ልጥፎች

ከኖቬምበር 26, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

24.11.2019 EC ለቆጠራ ዬተቀመርን።

ምስል
    ለቆጠራ ዬተቀመርን። ፍቅር ነስቶን ኢጎ አውሮን ሰውሮን በምንትሶ ተወረን ተንተክትከን ወዬብን። ተጣፍተን አጣፍተን ማሰብን አደረግነው ገደል። መኖር ጠፎቶን ተስፋን ቀበርን። ትዕግስት ነስቶን ተነን። መቻል አጥተን ባከን። ምንስ ብንሆን ምንም። በጭካኔ ሰግረን በመታበይ እትብት ቆረጥን ቂም ንብረት ሆኖ ቋጥረን ጧ ብለን ተዘርግተን ሟሟን። ከእንፋቅቅ ጋር ተርትመን በማነስ ተደምረን በሽሚያ ደንብረን በጥድፊያ ተሸርበን በራስ ምልኪያ ተሸንሽነን ተሸብልለን ተቀሽረን። በክፍፍል ሰክረን በዲስኩር ብቻ አበድን ዝለን በድነን በራስ ፍቅር አረግን እፍ ብለን በነን። ተፈጥሮን ዘቅዝቀን ባለማወቅ ቀበርን። በምሻምሾ ተረት ተዛለን ላሸቅን። ኢትዮጵ...

#ጦርነት #ቤርሙዳ #ትርያንግል ነው። #አስማጭ። "አሜሪካ ባቀረበችው የዩክሬን የሰላም ዕቅድ ላይ በሚደረገው ንግግር "ከፍተኛ መሻሻል" መታየቱ ተገለጸ" BBC

  #ጦርነት #ቤርሙዳ #ትርያንግል ነው። #አስማጭ ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።    https://www.bbc.com/amharic/articles/c7419ydkgw8o   "አሜሪካ ባቀረበችው የዩክሬን የሰላም ዕቅድ ላይ በሚደረገው ንግግር "ከፍተኛ መሻሻል" መታየቱ ተገለጸ" ማህበረ ቅንነት እንዴት አረፈዳችሁልኝ። እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።   #በሰላም #ልዕልቷ #እምዬ #ሲዊዘርላንድ #ጄኔባ ላይ የሚከወነው ቅድመ የሰላም መሰናዶ ተግባር ፈጣሪ አምላክ ያሳካው ዘንድ ጽኑ ምኞቴ ነው። የዩክሬን እና የራሺያ፤ በተዘዋዋሪም የኔቶ እና የሩሲያ #ፍጥጫን ተግ አድርጎ መስመር ለማስያዝ የሚደረገው ጥረት ሁሉ #ሰው - #ጠቀም ፤ #ተፈጥሮ #ጠቀም ነው።   በሌላ በኩል ቀጣዩ ትውልድ #ጦርነትን ሊረከብ አይገባም። #ቀጣዩ ትውልድ #ጥላቻን ሊረከብ አይገባም። #ቀጣዩ ትውልድ #በቀልን ሊረከብ አይገባም። #ቀጣዩ ትውልድ #ቂምን ሊረካከብ አይገባም። #ለትውልድ ጠቃሚው ስጦታ #ሰላም እና #ተፈጥሯዊ ፍቅር፤ #ሥልጣኔ እና ቅንነት፤ #ሰዋዊነት እና መከባበር፤ #ትዕግሥት እና ትህትና ሊሆን ይገባል።    ይህ ቸር ዜና ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለምንኖርባት #ምድር ፤ ነፍስ ላላቸው ፍጡራን፤ ለቤት እና ለዱር እንሰሳት፤ #ለወንዞች ፤ ለተራሮች፤ ለፏፏቴው እና ለአየር ጠባይም ጭምር #ተናፋቂ ክስተት ነው።     24 ህዳር 2025 "አሜሪካ፤ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነትን ለመቋጨት ያቀረበችውን የሰላም ዕቅድ በተመለከተ የሚደረገው ንግግር ላይ "ከፍተኛ መሻሻል" መታየቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ተናገሩ። ሩቢዮ፤ የዩክሬን እና አውሮ...

"#ሁለገብ ትግል" እና ትውልዱ።

ምስል
  " #ሁለገብ ትግል" እና ትውልዱ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት አደራችሁ?   #ምዕራፍ ፲፯   "የሁለገብ ትግል" መሠረተ ሃሳብ ጠንሳሹ ግንቦት 7 ነበር። በዛ ዘመን "ሁለገብ" የሚለው የመነሻ ሃሳብ እርሾ ነበረው። እኔ እንደማስበው ከቅንጅት መራራ ስንብት በኋላ የተፈጠሩት፤ አገር ውስጥ ይታገል የነበረው አንድነት የግንቦት 7 አዲስ የሁለገብ ፍልስፍና መንፈስ የመጋራት አቅምን አጠይቆ ይመስለኛል ግንቦቲዝም ሁለገብ ትግል ዶግማው የነበረው፤ ይመስለኛል። ይመስለኛል እምለው እራሱን ችሎ ጥናት ስላልተደረገበት ነው የአቀረብኩት አመክንዮ።   አገር ውስጥ ግንቦቲዝምን በበዛ ጉጉት ይጠብቁ የነበሩ ተናጠላዊ መንፈሶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ አስባለሁኝ። ግንቦቲዝም የቅንጅትን መራራ የስንብት መንፈስ ትንሳኤውን ያወጄ ንቅናቄ ስለነበር። ዲያስፖራ ላይ አንጃ አልተፈጠረም፤ ወጣ ገብም ሁነት አልነበረም። ግንቦት 7 ዲያስፖራውን በአካል የመምራት አቅም ስለነበረው ለሌላ ኃይል ድውለት አልሆነም።    #ግን ሁለገብ ትግል የትኛውን የትግል መሥመር ሊከተል ይችላል?   1) ሰላማዊ ትግልን። 2) የትጥቅ ትግልን። 3) ከዚህ ውጪም ሌላ የትግል መስክ ሊኖር ይችላል በእኔ ዕይታ። #የዝምታ #ዕድምታ ።    በዘመነ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የሁለገብ ትግል አራማጅ ተብለው፤ "በአሸባሪነት" ተፈርጀው ብዙ በጣም ብዙ #ንጹኃን የጥቃት ሰለባ ሆነዋል። በተለይ በበዛ ሁነት የአማራ ልጆች። ሙየህወሃትን መንበር ከሥሩ የነቀለው ግን ከሁለቱም የትግል ስልቶች ውጪ የነበረ ዝቅ ሲል ጥቃት አሻም ያለ #ቅን መንፈስ፤ ከፍ ሲል #የዊዝደም ሙሉ አቅም...