የዓድዋ ድል ሆይ #ይቅርበለን።
#የዓድዋ ድል ሆይ #ይቅርበለን ። እኛነታችን በግርማ፤ በሞገሥ ያላቀ፤ የእኛነታችን ንጥረ ነገር ለዓለም የገለጸ #ራዲዮሎጂያችን የዓድዋ ድላችን። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።" የዓድዋ ጥንካሬ፤ ብርታት፤ መንፈስ፤ ህይወት፤ አቅም እና ክህሎት #ዊዝደሙን አክሎ ከእኛ ጋር ይሁን። አሜን። አድዋ - ለእኔ፤ ዓድዋ - ለእኛ፤ ዓድዋ ለሁላችንም እኛነታችን የሰጠን፤ የማድረግ፤ የመሆን አቅማችን ለዓለም የገለጠ #ራዲዮሎጃችን ነው። እኛስ ለዓድዋ ድል ምን አደረግንለት? እኛስ ምን ለዓድዋ #ዕውነት ምን ሆንለት? በጎሳ፤ በዞግ ተከፋፍለን የድሉን አልማዛዊ ብርኃን #አደበዘዝንበት ። የስላቅ መደርደሪያ ካንፓስ ሆንበት። እኛ ለዓድዋ ለተፈጥሯዊ አቅሙ #እንቅፋት ሆንበት። ይህ እርግጥ እና ዕውነት ነው። የአድዋን ክብር እና ልዕልና አብዝተን ተዳፈርነው። አንድነትን ዓድዋ ሰጠን። እኛ ግን ለመቆራረጥ ህግ አርቅቀን አጽድቀን #በአንቀጽ 39 ስንፎክር እንገናኛለን። ጋዜጠኛ ሆኖ የአንቀጽ 39 ሞጋች ከመሆን በላይ ምን አሳፋሪስ፤ አንገት አስደፊ የታሪክ አሰርነት አለና? ኢትዮጵያ አጀንዳዬ አዬደለችም ማለትስ ከማን ከዬት የተወረሰ #ቋቁሻዊ ዕሳቤ ይሆን???? በውነቱ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ፤ ልካችን ሳናውቅ በዓድዋ ድል #ክብር ዕውቀት የአመራር ክህሎት፤ ልቅና እና ልዕልና ልክ መሆን ላልቻልን የስንፍና #ግዞተኞች እግዚአብሄር አምላክ ማህሪ ነውና ምህረቱን ይላክልን። አሜን??? በውነት ተሳስተናል። በውነትም ከዊዝደማችን ጋር ፈቅደን #ተካክደናል ። ፈጣሪ መርቆ ከሰጠን ከብልህነታችን ጋር ወደን #ተላልፈናል እና የዓድዋ ድል ሆይ! ይ...