ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዬተሞገቱበት። 15.11.2022

 

ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዬተሞገቱበት።

 

P 1/2/3

 


#የዛሬ ትናንት ዋዜማ።

#ሁለት የውስጥነት አንስቶች እና የጠቅላይ ሚር አብይ ግሳፄ።

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

በጠቅላይ ሚር አብይ አሐመድ አሊ በሴት ሊቃናት መካከል በፍጽምና የሚያቀርቧቸው አሉ።

እንዲሁም ለሟሟያ ዬሚዮዋቸውም አሉ። ዬህሊናቸው ያህል ወሮ ሙፍርያት ካሜል እስከ ምርጫ፤

/ አዳነች አበቤ እስከ ትናንት ዋዜማ።

የአማራ ሊቃናት ጭፍጨፋ፤ የጦርነት መከራ እና የህወሃት ሊቃናት ብክነት ለደህዴን የጫጉሊ ጊዜ ነበር። ከራስ ፀጉራቸው በሥልጣን፤ በሹመት፤ በኮሚቴ መሪነት፤ በገላጭነት፤ በልዑክ አደራጅነት፤ በአብሮ ተጓዥነት፤ ለመሪያቸው ዕንባማዋ፤ ዬኖቬል ድግስ ዋና ሚዜ የልቤ የተባሉት፤ የምክትል ጠቅላይ ሚር ደረጃ የተሰጣቸው ነበሩ / የሰላም ሚር ሙፍርያት ካሜል። በምርጫ የአደባባይ ሥርዓት ግን ታች ላይ የተወረወሩ።

በሌላ በኩል ከጉምሩክ፤ አቃቢ ህግነት፤ ከአቃቢ ህግነት ወደ ታላቋ አዲስ አበባ ከንቲባነት የተሸጋገሩት ከንቲባ አዳነች አበቤም ሚስጥሬ፤ ዬልብ አድራሼ፤ መካቼ ይባሉ ነበር በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ።

በዛሬው ጉባኤ መንትዮሻቸውን ወርፈዋቸዋል። ምክትል ከንቲባ ሁነው ለመስራት እንደተገደዱ ገልፀዋል። ሰሞኑን ሽልማቱም፤ ቅኔውም የተደረደረላቸው ወሮ አዳነች አበቤን ጎሸም አድርገዋቸዋል። ፋክክር መጣ ማለት ነው። በልጦ ብቅ አይፈቀድ ይሆን?

የሚወረውሩበት ቦታ ሲያጡ ሥም አያጡምም የክህሎት ሚር ብለው በዲሞሽን የወሸቋቸውን አንደበተ ርትዑ / ሙፍርያት ካሜል "ሥራ አለ። ሠራተኛ አለ። ድልድዩን ማን ይሥራው?" ብለዋል ገስፀዋቸዋል። ደቡብማ አይሆኑ ሆኖ ተበትኗል። "……? በሬ ሆይ"

ዬሚዘልቅ ፍቅር የለም። የሚፀድቅ የግንኙነት ዬልብ ለልብ ሃዲድም የለም። ተተኪ ሲገኝ እንደ ቲም ገዱ ……

ነገም ደማቅ የህዝብ ተቀባይነትን ጥሶ አሸብሻቢ የሆነው ሁሉ ወዮ ነው???

/ ሙፍርያት ሁሉ አጀብ የለም። ክፍት ብሏቸውም አይቻለሁኝ። ጥቁርቁርም ብለዋል። ቀጣዩ ቀን ቀጣዩን ውሳኔ ይዳኛል።

ፎቶው ግን የቆዬውን መረጥኩትኝ። ለጠቅላይ ሚሩ ኖቬል ዕንባ ወረድ ወረድ ያደረጉበትን። ይመቻል አይደል???

