#ስለምን አዲስ አበባ እና ኦሮምያ ላይ ጥድፊያው ጠና???
#ስለምን አዲስ አበባ እና ኦሮምያ ላይ ጥድፊያው ጠና??? • https://sergute.blogspot.com/2019/12/blog-post.html ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም። - ዲሴምበር 16, 2019 ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም። ከዚያ የከበደ መከራ ላይ ናቸው አላዛሯ ኢትዮጵያም ሆነ እማማ አፍሪካም። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ዬኦህዴድ ኦነግ ሥርዕወ ዬኦሮምያን ልዩ ኃይል የፌድራሉን እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ልብስ አልብሶ አዲስ አበባን የማጥቃት ሂደት ጀምሯል ይባላል። ለእኔ አይደንቀኝም። ምክንያት ከ2011 መስከረም 5 ጀምሮ አዲስ አበባ በኦሮምያ ሥር ናት። የትግሉ ጭብጥ ከዚህ ይነሳ ብዬ ሳስተምር ባጅቻለሁ። መንበረ ፓትርያርኩ በኦሮምያ ክልል ስር ነው። ዲፕሎማት ማህበረሰብ በኦሮምያ ክልል ህግ ሥር ነው። ዓለም ዓቀፋ፣ አህጉር አቀፋ፣ ብሄራዊ ተቋማት ሁሉ በኦሮምያ ህገ መንግሥት ሥር ናቸው። ይህ ስላልገባው ፖለቲካው ሁልጊዜ ግጭት ላይ ነው። የፖለቲካ ትግሉ ዬለም። ባለቤትም ዬለውም። ሁልጊዜ ፓራሳይት ነው። ንቅናቄ ኮሽ ባለ ቁጥር እንደ ንብ ይሰፍርበታል። ዛሬ አይደለም መሰናዶው። ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር ፕላን ሰርቶ ነው። ሄሮድስ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ዬረጅም ጊዜ ህልማቸውን ፕላን ሠርተውለታል። ያን ነው የሚፈፅሙት። ዘመናዊ ዬገዳ ሞደሬተር ናቸው። አዲስ አበባ ዬእኛ ናት ያቅራቸዋል። ኢትዮጵያ ዬእኛ ናት ዛራቸውን ያስነሳዋል። ዬሚሹት ኦሮምያ ዬእኛ ናት አዲስ አበባም የኦሮምያ ናት እንዲባል ነው። ይህን የሚቀበል ይኖራል። ዬማይቀበል ግን ይጋዛል። ዬ...