#የአማራን ልጅ #ስለኢትዮጵያዊነት #ለማስተማር ማሰቡ እራሱ #የውርንጫ ድካም ነው። #መቅኗችን ኢትዮጵያችን ናት።
#የአማራን ልጅ #ስለኢትዮጵያዊነት #ለማስተማር ማሰቡ እራሱ #የውርንጫ ድካም ነው። #መቅኗችን ኢትዮጵያችን ናት። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፯ ክብሮቼ እንዴት አላችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። የአማራ ወላጅ #ዶክትሬኑ #ኢትዮጵያዊነት ነው። የትኛውም ቦታ አማራ ልጁን ሲያሳድግ ደቡብ ይሁን ሰሜን። ስሜን ይሁን ምዕራብ። ምዕራብ ይሁን ምስራቅ ስለፈላስፊት ኢትዮጵያ ቅንነት #መቅኗችን ፤ ካልሽየሙ አድርጎ፤ መልቲ ቫይታሚኑ፤ ፕሮቲኑ፤ ሚኒራሉ፤ ንጥረ ነገሩ አድርጎ ነው ልጁን በኢትዮጵያኒዝም የከበረ ልዑቅ በራስ የመተማመን ተፈጥሯዊ ሙሉ አቅም እና ክህሎት አንፆ የሚያሳድገው። የአማራ ህዝብ በመላ ኢትዮጵያ በተለይ በከተሞች በስፋት ይገኛል። መገኜቱ ብቻ አይደለም፤ አብሮነቱን በጋብቻው፤ በቁቡ፤ በእድሩ፤ በቤተ አምልኮ ባዕቱ፤ በሥራ እና በመኖሪያው ሁሉ በተባ ኢትዮጵያዊነት አለምልሞ ነው የሚኖረው። ተጋብቶ ተዋልዶ። ተዛምዶ ተጎራብቶ። ተዋህዶ ተስማምቶ። አሁን ከሆነም ውጭ አገርም በብዛት የአማራ ልጅ ይኖራል። የትም ይሁን የትም የአማራ ቅን ወላጅ የቅንነቱ መሠረት የሆነችውን ዩንቨርስ እናቱን ኢትዮጵያን የውስጥነቱ መገለጫ አድርጎ አስጠንቶ ነው የሚያሳድገው። ለዚህ እኮ ነው "የአማራ ……… ብሎ" ተደራጅቶ ኢትዮጵያዊነቱ ነግስ፤ የተነሳበትን ተልዕኮ ሳስቶ የሚታየው። ኢትዮጵያዊነት ለአማራ ህዝብ #እንደሬሰው ነው። ካፒቴኑ ነው። #የኖህ መርከቡም ነው። ይህ እንደ ባቢሎን ግንብ የሚናድ አይደለም። የታነጸበት ንጥረ ነገሩ ነው። እና ኢትዮጵያዊነትን ለአማራ ህዝብ ለማስተማር ማሰቡ በራሱ #የውርንጫ ድካም ነው...