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

15/11/2022

ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

"ዛሬን በአወንታዊ"

ዬዛሬው አንድ እጅ የፓርላማ ስብሰባ ሂደት አወንታዊው ጎኑ።

ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ውይይት ላይ የሚያሳዩት መወራጨት፤ ያልተገባ የእጅ እንቅስቃሴ የዓይነት ለውጥ አይቻለሁኝ። በሁለት ነገር ብቻ ነበር የተበሳጩት #በአዲስ አበባ ጥያቄ እና #የሽግግር መንግስት አስታከው ሲያቀርቡ። በተረፈ ስክን ብለው፤ ፕሮቶኮላቸውን ጠብቀው አይቻለሁኝ።

ይህን ስል እላፊ የሄዱበት፤ ዬድርጅታቸውን ሚስጢር የዘረገፋበት፤ ዬዘለሏቸውን ጥያቄወች፤ ያቃለሏቸውን አመክንዮወች አይደለም። እንደ አንድ መሪ ቦታውን የዬሚመጥን ሰብዕና፤ የንግግር ፍሰት የአካል እንቅስቃሴ በብዙ ልቅ ነበር። ዛሬ የተገራ ሁኔታ አይቻለሁ። ከውስጥም የመረጋጋት ሁኔታ በአንፃራዊነት አይቻለሁኝ። ዬተሻለ ኮንፊደንስም አስተውያለሁኝ።

እርግጥ ነው የወታደር አይነት የአቀማመጥ ሁኔታ አይቻለሁኝ። ብዙ ክፋ አይደለም። ዬጥያቄወቹ አቅጣጫወች ብሄራዊ፤ ካቢኔያዊ አይመስሉም። #የአብይ ጎዳና እና ስኬቱ ዓይነት ነው። ባይጎረብጥም በአንድ ሰው ላይ ዬተንጠለጠለ ተስፋ ሲታጣ ይናዳል። የቲም ወርክ ስኬት ብዙም አልሰማሁም በገለፃው። የሰብዕና ግንባታ ይመስላል አመላለሱ።

ዬሆነ ሆኖ ባነሷቸው ነጥቦች

1) ውጭ ዬሚኖሩ ፖለቲከኞች በሰኔት፤ በኮንግረንስ ተመርጣችሁ እስቲ እንያችሁ ያሉት ጥሩ ሃሳብ ነው። ቅን ሃሳብ ነው። እንደ መሪም ልክ ዬሆነ ዕይታ ነው።

2) ተማሪ ልጆችን በቀን ሁለት ጊዜ የመመገብ ፕሮጀክት። ከድንቅ በላይ ነው። ችግሩ ሲማሩ፤ ከተማሩ በኋላስ መብታቸውን የሚያስከብቅ ምን ፖሊሲ አለ? በዞግ ፖለቲካ አገር እዬተመራች? ለምሳሌ 12993 ተማሪወች ከፈተና ውጪ ሆነዋል።

ይህ የተጀመረውን መልካም ጉዞ ያቆስለዋል። ተማሪወችን ከብስጭታቸው አብርዶ ሊፈተኑ ዬሚችሉበት ዲስፕሊን አምጦ መውለድ ይጠይቃል። ተማሪወች እኛ አጥፍተናል አባታችን መንግሥት ግን ታግሶናል ላጠፋነው በሳምንት አንድ ቀን ከተማችን አጽድተን እንክሳለን የሚል የኃላፊነት እና የተጠያቂነት ስሜትን ሊማሩ የሚችሉበት መንገድ ተከርችሟል።

አንድ ተማሪ በቅርበት አምስት ሰወች ጋር ኮንታክት ቢኖረው ሲባዛ ወደ 64 ሺህ ሰው በትምህርት ሚር ጨካኝ እርምጃ ተጎድቷል። ይህን መዳኜት የጠቅላዩ ተግባር ነበር። ግን ትምህርት ሚር ኮበሌ፤ መንግሥትም ጎረምሳ ሆነ። አንድ የሃይማኖት አባትም አልተገኜም። የተገነባ እዬተናደ አዲስ መገንባት ጉም መጨበጥ ይሆናል።

3) መኖር ያቃታቸው እንደ ቤታቸው ሂደው የሚመገቡበት ሁኔታም መሰናዳቱ በውነቱ መንፈሳዊ ኃብት ነው። ያረካልም። ግብረ ሰላም፤ ዝክር ትውፊት ነው። የቆዬ የነበረ። ያን አስፍቶ ማስቀጠል ዓይነታ ተግባር ነው። በሥያሜ ላይ" የሌማት ትሩፋት " ይህን ሥም "ሌማት" የሚለውን የሚጠቀሙበት የወጣቶች የሙዚቃ ቲም አለ። መቀማት፤ መንጠቅ፤ አይገባም።

