የመንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል፡ሂዩማን ራይትስ ዋች

 

"የመንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል፡ሂዩማን ራይትስ ዋች"

ታማሚ እና አስታማሚ

የፎቶው ባለመብት, Amhara Health Bureauየኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን በጤና ባለሙያዎች፣ በህሙማን እና በጤና ተቋማት ላይ ፈጽመዋል ሲል የመብት ተሟጋቹ ሂማን ራይትስ ዋች ከሰሰ።

 

"የመንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል፡ሂዩማን ራይትስ ዋች ታማሚ እና አስታማሚ"
 
የፎቶው ባለመብት, Amhara Health Bureau
ከ 8 ሰአት በፊት
 
"የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን በጤና ባለሙያዎች፣ በህሙማን እና በጤና ተቋማት ላይ ፈጽመዋል ሲል የመብት ተሟጋቹ ሂማን ራይትስ ዋች ከሰሰ።
 
አንድ ዓመት ሊሞላው በተቃረበው በአማራ ክልል በፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት፣ የመንግሥቱ ኃይሎች እና ተባባሪ ሚሊሻዎች በክልሉ የጤና ተቋማት ላይ ፈጽመዋቸዋል ያላቸውን ጥቃቶች በተመለከተ ሂዩማን ራይትስ ዋች ዝርዝር ሪፖርት አውጥቷል።
 
ሪፖርቱ በክልሉ ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ካለፈው ዓመት ማብቂያ አንስቶ የመንግሥት ኃይሎች ቢያንስ 13 በሚደርሱ ከተሞች በጤና ተቋማት እና በሠራተኞች እንዲሁም በትራንስፖርት አገልግሎቶች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎችን ማሰባሰቡን አመልክቷል።
 
የሂማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ላቲሺያ ባድር “የኢትዮጵያ ፌደራል ኃይሎች ለሰላማዊ ሰዎች ሕይወት ግድ ሳይሰጣቸው ካለተጠያቂነት በጣም አስፈላጊ የሆነውን የጤና አገልግሎት በሚሰጡት ተቋማት ላይ ጥቃት ፈጽመዋል” ብለዋል።
 
ምክትል ዳይሬክተሯ ጨምረውም የኢትዮጵያ መንግሥት ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለድርጊታቸው ተጠያቂ የማያደርግ ከሆነ ተመሳሳይ ድርጊቶች ሊቀጥሉ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።
 
በአማራ ክልል ያለው ጦርነት በህክምና ግብዓት እጥረት እና በእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ህሙማን ተገቢውን ህክምና እንዳያገኙ ከማገዱ ባለፈ፤የህክምና ባለሙያዎች በተለይም በመንግሥት ኃይሎች እንግልት፣ ወከባ እና ዛቻ እንደሚደርስባቸው ስማቸው እና የሚሠሩባቸው ተቋማት እንዳይገለጽ የጠየቁ ባለሙያዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
 
የመንግሥት ኃይሎች የቡድን መሳሪያዎች የተጠመዱባቸውን ተሽከርካሪዎች የጤና ተቋማት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ይዘው እንደሚገቡ እና ወታደሮችም እስከ ትጥቃቸው ወደ ታካሚዎች እና የቀዶ ጥገና (ኦፕሬሽን) ክፍል እንደሚገቡ ባለሙያዎች ለቢቢቢ ገልጸዋል።
 
ሂዩማን ራይትስ ዋች ካለፈው ዓመት ነሐሴ አስካለፈው ግንቦት ድረስ ከርቀት ካናገራቸው 58 የጥቃቱ ሰለባዎች፣ የዐይን እማኞች፣ የህክምና ባለሙያዎች እና የእርዳታ ሠራተኞች መረጃ መሰብሰቡን ጠቅሶ፣ ለሪፖርቱ የሳተላይት ምሥሎችን እንዲሁም የተረጋገጡ ቪዲዎችን እና ፎቶግራፎችን ተጠቅሟል።
 
የመንግሥት ኃይሎች የሚፈጽሟቸው በደሎች በክልሉ በሥራ ላይ ያሉ ሆስፒታሎችን እንቅስቃሴ “አደጋ ላይ ጥሏል ወይም አስተጓጉሏል” የሚለው የመብት ተከራካሪው፣ ይህ ሁኔታ የህክምና ተቋማቱን እና ባለሙያዎቹ በሚጠበቅባቸው ሁኔታ አገልግሎት እንዳይሰጡ እንቅፋት ሆኗል ብሏል።
 
“ወታደሮች የፋኖ አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎችን ጨምሮ ለቆሰሉ እና ለታመሙ ሰዎች አገልግሎት የሚሰጡ የህክምና ባለሙያዎችን ይደበድባሉ፣ በዘፈቀደ ያስራሉ፣ ያስፈራራሉ። በተጨማሪም በአምቡላንሶች እና በሕክምና ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ይፈጽማሉ፣ በሰብአዊ እርዳታ መካከል ጣልቃ ይገባሉ። ይህም የአማራ ሕዝብን የጤና አገልግሎት እንዳያገኝ አድርጎታል” ብሏል።
 
ቢቢሲ ያናገራቸው ባለሙያዎችም በመሳሪያ ታጅቦ ህክምና ለመስጠት “ውስጣችን ይረበሻል” የሚሉት ባለሙያዎች፤ “የፋኖን ታጣቂዎችን ታክማላችሁ” በሚልም እንግልት እና ዛቻ እንደሚደርስባቸው ይናገራሉ።
 
ህክምናቸውን ሳይጨርሱ በመንግሥት ኃይሎች ተይዘው የሚወሰዱ ታካሚዎች እንዳሉ የሚናገሩት ባለሙያዎች፤ በሚደርስባቸው ጫና ምክንያት በሥራ ገበታቸው ላይ ወጣ ገባ እያሉ ለመሥራት መገደዳቸውን ይገልጻሉ።
 
ወታደሮች “በህክምና ሥራው ውስጥ ሲገቡ የባለሙያው ሥነ ልቦና ይጎዳል፣ እንዲሁም የታካሚዎችን ግላዊ መብት ሲነኩ ብዙ ጫና አለው” ያሉ በአንድ የዞን ከተማ የመንግሥት ሆስፒታል የሚያገለግሉ ባለሙያ፤ ጫናው ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።