ደራሲ ባለቅኔና ዲፕሎማቱ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ

 

ደራሲ ባለቅኔና ዲፕሎማቱ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ
 May be an image of 1 person and textMay be an image of 1 person and text
 May be an image of 1 person and text
በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ታላቅና ግዙፍ አስተዋጽኦ ያላቸው ደራሲ፤ታሪክ አዋቂ፤የታወቁ ዲፕሎማት፤በቤተ ክህነት ትምህርትና በቋንቋ የተካኑ፤ ባለቅኔ፤ገጣሚ፤የዘመናቸውን ዕውቀት የቀሰሙ ምሁር፤ በአኗኗራቸው በምሳሌነት የሚታዩና ሠርተው የማይደክሙ ኢትዮጵያዊ ናቸው ፡፡እኒህ ሊቅ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ይባላሉ፡፡ ከአባታቸው ከአቶ ወልደ ሥላሴና ከእናታቸው ወይዘሮ ወለተ ማርያም ዜና የተወለዱት ግንቦት 1 ቀን 1871 ዓ ም በቀድሞ አጠራሩ በመርሐ ቤቴ አውራጃ በታች ቤት ወረዳ ረመሸት ቀበሌ ደን አቦ ገዳም በተባለ ሥፍራ ሲሆን ያረፉት ደግሞ መስከረም 9 ቀን 1931 ዓ ም እንግሊዝ አገር ባዝ በተባለው ቦታ በስደት ላይ እያሉ ነው:: ብላቴን ጌታ ኅሩይ ለቤተ ሰቦቻቸው የመጀመሪያ ልጅ ሲሆኑ አባትና እናታቸው ከእርሳቸው ቀጥሎ በተከታታይ ሁለት ሴት ልጆችን ወልደዋል። እንጦጦ ራጉኤል ደብር መጥተው የመጻሕፍትን ትርጓሜ በዘመኑ ከነበሩት የደብሩ ሊቃውንት ዘንድ ተምረዋል።
ብላቴን ጌታ ኅሩይ በትዳር ሕይወታቸውም መልካም አርዓያ ስለነበሩ ከባለቤታቸው ወይዘሮ ሐመረ እሸቴ ስድስት ልጆን ወልደዋል፡፡በርካታ የልጅ ልጆችንም አፍርተዋል፡፡ቤተሰባቸውንም በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት በፍቅር ይመሩና ያስተዳድሩ ነበር፡፡በድርሰት ረገድ ከ21 በላይ የተደነቁ መጻሕፍትን ደርሰዋል፡፡ሥራዎቻቸው ሁሉ ትሕትናን፤ትክክለኛነትን፤ምግባረ ሠናይነትንና ሞራልን ከፍ አድርገው የሚያሳዩ ናቸው፡፡
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ከጻፉዋቸው መጻሕፍት ውስጥ
ኢትዮጵያና መተማ የዓፄ ዮሐንስ ታሪክ ባጭሩ፤
ወዳጄ ልቤ ፤
ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፤
የልዕልት ወይዘሮ መነን መንገድ በኢሩሳሌምና በምስር፤
መጽሐፈ ቅኔ፤
ዋዜማ፤
በኢትዮጵያ የሚገኙ በግእዝና በአማርኛ ቋንቋ የተጻፉ የመጻሕፍት ካታሎግ ፤
የኢትዮጵያ ታሪክ ከንግሥት ሳባ እስከ ታላቁ የዓድዋ ድል ፤
ድርሳኖች፤
ማኅደረ ብርሃን ሀገረ ጃፓን፤
የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ታሪክ1871-1931ዓ/ም በፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡
ከሥራዎቻቸው ውስጥ አብዛኞቹ በታሪክ፤በግለ ታሪክ‹መዝገበ ቃላት፤በጉዞ ማስታወሻሳዎችና በልቦለድ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸውም ዓለማቀፋዊ ዝናን አትርፈውላቸዋል፡፡
ብላቴን ጌታ ኅሩይ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የታወቁ ፖለቲከኛና በቤተክህነቱም ከፍተኛ ምሁር የነበሩ ሰው ናቸው፡፡ኅሩይ በጥንታዊና ዘመናዊ ትምህርት የተቀረጹ ሰው ነበሩ፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲሬክተር ጀኔራል ሆነው ተሾመዋል፡፡
በ1910 ዓ/ም የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ዲሬክተርነትን ተሾሙ።በ1913 ዓ/ም በልዩ የቆመ ፍርድ ቤት ተብሎ በኢትዮጵያና በውጭ አገር ዜጎች መካከል የሚነሣውን የሀብት ወይም የወንጀል ክርክር የሚሰማና ፍርድ የሚሰጠውን ፍርድ ቤት ፐሬዜዳንትነት ተሾሙ። በተለያየ ጊዜ ወደ እንግሊዝ ፣ጃፓን ፣ፈረንሳይ ፣አሜሪካ ፣ኢጣልያ ፣ጄኔቫ የዓለም መንግሥታት ማኅበር (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ) የመንግሥት መልእክተኛ ሆነው ሄደዋል።
በኢጣልያ ወረራ ዘመን በስደት ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር እንግሊዝ አገር ሄደው ሳሉ በስድሳ ዓመታቸው መስከረም 9 ቀን 1931 ዓ/ም አርፈው መስከረም 9 ቀን 1931 ዐርፈው መስከረም 10 ቀን 1931 ዓ ም በባዝ ከተማ ሉግዘምበርግ በተባለው ቦታ በተከናወነው የቀብራቸው ሥነ ሥርዓት ላይ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር «ታላቅ ነህ ሳልልህ ብቀር ሥራዎችህ ቀድመውኝ ይናገራሉ» ብለዋል፡፡ ቀጥለውም«ይህ የአዳም ልጆችን ወግ ሲቀበል የምታዩት







  • Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
    Facebook
     
    Shared with Public

    አስተያየቶች

    ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

    ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

    እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

    አብይ ኬኛ መቅድም።