ልጥፎች

ከሜይ 17, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ችግር መፍትሄው ግልጽነት ነው። ( የወግ ገበታ 17.05.2019)

ምስል

ለአላዛሯ ኢትዮጵያ መከራ መፍትሄው ግልጽነት ነው።

ምስል
ለአላዛሯ ኢትዮጵያ መከራ መፍትሄው ግልጽነት ነው። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 16.05.2019 ከእመ ዝምታ ሲወዘርላንድ ·        እፍታ። የትህትና ሙሉ ወርድ እና የአክብሮት ጃኖን የተጎናጸፈ ሰላምታዬ ይድራሳችሁ ቅኖቹ የአገሬ የኢትዮጵያ ልጆች? ደህና ናችሁ ወይ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ዛሬ ስለ ግልጽነት የሚሰማኝን መግለጽ ፈለግሁኝ። ስለ ግልጽነት ፍልስፍና አይደለም። ስለ ግልጽነት የምህንድስና ዝበት እና ክስረቱን ነው። ግድ ነው ዛሬ ስለ ግልጽነት ማንሳት። ምክንያቱም መከራው፤ ፍዳው የድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባን ቀጣይነት አሁንም እዬታወጀ ስለሆነ። እራሱ አሁንም መንፈሳችን ብክነት ላይ ነው። ሊሰከን አልተቻለውም። አንዱን አለፍነው ስንል ሌላው እዬተተካ … ይደቁሰናል። በድምጽ   https://www.youtube.com/watch?v=n_ffYPTo0VE&feature=youtu.be ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ችግር መፍትሄው ግልጽነት ነው። ( የወግ ገበታ 17.05.2019) ·        ውስጤ። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ በእኔ ዕድሜ ያለውን ማለትም የፖለቲካ ተሳትፎ ማድረግ ከጀመርኩበት ጊዜ እስካሁን ያለውን ውስጡን ስጎረጎረው ችግሩ የግልጽነት ጉዳይ ነው ብዬ አመንኩኝ። ሴራም፤ ሸርም፤ ተንኮልም የግልጽ አለመሆን ጥገኞች ናቸው። ግንዱ ግን ፖለቲካው የሚማገርበት ስውር ፍላጎት ነው። ዋናው የትውልዱ ብክነት መሰረታዊ ችግር የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቃን የአካሄድ ግልጽነት ከሚባለው ተፈጥሮ ጋር የተላለፉ ስለሆኑ