#ዬድሆን ትሩፋት፤ #ዬጥራር ትሩፋት፤ #የሙጎጎ ትሩፋት፤ #ዬቀለምሽሽ ትሩፋት፤ አማርኛ ቋንቋ ዲታ ነው። ስለዚህ እንደ ጎረምሳ የሌላውን ከመንጠቅ የራስን ማፍለቅ ይገባል። እነኝህ ወጣቶች ቀድመዋል። ኮፒራይቱ ሊጠበቅ ይገባል።

የጎርጎራ ፕሮጀክት የአትሌት ኃይሌ ነበር ቀድሞ የወጠነው። ገለፃውን ሰሙ በጠራራ ፀሐይ ነጠቁት። ከዛ በፊት ጎርጎራ ትዝ ብሎወት አያውቅም ነበር። ቆይቶም አዲስ ማንነት ይሰጠዋል። እንደ ኩታራ በአጥንት እንደሚጣላ። መልካም ነገሮች ሲታቀዱ ከሚያጠነዝላቸው ጉዳዮችም እራስን ማዳን ይገባል።

4) ዬውሃ ፕሮጀክት፤ የመስኖ ፕሮጀከት 100 ቀን ተግባራት ሰመራ ላይ ተናግረውት ነበር። ይህ ወደ ተግባር መለወጡ ያበረታታል። የጎንደር የውኃ ዬአንገረብ ግድብ ግን የቀደመ ፕሮጀክት ነው። የጉድጓድ ውሃም ድሮም ነበር።

የተሻለው ዘለግ አድርጎ ማሰብ፤ ከጣና መሳብ ፕሮጀክት ቢኖር መልካም ነው። አንገረብ፤ ቀኃ፤ ፈጭፋጭት አቅማቸው ውስን ነው። በጋ እንዲያውም የሉም። ይደርቃሉ። #ውኃ ስልጣኔ ነው። #ውሃ መዳህኒት ነው። #ውኃ ጤናም ነው። ጅምሩ ጥሩ ነው። ግን ሰፋ አድርጎ መጀመሩ የትውልድ ይሆናል። ቁንጣ ቁንጢው ቆሞ ማለት ነው። ይህን ስል መዋለ ንዋይ እንደሚጠይቅ አውቃለሁኝ። ጣና ይታሰብ እያልኩኝ ነው።

5) ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ በአፍሪካ ከገዘፋት ተርታ የ። እንደሆነች ተነግሯል። ከሆነ ያድርግላት። ኢንፍሌሽን እንደ ተባለው ዛሬ በኮረናም፤ በራሽያ እና በዩክሬን ጦርነትም ግሎባል ሆኗል።

በእያንዳንዳችንም ቤት ገብቷል። ኢትዮጵያ ላይ 5 ዓመት የዘለቀው የአማራ ህዝብ ጭፍጨፋ፤ የአማራ ተቋማት ውድመት እሱን ተከትለው የመጡ መፈናቀሎች ሁሉንም ደሃ አድርጓል።

አጣዬ፤ ደራ ስንት ጊዜ በኦነግ ተቃጠሉ፤ የባንኩ ዘረፋ፤ የሁለት ዓመቱ ጦርነት እና የተስፋ ውድመቱ፤ ድርቁ፤ ዝርፊያው፤ ሴራው፤ ጋር በውነትም ኢትዮጵያ ላይ መሽቶ መንጋቱ ይገርመኛል። የዋጋ ግሽፈቱን ተቋቁሞ ህዝቡ መኖሩ የሰማይ ታምር ነው።

6) አረንጓዴ አሻራው በተፈጥሮ ጥገኛ ነው። በደርግ ጊዜም ነበር። ማስቀጠሉ ጥሩ ነው። የግል ፕሮጀክት መሆኑ ግን አይገባም። የሩዝ ተከል ተነስቷል። ወረታ በዘመነ ደርግ የነበረ ፕሮጀክት ነው። ኮነሬል መንግሥቱ እራሳቸው ጎብኝተውታል። ኮርያኖች ነበሩ ዘምተው ያስጀመሩት። በእርስወ ዘመን አልተጀመረም።

