ዬሞት ተማህጽኖ፣ የስቃይባለተስፋ።
ዬሞት ተማህጽኖ፣ የስቃይባለተስፋ።
ምን እና ለምን ስለምንስ።
ምን አድርገን ተገኜን???
ጭንቀት ያነሰን መሰለወትን?
መሬት ደብድበው ማት አውርድ ብለው መና ለቤተ እግዚአብሄር ዬሚልኩ መሪ ነበሯት። ኢትዮጵያ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይም በድምጽ ያገኙትን በትረ ሥልጣን በደም ጎርፍ አጥለቀለቁት።
ውጭ አገር እንደሚሰለቻቸው አውቃለሁ። ግን ይህም መከራ መቀበል ነው። እናቴ አዘውትራ ፃድቅ ትለኝ ነበር። የቀረብኝን ነገር ሁሉ ኡስባ። ፆምም ሲመጣ የሁልግጤ ፆሚነሽ እኮ ትለኝ ነበር። ከሚወዱት ባተሌነት መለዬት መከራን ፈቅዶ መቀበልም ነበር።
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
ዛሬ ምዕራፍ ዘጠኝን ልጀምር ሃሳብ አልነበረኝ። ሦስት ሃሳቦች ሲሞግቱኝ አድረዋል። አንዱ በቤተሰብ ጉዳይ ነው። ሁለተኛው ውሳኔ ነው።
ባርች ሆይ ይቅርታ አድርጊልኝ። ሰላም ስጧቸው ቢያንስ አንቺ በመልካምም ቢሆን ሥማቸውን እንዳታነሺ ብለሽ የህማማት ዋዜማ ቃል አስገብተሽኝ ነበር።
ይህም በመሆኑ ያዘጋጁት ዬሽግግር ሰነድ በማን እና በምን አመክንዮ እንደ ተጨናገፈ ስገልጽ ኢዴፓ እያልኩ ነበር።
የሆነ ሆኖ አሁን ሞት ውሰደኝ፣ ጭንቀት እና ስቃይ ራዕዬ ይሁን ብለው ሲወስኑ ዝም ልል ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። ፈጽሞ።
ላም እረኛ ምን አለ ዬእኛ ፖለቲከኞች ድርቅ ዬመታው አመክንዮ ነው። የብዙ ነገር ውድቀት፣ የብዙ ነገር ኪሳራ ዬሚነገረው ስለማይደመጥ ነው።
ላደለው ንግግር ብቻ አይደለም ዬሚደመጠው። ፀሃይ አድማጭ ትሻለች። ንፋስ አድማጭ ይሻል። ተፈጥሯዊ ወጀብ አድማጭ ይሻል። የወፎች ዜማ አድማጭ ይሻል መንገድ ቀያሽ ነው።
አድማጭ የማይሻ የተፈጥሮ ኩነት የለም። አድማጭ አልባም የተፈጠረ አመክንዮም የለም። ገፅ ያደምጣል። አፍንጫም ያደምጣል፣ እጅ እና እግርም ያደምጣል። ሁሉም ለመናገር የተሰጠን አካል ሁሉ ተመስጥሮ የማድመጥ ፀጋ አላቸው።
ሞት "አሟሟቴን አሳምረው ይላሉ" ባለ ቅኔወቹ ጎንደሮች። ይህ ቅኔ ለእኛ ነው። ሞታቸውን ወሰኑለት። ይህም መብት ነው። ግን በአሟሟት ሂደት ሊገጥሙ ዬሚችሉ ትሬኮላታወችንስ አስበውበታልን?
አንዱ እኛን ዬሚያሰቃዩን መንገድ ነው። በፖለቲካ አቋም መስማማት አለመስማማት ስለ ሰው ልጅ ከማሰብ በላይ አይደለም። የተሰጠን ፀጋ ሰው ሁነን እንቆም ዘንድ ነውና። ፀጋዬን ስጥስ "ህግ ተላልፌያለሁኝ።" ህግ እንዳልተላለፍ በህግ አምላክ ማህተሜ ነው።
ብዙ ጊዜ ለረጅም ጊዜ በህልሜ አያቸዋለሁ። ከሁለት ዓመት በላይ። ቤተሰቦቼ ያውቃሉ ይህን። ለምን እኔም አላውቀውም። ፈጽሞ።
እናቴ በጣም የምታከብራቸው እና የምትሞግትላቸውም ፖለቲከኛ ናቸው። አሁን ሳይለንት ማጆሪቲ ያለችው መልካም ንግግሮችን ብቻ ማድመጥ እምትሻው ባርችም ህይወታቸው አሳስቧት በምንም መልክ ሥማቸውን እንዳላነሳ አስማለችኝ።
ትናንት ጥዋት የሰማሁት ጉዳይ ግን ሃግ ሊባል ስለሚገባው ብዕሬን አንስቻለሁኝ።
አሁን ያሉትን ጠቅላይ ሚር አብይን አለማወቅ ይመስለኛል ውሳኔው ዬወሰነው። ሞትማ እሱ ባለው ቀን ተገኝቶ ነውን። ተሰቃይቶ፣ መጫወቻ ሆኖ፣ መቀለጃ ሆኖ ሞት ግን???
