የሚከተለውን መረጃ አስተላልፏል። ·        ኮሮና ቫይረስ ምንድነው ? የኮሮና ቫይረስ ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን ሞትን ሊያስከትል የሚችል ህመም ነው። የቫይረሱ   መተላለፊያ መንገዶች በሽታው ያለበት ሰው ሲያስነጥስ፣ ባልበሰሉ ምግቦች፣ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ ይተላለፋሉ። ·        የበሽታው ምልክቶች በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥ እና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይ