ልጥፎች

ከኖቬምበር 26, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ነገ ቀጥ ብሎ ቆሞ የተጠረገ ልብን ከሊቃናት ይጠብቃል!

ምስል
መኖርን ለማሰብ መሆንን መቀበል። „ጎለመስሁ አረጀሁም፤ ጻድቅ ሲጣል ዘሩም እህል ሲለምን አላዬሁም።“ መዝምሩ ዳዊት ፴፮ ቁጥር ፳፭ ከሥርጉተ©ሥላሴ  26.11.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ኑርልን አሜኑ! ክፉ አይንካብን ተስፋችን! አሜን! ·       መ ቅድመ ዕሳቤ። መኖር በነፃነት ልክ ይለካል። መለካትም በመኖር ልክ ይለካል። ነፃነትም በመኖር ልክ ይለካል። ነፃነት የአራት ፊደል ቅምረት ቢሆንም የሰው ልጅ መፈጠርን የሚገልጽ ታላቅ ቁምነገር ነው። የሰው ልጅ የተፈጠረው ለነፃነት ነው። የሰውን ልጅ የፈጠረውም ነጻነት ነው። ሰውነት እራሱ ነፃነት ነው። ስለሆነም የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ነፃነቱን ሊጠብቅ ነው የተፈጠረው። የሰው ልጅ የተፈጠረውም ነፃነቱን ሊኖርበት ነው የተፈጠረለት። የሰው ልጅ የተፈጠረበት ምክንያትም በመፈጠር ነፃነት ነው። እግዚአብሄር አምላካችን የነፃነትም ፈጣሪም ንጉሥም ነው። ጌታ ቢባል ነፃነት የሰጠን የፈጠረልን እሱ ብቻ ነው ጌታ። ምድርም ለነፃነት የተፈጠረች ናት። ህዋም ለፃነት የተፈጠረ ነው። ተፍጥሮም ለነፃነት የተፈጠረ ነው። ጠባቂ ወታደራቸው ደግሞ ፍቅር ነው። ፍቅር የአግዚአብሄር  አካል የሌለው የቃሉ አገልጋይ የመንፈስ ድርጁ ሠራዊት ነው። ወልጋዳን መንፈስን የሚጋራ፤ የሚሞረድ። ሸካራውን አለስልሶ፤ ኮረኮንቹን የሚጠርግ።  ፍቅር ነፃነት ካገኜ ነፃነት ህልው ይሆናል። ነፃነት ህልው ከሆን ፍቅር ህልው ይሆናል። ሁለቱ በአንድ ሲዳመሩ ሰላምን ለዛውም የውስጥን ይፈጥራሉ። ሰላም ሰው ሰራሽ አይደለም። መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶት የምድር ተልዕኮውን የመጨረሱ ዋዜማው የውስጡን ሰላም ትቶልን ስለመሄዱ አብስሮናል። የውስጥን ሰላም የተሰጠንን ስጦታ የምናውከው ደግሞ እኛው