ስንዴ፤ የተለያዩ ፍራፍሬወችም የነበሩ ናቸው። አደራጅቶ ማስቀጠሉ ካልሆነ አዲስ ነገር የለውም። ህዝብ ይበዛል። ዲጂታል ዓለም ላይ ነን። በነበረው ዘመን ዬነበረው ነበር። አሁን ጊዜ በሚፈቅደው ልክ መጓዝ ግዴታ ነው። የመንግሥት ሩትን ተግባርም ነው።

ቱሪዝም ላይም የነበረ ጉዳይ ነው። እንዲያውም ከጉዳዩ ዬማይመለከታቸው ምደባ ጋር ደብዝዞ ይታያል። በባህል፤ በኪነ ጥበብ ዝቅታ ላይ እንደተሆነ ይሰማኛል።

9) ኢንቬስተሩ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሆነው ይታዩኛል። በቀጥታ ንግድ ውስጥም ገብተዋል። አሳታፊ አይደሉም። የእንግዳ አያያዝ ተምሬያለሁ ብለዋል፤ የፕሮጀክት ሽሚያውንም ተግ ቢያደርጉት ጥሩ ነው። አሳታፊ ይሁን። የሚር መሥሪያ ቤቶች ይኑሩ አይኑሩ አይታወቅም።

ለመሆኑ ግብርና ሚር፤ ኮንስትራክሽን ሚር የሚባሉ አሏችሁን??? ተገላይ እና የውስጥ ካኒቲራ የሚር /ቤቶችን ዘወትር ስለማይ። ህግ እና መርህ ሳይሆን በጓኝነት በሻይ የቡና ፈክቶ አያለሁኝ።

9) ፍትህ ግን ዶር አብይ እርስወ እና ፍትህ ምን እና ምን ናችሁ? ዬሚሰጡት ሃሳብ ለዕለቱ ፕሮፋይል ብቻ ነው። ህግ እና ኢትዮጵያ አልተገናኙም። እርስወ ቲም ወርክ ላይ አይተጉም። ሲፈጽሙ ለምርቃን ለሪባን ቀለምሽሽ ሁኑልኝ ካልሆነ።

10) የቦንጋ ዩንቨርስቲ ተግባሩን አይቻለሁኝ። በደርግ ዘመን ልዩ ፍፁም ልዩ፤ ፖርሳ፤ ቀበቶ፤ የቁልፍ መያዣም ይሠራ ነበር። ነበረኝ። እጅግ ዘመናዊ በጣምም የሚያምር። ከዬትኛውም አገር ፖርሳ ዬሚያስንቅ። ዬት ደርሶ ይሆን? ዕፁብ የሆነ ጥበብ ነበር።

ይህን የማነሳው እርስወ በእርስወ ዘመን ብቻ የተፈጠረ ታምር አድርገው ስለሚያቀርቡት ነው። እንጨት ቦንጋ ብቻ ሳይሆን አርሲ ጢቾ አውራጃ ጠና ወረዳ ውስጥ ያለው ኃብትስ?

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

15/11/2022

ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

 

መቅድመ ዛሬ ከፖለቲካ አንፃር ተስፋነሽ። ወጣቷ "የብልጥጋና" ሞጋች።

"ምን ደስ ብሎኝ ባህላዊ ቀሚስ ልልበስ?"

(ታዳጊዋ የፓርላማ ተመራጭ እህት ተስፋትሁኔ።)

"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"

በዛሬው ዬጋዜጣዊ መግለጫ የፓርላማ ውሎ

ዬሴቶች ተሳትፎ የተሻለ ነበር።

ይህችን ወጣት ሳይ እራሴን አስታወስኩኝ።

በፖለቲካ የቀረፁኝ የፖለቲኪ ሊቀ ሊቃውንታት

ታወሰኙ። ትምጣ እና ግንባር ግንባራችን ትበለን እባል ነበር።

በፍቅር፤ በስስት ያዩኝ ነበር። ጭብጤን እንይዋጥብኝ

በማለት ሃሳቤን አንጠልጥዬ ወደ ተስፋሁኔ ልመለስ።

ይህቺ ወጣት ፕሮፌሰር ብርኃኑ ነጋ ትምህርት ሚር ሲመደቡም ሃሳብ አንስታ ነበር።

ዛሬም እጅግ መሳጭ #የመብት ፍልስፍና ይዛ ቀርባለች። እስኪ ይለመኑ በህይወተወት

አንድ ቀን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ። ሙግቷን ይቻሉ፥ መብቷ ይጠበቅላት።

