ልጥፎች

ከጃንዋሪ 3, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

"በኮማንድ ፖስት ሥር ያሉ ክልሎች በፌዴራል እስረኞች መጨናነቃቸውን አስታወቁ" BBC

 https://www.ethiopianreporter.com/136872/     በኮማንድ ፖስት ሥር ያሉ ክልሎች በፌዴራል እስረኞች መጨናነቃቸውን አስታወቁ   "በአሁኑ ወቅት በኮማንድ ፖስት ሥር ካሉት ክልሎች መካከል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማረሚያ ቤቶች በፌዴራል እስረኞች ተጨናንቀው መፍትሔ አጥቻለሁ ሲል፣ የጋምቤላ ክልል በበኩሉ የክልሉ ፖሊስ አፋጣኝ ምላሽ እንዳይሰጥ የአገር መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ሀብቱን እየተሻሙት መቸገሩን ገለጸ። የክልሎቹ ተወካዮች ይህንን የገለጹት በወንጀል ተጠርጥረው ነፃነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች የሰብዓዊ መብቶች አተገባበርን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደው፣ ብሔራዊ ምርመራ ሒደት፣ ግኝቶችና ምክረ ሐሳቦች አተገባበር ላይ  ከተለያዩ ክልሎች ከተሰባሰቡ የፍትሕ አካላት ተወካዮች ጋር ባለፈው ሳምንት ባደረገው ውይይት ነው። በውይይቱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ተወካይ በማረሚያ ቤቶችና በፍርድ ቤቶች መካከል ሰፊ ርቀት መኖሩን ገልጸው፣ ከማረሚያ ቤት ለፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮዎች በፍጥነት ለመውሰድና ለመመለስ ፖሊስ እየተቸገረ መሆኑንና ጉዳዩም መፍትሔ አለማግኘቱን ተናግረዋል። ከክልሉ ቢሮ ጋር በመጻጻፍ በእስር ላይ ያሉ ተጠርጣሪዎች መብታቸው እንዳይጣስ እየሠራን ነው ያሉት ተወካዩ፣ የቦታ ጥበት በመኖሩ ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር በመተከልና በአሶሳ ዞኖች የሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ላይ የማስፋፊያ ግንባታ እያከናወኑ መሆኑን አሳውቀዋል። ይሁንና ከምንም በላይ በፌዴራል መንግሥት እስረኞች መቸገራቸውን ገልጸዋል። ‹‹በክልሉ እያጨናነቀን ያለው የፌዴራል እስረኞች ጉዳይ ነው። በርካታ የፌዴራል እስረኞች ነው ያሉት...