የመንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል፡ሂዩማን ራይትስ ዋች
"የመንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ላይ ጥቃት ፈጽመ ዋል፡ሂዩማን ራይትስ ዋች" የፎቶው ባለመብት, Amhara Health Bureau ከ 8 ሰአት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን በጤና ባለሙያዎች፣ በህሙማን እና በጤና ተቋማት ላይ ፈጽመዋል ሲል የመብት ተሟጋቹ ሂማን ራይትስ ዋች ከሰሰ። https://www.bbc.com/amharic/articles/c97832pz01mo "የመንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል፡ሂዩማን ራይትስ ዋች ታማሚ እና አስታማሚ" የፎቶው ባለመብት, Amhara Health Bureau ከ 8 ሰአት በፊት "የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን በጤና ባለሙያዎች፣ በህሙማን እና በጤና ተቋማት ላይ ፈጽመዋል ሲል የመብት ተሟጋቹ ሂማን ራይትስ ዋች ከሰሰ። አንድ ዓመት ሊሞላው በተቃረበው በአማራ ክልል በፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት፣ የመንግሥቱ ኃይሎች እና ተባባሪ ሚሊሻዎች በክልሉ የጤና ተቋማት ላይ ፈጽመዋቸዋል ያላቸውን ጥቃቶች በተመለከተ ሂዩማን ራይትስ ዋች ዝርዝር ሪፖርት አውጥቷል። ሪፖርቱ በክልሉ ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ካለፈው ዓመት ማብቂያ አንስቶ የመንግሥት ኃይሎች ቢያንስ 13 በሚደርሱ ከተሞች በጤና ተቋማት እና በሠራተኞች እንዲሁም በትራንስፖርት አገልግሎቶች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎችን ማሰባሰቡን አመልክቷል። የሂማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ላቲሺያ ባድር “የኢትዮጵያ ፌደራል ኃይሎች ለሰላማዊ ...