ዬማትገኝም ናት። በዘመን ማህል እንዲህ ደፋሮች ብቅ ይላሉ። ተመስገን።

የአዲስ አበባ ተመራጭ ሆና ከንቲባዋን ማግኜት አይፈቀድም።

የፓርላማ አባል ሆና ሙሉ መረጃ አታገኝም። ይህ ዝበት ሊስተካከል

ይገባል።

ወሳኝ ነጥብ አንስታለች ምርጫ ላይ ዬፈተነን የፖለቲካ ድርጅት አለ።

ይህ ድርጅት የህዝብ ድጋፍ አለው። አብረን የምንሰራበት ሁኔታ

ይመቻችም ብላለች። ኢትዮ እስራኤላዊ የፓርላማ ተመራጭ የራሳቸውን

ፓርቲ ብቻቸውን ተሟግተው ፖሊሲ አስቀይረዋል። በኮረና ኬዝ።

በዚህች ወጣት ውስጥ ያዬሁት ዊዝደም አለ። እባካችሁ ተጠቀሙበት።

የአዲስ አበባን የማንነት አደጋም አንስታለች። ዕፁብ ዕይታ ነው።

አዲስ አበባ ከፍ ሲል #ግሎባል ማንነት፤ በማዕከላዊ በሆነ ሁኔታ #አህጉራዊ ማንነት፤

መሬተ ዬያዘብሄራዊ ማንነት አላት።

ከዚህ እንድትወርድ ሽሚያ አለ። ፕሮጀክቶችም የለኮፒራይት የታቀደ ኦፕሬሽን ነው።

የአዲስ አበባን ነባር ማንነት ነቅሎ አዲስ የመተካት። አሉታዊ ዴሞግራፊ።

ይህ አደጋው በግሎባል ደረጃ አልተሠራበትም እንጂ ቢሠራበት ብዙ አቅም መፍጠር በተቻለ።

በቃላት እርኩቻ የጎረምሳ ፖለቲካ ላይ ባይተኮር።

የጠቅላይ ሚር አብይ ስክነት፤ እርጋታ የሚፈትነው የአዲስ አበባ ጥያቄ ሲነሳ ነው።

ለምን? ስውር የውርስ ፖለቲካ ስላለበት። ነርብ ነውና። ሌላ ሰው ሆነው ቁጭ ይላሉ።

ሳያሳውቁ፤ ሳያስጠጡ ሁሉንም በፈርጅ በፈርጁ ከውነውታል ለኦነግ ገዳ አስመችተው።

ዛሬ አዲስ አበባ መግባት የገነት ያህል እሩቅ ነው። ነገ ከዛሬው ከርቤ ይሆናል። በቢዛም።

ይህ ግን በግርዶሽ ትርዒት የሚከወን ነው። ኢትዮጵያ በሚል የተሸበለለ #እንቆቆ

ስለሆነም ብስጭታቸው ዬዶር አብይ ከዛ ስለሚነሳ ነው። በሳቸው ህሊና አዲስ አበባ #የኦሮምያ ናት።

#አድርገዋታልም ሙሉ ደቡብም እንዲሁ። ለዚህ ነው ወደዛ ሲጓዙ አቶ ሽመልስ አብዲሳ

የልዑኩ አባል የሚሆኑት። ከውስጣችን እንከታተላለን።

ነገ የሰቲት ዕጣ ፈንታም አስጊ ነው። አንከርፍፈው የያዙትም ለዚያ ነው።

እያንከባለሉ ለመጠቅለል። እምቅ ጉድ ነው ያለው።

ጆኖሳይድን አዘምነው እንደሚፈጽሙት የገዳ ሥርዓትንም እያስኬዱት ነው። እያንዳዱ ኮቴያቸው ከዛ

ዕሳቤ ጋር የተቆረኜ ነው። ለዚህ ነው እኔ "ተረኝነት" እጭ ፖለቲካ ነው ዬምለው። ያለው የገዳ #መስፋፋት

ዬገዳ #ወረራ የገዳ #አስምሌሽን ዬገዳ #ዲስክርምኔሽን ነው የምለው። ከጫፋ ያልደረሰ ፖለቲካ

ለመፍትሄውም እሩቅ ነው።

ዬሆነ ሆኖ ጠቅላዩ ኢትዮጵያኒዝም አራማጅ ቢሆኑ ለዚህች ቀንበጥ ቁጭ ብድግ የሚያደርግ

የሐሴት ገጽ ይታይ ነበር። ይልቁንም ሚስጢር ዘርገፋዋል። ይህን እኔ ዓለምን ስሞግት ነበር።

በምርጫው ዕለት በሰላም እንዲከወን ቀድሞ ግብር የሰው፤ የከተሞች ተከፍሎበታል እልም ነበር።

