ልጥፎች

ከሜይ 11, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዬሞት ተማህጽኖ፣ የስቃይባለተስፋ።

ምስል
ዬሞት ተማህጽኖ፣ የስቃይባለተስፋ።     ምን እና ለምን ስለምንስ። ምን አድርገን ተገኜን??? ጭንቀት ያነሰን መሰለወትን? መሬት ደብድበው ማት አውርድ ብለው መና ለቤተ እግዚአብሄር ዬሚልኩ መሪ ነበሯት። ኢትዮጵያ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይም በድምጽ ያገኙትን በትረ ሥልጣን በደም ጎርፍ አጥለቀለቁት። እኛ ቋያ ላይ ያሉ ቅኔወቻችን ነገን እንዲዩ እንዴት ዞር ሊሉ ይችላሉ እያልን እንጨነቃለን ህግ በሌለበት አናርኪዝም በሰፈነበት ባዕት፣ ባረገረገ ዙፋን ልቀቀል ብሎ መፍቀድ ሥምዬለሽ ማት ነው።።።።።።። ውጭ አገር እንደሚሰለቻቸው አውቃለሁ። ግን ይህም መከራ መቀበል ነው። እናቴ አዘውትራ ፃድቅ ትለኝ ነበር። የቀረብኝን ነገር ሁሉ ኡስባ። ፆምም ሲመጣ የሁልግጤ ፆሚነሽ እኮ ትለኝ ነበር። ከሚወዱት ባተሌነት መለዬት መከራን ፈቅዶ መቀበልም ነበር። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" ዛሬ ምዕራፍ ዘጠኝን ልጀምር ሃሳብ አልነበረኝ። ሦስት ሃሳቦች ሲሞግቱኝ አድረዋል። አንዱ በቤተሰብ ጉዳይ ነው። ሁለተኛው ውሳኔ ነው። ባርች ሆይ ይቅርታ አድርጊልኝ። ሰላም ስጧቸው ቢያንስ አንቺ በመልካምም ቢሆን ሥማቸውን እንዳታነሺ ብለሽ የህማማት ዋዜማ ቃል አስገብተሽኝ ነበር። ይህም በመሆኑ ያዘጋጁት ዬሽግግር ሰነድ በማን እና በምን አመክንዮ እንደ ተጨናገፈ ስገልጽ ኢዴፓ እያልኩ ነበር። የሆነ ሆኖ አሁን ሞት ውሰደኝ፣ ጭንቀት እና ስቃይ ራዕዬ ይሁን ብለው ሲወስኑ ዝም ልል ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። ፈጽሞ። ላም እረኛ ምን አለ ዬእኛ ፖለቲከኞች ድርቅ ዬመታው አመክንዮ ነው። የብዙ ነገር ውድቀት፣ የብዙ ነገር ኪሳራ ዬሚነገረው ስለማይደመጥ ነው። ላደለው ንግግር ብቻ አይደለም ዬሚደመጠው። ፀሃይ አድማጭ ትሻለች። ንፋስ አድማጭ ይሻል። ተፈጥሯዊ ወጀብ አድማጭ ይሻል። የወፎች ዜማ አድማጭ ይሻል መ...

#የኢትዮጵያ_86ቱ ብሄር ብሄረሰቦች መጠሪያ ስም:-

ምስል
አቶ መላኩ ደጀኔ ዬተገኜ ነው። ይህቺ ኢትዮጵያ ትናፍቃኛለች።      ለጠቅላላ እውቀት #የኢትዮጵያ_86ቱ ብሄር ብሄረሰቦች መጠሪያ ስም:- 1. አማራ 2. ኦሮሞ 3. ትግራዋይ 4. ሶማሌ 5. አፋር 6. ሲዳማ 7. አገው 8. ዎላይታ 9. ከምባታ 10. ሀዲያ 11. ጋሞ 12. ጉራጌ 13. ኢሮብ 14. አርጎባ 15. ቱለማ 16. ስልጤ 17. ሺናሻ 18. አኝዋክ 19. ኑዌር 20. ሀመር 21. ኩናማ 22. ጉምዝ 23. በርታ 24. በና 25. አሪ 26. ሙርሲ 27. ቡሜ 28. ካሮ 29. ፀማይ 30. ኮንሶ 31. ዳሰነች 32. ቦረና 33. ጋብራ 34. አላባ 35. አርቦሬ 36. ባጫ 37. ቤንች 38. ባስኬቶ 39. ቡርጂ 40. ጫራ 41. ጋዋዳ 42. ጌዲኦ 43. ጊዶሌ 44. ጎፋ 45. አደሬ 46. ከፊቾ 47. ኮንታ 48. ኒያንጋቶም 49. ናኦ 50. ቀቤና 51. ሱርማ 52. ጠንባሮ 53. የም 54. ወርጂ 55. ዲዚ 56. ዶንጋ 57. ዳውሮ 58. ዲሜ 59. ምዓን 60. ኮሞ 61. ማረቆ 62. ሞስዬ 63. ኦይዳ 64. ቦዲ 65. ፈዳሼ 66. ኮሬ 67. ማሌ 68. ማኦ 69. መሰንጎ 70. መዠንገር 71. ቀዋማ 72. ቀጨም 73. ሸኮ 75. ዘየሴ 76. ዘልማም 77. ሽታ 78. ቤተ እስራኤል 79. ማሾላ 80. ኮጉ 81. ድራሼ 82. ገባቶ 83. ጌዲቾ 84. ብራይሌ 85. ሙርሌ 86. ኮንቶማ .... ናቸው። ************************ ምንጭ - የኢትዮጵያ ታሪክ፣ Amsalu Getu ኢትዮጵያ በትገነጠል 86አገር ይወጣታል  

