#ስለምን አዲስ አበባ እና ኦሮምያ ላይ ጥድፊያው ጠና???
#ስለምን አዲስ አበባ እና ኦሮምያ ላይ ጥድፊያው ጠና???
• https://sergute.blogspot.com/2019/12/blog-post.html
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።
- ዲሴምበር 16, 2019
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም። ከዚያ የከበደ መከራ ላይ ናቸው አላዛሯ ኢትዮጵያም ሆነ እማማ አፍሪካም።
„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“
(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
ዬኦህዴድ ኦነግ ሥርዕወ ዬኦሮምያን ልዩ ኃይል የፌድራሉን እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ልብስ አልብሶ አዲስ አበባን የማጥቃት ሂደት ጀምሯል ይባላል።
ለእኔ አይደንቀኝም። ምክንያት ከ2011 መስከረም 5 ጀምሮ አዲስ አበባ በኦሮምያ ሥር ናት። የትግሉ ጭብጥ ከዚህ ይነሳ ብዬ ሳስተምር ባጅቻለሁ።
መንበረ ፓትርያርኩ በኦሮምያ ክልል ስር ነው። ዲፕሎማት ማህበረሰብ በኦሮምያ ክልል ህግ ሥር ነው። ዓለም ዓቀፋ፣ አህጉር አቀፋ፣ ብሄራዊ ተቋማት ሁሉ በኦሮምያ ህገ መንግሥት ሥር ናቸው።
ይህ ስላልገባው ፖለቲካው ሁልጊዜ ግጭት ላይ ነው። የፖለቲካ ትግሉ ዬለም። ባለቤትም ዬለውም። ሁልጊዜ ፓራሳይት ነው። ንቅናቄ ኮሽ ባለ ቁጥር እንደ ንብ ይሰፍርበታል።
ዛሬ አይደለም መሰናዶው። ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር ፕላን ሰርቶ ነው። ሄሮድስ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ዬረጅም ጊዜ ህልማቸውን ፕላን ሠርተውለታል። ያን ነው የሚፈፅሙት። ዘመናዊ ዬገዳ ሞደሬተር ናቸው።
አዲስ አበባ ዬእኛ ናት ያቅራቸዋል። ኢትዮጵያ ዬእኛ ናት ዛራቸውን ያስነሳዋል። ዬሚሹት ኦሮምያ ዬእኛ ናት አዲስ አበባም የኦሮምያ ናት እንዲባል ነው። ይህን የሚቀበል ይኖራል። ዬማይቀበል ግን ይጋዛል።
ዬዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ የገዳ ወረራ፤ ዬገዳ መስፋፋት፤ ዬገዳ አስምሌሽን እና ዲስክርምኔሽን ነው። በዚህ ምክንያት ነው የምታዩት ሁሉ ጭካኔ ዬምታዩት። ፖለቲከኞች፤ ጋዜጠኞች፤ ተንታኞች እኔን አይጨምርም ሻል ያሉት ተረኝነት ይሉታል። ሌሎቹ ግን ጉዞ ወደ አንድነት ይሉታል ማህበረ ግንቦት 7 // ማህበረ ኢሳት። ሁሉም አዛይ ነበር። መከራችን ያበራከተ።
ዕውነቱ ኦሮምያ የሚገዛው አገር ነው ያለን። ለኦሮምያ ህግ ደንብ የማይገዛ ማንኛውም ነገር ይጋዛል። ይወገዳል። ይመነጠራል። ዬእኔ ሃሳብ ገዢ ሆኖ እዬመጣ ነው። ለዚህ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁኝ። በሚሆነው ሁሉ አልደነግጥም። ምክንያት። ሊሆን የሚገባውን ጽፌያለሁ፤ አስተምሬያለሁ በሎቢም ተግቻለሁኝ። ላም እረኛ ምን አለን ማድመጥ የቅድስቷም፤ የፖለቲከኞችም ነበር።
ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል ግን አዲስ አበባ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ አይፈቀድም። ስለምን? አዲስ አበባ የገዳ ፖሊሲ ጥገኛ ስለሆነች።
መሸቢያ ቀን ውዶቼ። ደህና ዋሉልኝ።
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
15/02/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