ዛሬ ነገሩን "" "የብልጽግና አባል ባትሆኚ አትመረጭም ነበር። እጩ አድርጎ ያቀረበሽ "ብልጽግና"

ያስመረጠሽም "ብልጽግና" ነው" ብለዋል። " ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል።" ግን ደንግጫለሁኝ።

ዬወጣቷን በራስ የመተማመን መንፈስ ተፈታትኗል። ሥነ ልቦናዋን ለመጫን አቅሟን

ቅስም ለመስበር የተደረገው ሁሉ መራራ ነው። በሌላ በኩል ከህወሃት ጋር ግብግብ ግጥሚያ

ላይ ራሺያ፤ ቻይና በህዝብ የተመረጠ ህጋዊ መንግሥት እያሉ 13 የተመድ ጉባኤ የበተኑበት ትልቁ

የመንፈስ ተቋም አጋዩት በራሳቸው ዶር አብይ አህመድ።

ድርጅታቸው አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ የተሰራውን ድርጅታዊ ሥራ ገልፀዋል።

እያንዳንድህ ፓርላማ የገባህ "የብልጽግና" ተመራጭ አትንጠራራ ነው። አጣዬ፤ ሻሸመኔ፤ ዝዋይ የነደዱበት፤ ባህርዳር

በደም አላባ የታጠበችበት የአማራ ክልል ሲነሪቲ ያላቸው ሊቃናቷ ከእነ ቤተሰባቸው ዬተመተሩበት፤ የአብን እና ዬባልደራስ እስር፤

ቀውስ ተደራጅቶ ሺወች ዬተፈናቀሉበት፤ ዬሞቱበት በስጋት ውጥረት ህዝብ የተሰቃዬበት፤ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ህልፈት፤ በፍርኃት የራደ መንፈስ አስፍኖ እራስን ማስመረጥ ነበር። በጀርመንኛም ጽፌዋለሁኝ። ዛሬ አስኳሉን "የብልጽግናው" ፕሬዚዳንት ዶር አብዬ አህመድ ነገሩን። የምርጫ ቦርድ ተልዕኮም ምን እንደ ነበር ፍንትው አድርገው አሳዩን። ለነገሩ እኔ 2019 ዬጨነገፈ ብዬ ጽፌበታለሁኝ።

በፓርቲ ውስጥ ለሰራ ሰው የሞገድ ጋዜጣ ልበ ወለድ ታሪክ በኢትዮጵያ ድርጊት ላይ እንደዋለ ለሰባት ጊዜ ጽፌበታለሁኝ። አዲስ አበባ ህዝብ ያቀረበው እጩ፤ የመረጠው ተወካይ ዬለም ብለውናል። በእጃችን የሠራነው ነው ብለዋል። ተጠያቂነት እና ኃላፊነትስ??????

እህት ተስፋትሁኔ ግን ከዚህ በላይ ነገም፤ ከነገ በስቲያም ፀፀት የለባትም። ይህን ሳታደርጊ ተብላ ልትወቀስ አይገባም።

ደፋር፤ በእራስ የተማመነ አዳዲስ ሃሳብ አቅርባለች። ለእኔ ዕንቁ ናት። እባካችሁ እንዳታሸማቅቋት። በህይወቷ ላይ ዛቻ ሊደርስ ይችላል። ሰፊ የማፍያ ኔት ነው ያለው።

ሌላው የአፈ ጉባኤው ቁንጥንጥነት በዬትኛውም ዘመን ያላዬሁት አቅለ ቢስነት ነው። ስብሰባ እንዲህ አይመራም። የኢትዮጵያ ጉባኤ እንዲህ ባለ ቅለት አይሆንም። ኢትዮጵያ ልኳን አላገኜችም። ፈቀዱ። ዘነጠሉ። አስቆሙ።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

14/11/2022

ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።