ሌላው እስራት ብቻ አይደለም ማህበራዊ መሠረትን የሚያራግፍ ገጠመኝም ይደራጃል።
ይህም ብቻ አይደለም የምግብ ብክለት አለ።
ይህም ብቻ አይደለም አዕምሮ መሳትም አለ።
ይህም ብቻ አይደለም አካለ ጎደሎ መሆንም አይደለም።
ይህም ብቻ አይደለም ደግማ እማትገኜውን እናትን ማጣትም አለ። ማንም፣ ምንም ሊሆን ይችላል። በምድር ላይ የእናትን ሃዘን ዬሚያጽናና ምንም ነገር ዬለም። ምንም። ይህ የማይቻለው መቃብር ቤት ነው።
እናቱን በመንፈስ የጎዳ፣ ፈቅዶ ያጎሳቆለስ የሰይጣን ጆሮ ይደፋ እና ስለ እናት ለሚደርሰው አቅም በምን ሞራል ሃዘንን፣ ፀፀትን መግለፅ ይቻል ይሆን??
ሌላው እራስን ማወቅ ሲቻል አንድ ሰው እራሱን እና ዕሴቱን ሲነጋ ሊያበረክት ስለሚችለው ድርሻ አጀንዳው ሊሆን ሲገባ ይደፋልኝ ብሎ መወሰን ለትውልድ ወይንስ ለራስ ፍላጎት ማደር ብዬ እንድጠይቅ ይረዳኛል።
ኑሮዬ ዬተከደነ ነው። በማዕቀብ የተወሰነ ነው። መኖሬ ግን ረቂቅ ጥቅም አለው። በሰው እጅ ያልተሰራ የማይሰራም። ስለዚህ ምሽት ጉዞ አላደርግም፣ ግንኙነቴ በጥበቃ ዙሪያ ነው። መኖሬ ዬተከደነ ነው። የራሴ ዘብአደሩ እኔው ነኝ። ለምን? መኖሬ ጥቅም ስላለው። መኖሬ ከእኔ በላይ ለሆነው የትውልድ ራዕይ ስለሚበጅ እኔ ለእኔ አራስ ልጅ ነኝ።
ዓለምን እረስቶ ከዕንባ ጎን መቆም እምችለው እኔ እኔን ማኖር ስችል ነው። ለእኔ ራዕይ ነፃነቱ ዬእኔ ሰላም ነው።
በሽብር መከሰስ ከጠላቶቼ እጅ ወድቄ ጥቃትን እንድጨልጥ አያስወስነኝም። ሁላችንም በዚህ ተፈርጀን የነበረበት ጊዜ ነበር። ከዓላማችን ዝቅም ሳንል በሰራነው ትንታግ ተግባር ለእነሱ በርቶላቸዋል። ያ ጥንካሬ ለመላ ህዝብ ቢሆን ምኞቴ ነበር ለማህበረ ኦነግ ግጥግጦሽ ባይውል። ግን አስጠንቃቂወቹ ተጠቀሙበት። እኔን ሽብርተኛ ያሉ ዛሬም ከአሸባሪ ጋር ሆነው አፍሪካ ቀንድን እያወኩ ይገኛሉ።
ዬሰው ልጅ እራሱን ያውቀዋል። እራሱን ተርጓሚው አመሳጣሪው እራሱ ነው። የሰው ልጅ ቅኔ ነው። ሲፈጠር ጥሪ አለው። ሲፈጠር መልዕክት ይዞ ነው ዬተፈጠረው። ቢያንስ ለጥሪውና ለሜሴጁ እንዴት ጠንቃቃ አይሆንም? ቢያንስ ማለቴ ነው።
ሌላው አብረው ቅስማቸው ስለሚደቁት ወገኖቹስ እንዴት አያስብም። በህይወቴ ጆይን ያደረኩት አንድ ፓርቲ ብቻ ነው። ለመጀመሪያም ለመጨረሻም። የማህበር እንኳን አባል ሆኜ አላውቅም። ቤተሰቦቼን አሰቃይቻቸዋለሁኝ። ስለዚህም ወስኛለሁ። በግል ከማደርገው ተሳትፎ ውጪ ተጨማሪ ጭንቀት አላመርትም።
አንድ ሰው ደስ ሲለው፣ ሲከፋው፣ ሲስቅ ለብቻው አይደለም። ሰው ብቻውን አልተፈጠረም እና ለሌላውም ማሰብ ይገባል።
ዕውቀት ስለሌላው መኖር አስፈላጊ ያልሆነ መስዋዕትነት በመክፈል አይደለም። እራስን ማትረፍ፣ ፀጋን ማትረፍ፣ ቅባዕን ማትረፍ ይህ ነው ዊዝደም። እንኳንስ ጤና የሌለው ሰው። ዬቸኮለ ውሳኔ ነው። የራሴ አዛዥ ናዛዥ እኔ እንጅ ማንም አይደለምም ነው።
ሰው ግን የማህበረሱቡ ህሊና ነው። እንኳንስ ዛሬ በግሎባላይዜሽን ዘመን። አጀንዳ ያጣን ይመስል፣ የሰበር ሱናሜ ያላጥለቀለቀን ይመስል አዲስ ጊዜ አቅም ዋጮ የሆነ አጀንዳ። ሰላማችን ለምን እንደማይፈልጉት ፖለቲከኞች አላውቅም። እኔ እንኳን በሳቸው ዙሪያ ይህ የመጨረሻዬ እንዲሆን እመኛለሁኝ።
ክብሮቼ ላደረጋችሁልኝ መልካም ነገር ሁሉ እጅግ አመሰግናለሁ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10/05/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