ልጥፎች
ከኦክቶበር 19, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ጨካኝነት ለመሪነት ሊያበቃ አይችልም።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
Shared with Public ጨካኝነት ለመሪነት ሊያበቃ አይችልም። "የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁ ፱) አይዟችሁ የነጠፈበት፤ ማጽናናት ድርቅ የመታው፤ በቀውስ በጀት የሚተዳደር፤ በቅጥፈት ቦይ የሚፈስ፤ ቀደምትነትን የሚጠዬፍ፤ ህዝብን የሚጠላ የሚያሳድድ - የሚያሳቅቅ - የሚያቃልል- የሚያናንቅ መንፈስ ለመሪነት ለዛውም ሁለመናዋ በስጦታ ለከበረው የኢትዮጵያ መሪነት የሚታሰብ አልነበረም። ግን ተያይዘን ባበድንበት ወቅት በፈቃድ ሆ! ብለን ተቀበልን። አሁንም ተመሳሳይ ግድፈት ተፈፅሞ አረንቋ ውስጥ ተስፋችን እንዳይዘፈቅ ብርቱ ጥንቃቄ፤ የፀሎት እና የድዋ ጥረት ይጠይቃል። ካሳለፍነው መከራ መጪው ይገዝፋል። ስለዚህም በሁሉም መስክ ህሊናን አብቅቶ ማሰናዳት ይጠይቃል። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ማለት እያንዳንዷ እርምጃችን ማስተዋልን ሊጠጣ ይገባዋል። ፈቃዱ ቢኖር አቅሙ፤ ዕውነቱ ቢኖር ተመክሮው፤ ጽናቱ ቢኖር ልምዱ ሁሉም በዬዘርፋ ሊፈተሽ ይገባል። መሪነት በመፈለግ እና በመሻት ብቻ ሳይሆን ቅባዕም ይጠይቃል። ቅባዕው ከሌለ አይሆንም። እያንዳንዱ እራሱን ለመሪነት የሚያጭ ፖለቲከኛ ሁሉ እራሱን ገምግሞ በራሱ ዳኝነት እንቅፋት እንዳይሆን እራሱን መግራት ይገባዋል። ሁሉም ኑሮ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ቅባው ከሌለ ተያይዞ መንኮት ይሆናል። ይህ ሁሉ ግብር እዬተገበረ ነገን የተሰናዳ ማድረግ እንዲቻል ሆኖ ካልተደራጄ ደግሞ መዛገጥ ይሆናል። ከሁሉም ልዩ ጥንቃቄ የሚሻው ጉዳይ በመፈቃቀድ ላይ የሚፈጠር ሥርዓት ለማቆም መስማማት መቻል ይሆናል። በመዘላለፍ፤ በመወራረፍ፤ በመዘነጣጠል የምናተርፈው አገርም ትውልድም አይኖርም። አክብሮ መነሳት። አክብሮ መሞገት። አክብሮ የተሻለ ሃሳብ ማፍለቅ። አክብሮ መነጋገ...