ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዬተሞገቱበት። 15.11.2022
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዬተሞገቱበት። P 1/2/3 # የዛሬ ትናንት ዋዜማ። # ሁለት የውስጥነት አንስቶች እና የጠቅላይ ሚር አብይ ግሳፄ። " የቤትህ ቅናት በላኝ። " በጠቅላይ ሚር አብይ አሐመድ አሊ በሴት ሊቃናት መካከል በፍጽምና የሚያቀርቧቸው አሉ። እንዲሁም ለሟሟያ ዬሚዮዋቸውም አሉ። ዬህሊናቸው ያህል ወሮ ሙፍርያት ካሜል እስከ ምርጫ፤ ወ / ሮ አዳነች አበቤ እስከ ትናንት ዋዜማ። የአማራ ሊቃናት ጭፍጨፋ፤ የጦርነት መከራ እና የህወሃት ሊቃናት ብክነት ለደህዴን የጫጉሊ ጊዜ ነበር። ከራስ ፀጉራቸው በሥልጣን፤ በሹመት፤ በኮሚቴ መሪነት፤ በገላጭነት፤ በልዑክ አደራጅነት፤ በአብሮ ተጓዥነት፤ ለመሪያቸው ዕንባማዋ፤ ዬኖቬል ድግስ ዋና ሚዜ የልቤ የተባሉት፤ የምክትል ጠቅላይ ሚር ደረጃ የተሰጣቸው ነበሩ ወ / ሮ የሰላም ሚር ሙፍርያት ካሜል። በምርጫ የአደባባይ ሥርዓት ግን ታች ላይ የተወረወሩ። በሌላ በኩል ከጉምሩክ፤ አቃቢ ህግነት፤ ከአቃቢ ህግነት ወደ ታላቋ አዲስ አበባ ከንቲባነት የተሸጋገሩት ከንቲባ አዳነች አበቤም ሚስጥሬ፤ ዬልብ አድራሼ፤ መካቼ ይባሉ ነበር በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ። በዛሬው ጉባኤ መንትዮሻቸውን ወርፈዋቸዋል። ምክትል ከንቲባ ሁነው ለመስራት እንደተገደዱ ገልፀዋል። ሰሞኑን ሽልማቱም፤ ቅኔውም የተደረደረላቸው ወሮ አዳነች አበቤን ጎሸም አድርገዋቸዋል። ፋክክር መጣ ማለት ነው። በልጦ ብቅ አይፈቀድ ይሆን ? የሚወረውሩበት ቦታ ሲያጡ ሥም አያጡምም...