ኢትዮጵያ ምን ትፈልጋለች? አቅጣጫችን አዬሩ ምን ይሽታል? ምዕራፍ ዘጠኝ።

ምስል
  ኢትዮጵያ ምን ትፈልጋለች? አቅጣጫችን አዬሩ ምን ይሽታል? ምዕራፍ ዘጠኝ።     "መለዬትን የሚወድድ፦ ምኞቱን ይከተላል፥ መልካሙንም ጥበብ ሁሉ ይቃወማል።" (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፱፰ ቁጥር ፩) አመክንዮ ምን ይናፍቃል? እኛስ? እኔስ? ከአኔ ይጀመር። እሺ። ድካም እና ዬአቅም ፍሰት ለስኬት ሊሆን ይገባል። ትናንት ባልተደራጀ የትግል ፍሰት ሲኦል ውስጥ ተቀርቅረናል። አውራ ነን ያሉትም አውራ መሆን ተስኗቸው የኦነግ አንጋች ሁነዋል። አሁንም ያ እንዳይደገም በጠራ መስመር መጓዝ ግድ ይላል። እና። እኔ እምታገልለት ወሳኝ አመክንዮ። 1) ዬጎሳ ፖለቲካ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታገድ። 2) ፀረ ሰው፤ ፀረ ተፈጥሮ፤ ፀረ ታሪክ፤ ፀረ ዜግነት የሆነው የአልባንያ ሶሻሊስት ዬዞግ ግዑዝ መንፈስ ጋር የተቃቀፈው ህገ መንግሥት እንዲታገድ። 3) ኢትዮጵያን ሊመራ የሚችል ሰዋዊ፤ ተፈጥሯዊ ግብረ ኃይል ዕውቅና አግኝቶ አመራሩን እንዲረከብ። 3.1 አሁን ያለውን ሥርዓት በኃይል መደምሰስ የሚለውን አልስማማበትም። 3.2 በምርጫ መቀዬር ይቻላል የሚለውን አልስማማበትም። 3.1 በኃይል ማስወገድ ስልጡን መንገድ አይደለም። በተጨማሪ ነገን አጎሳቋይም ነው። ዛሬንም ዬሚገድል። መስዋዕትነቱን ዬሚያከብድ። አቅም ዬሌላቸውን ዜጎችም ለፈተና ዬሚዳርግ።ለቀጣይ ሰዓታት ዬነፍስ ማሳደሪያ ዬሚሆን ዬሌላቸው፤ ሊለምኑ ያፈሩ ሚሊዮኖች፤ አልጋ ላይ ያሉ ወገኖች፤ ህፃናት ብዙ ችግርን ዬምታስተናግድ አገር ይህ ተመራጭ አይደለም። 3.1.1 በምርጫ። ይህን በጀርመንኛ ምርጫ በሰላም ተጠናቀቀ ሲባል ጽፌዋለሁ። አጣዬ ስድስት ጊዜ ተቃጥላ፤ ሽዋ ሮቢት፤ ሻሸመኔ፤ ዝዋይ፤ ሃረር፤ ጅማ፤ ነደው፤ ሚሊዮኖች በገፍ ተፈናቅለው ከደቡብ እስከ ማዕከላዊ ጎንደር፤ በጦርነት፤ በስጋት በጭንቅ ህዝብ ሌላ አማ...