ልጥፎች

ከኤፕሪል 30, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#የኔታ! ትንሽ ስለ ቴዲ አፍሮ።

  #የኔታ !   #ምዕራፍ ፲፱።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።    #የኔታ !   የቅኔ ~ ቃና ዕውነትን ~ ሊያቀና በማስተዋል ልቅና፤ ያበራል ---------- በልዕልና የምዕት ማሾ - ገ- ናና።   #የኔታ !   መምህር ~ የዝምታ የፊደል ቋሚ -----------የገበታ የውስጥነት - ይሁንታ የተሰጠህ - ከጌታ!   #የኔታ !   የፓን አፍሪካ ሁነኛ ዓውዳችን የእኛ - ለእኛ ምንግዜም አለኽልን - ለእኛ የሆንክልን የመታገስ -------- እረኛ የእምዬ የሃቋ መከታ ዘበኛ።   #የኔታ ።   የሰውኛ ልዩ ፍቅረኛ ተፈጥሮኛ የሆንክ ህሊነኛ የማዕዶት ሥህነ --------ቀመርኛ፤ አለኽልን የተደሞ ዳኛ የዕድምታ ቀና ማኛ።   #የኔታ !   የመቻቻል ቋሚ - በረኛ ለአብሮነት ታዛዥ - እሽተኛ ለኪዳንም ጽኑ ---------ቃልኛ፤ የቅንነት አዝመራ ሰብለኛ የብራ ሆይ! ዜመኛ።   #የኔታ !    የእኔ ድንግል ትጠብቅህ! አሜን። ሳቅህን - ታዝልቅልህ! አሜን። ጥረትህን - ታስብልልህ። አሜን። ጥላ ከለላ - ትሁንልህ። አሜን። እናትነቷን ትመግብህ። አሜን።   አሜን - ወ - አሜን ትንግርት ነህና - ለዘመን የጥበብ ዓውራ - የንብ፤ የብራና ሰንደቅ - ነባቢት የብዕር አደራ -------ትሁት፤ ሆነ እኮ! ----ር ትህ ችሎት - ኽ።    ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን። ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።   ኑሩልኝ። አሜን።   እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።   ሥርጉተ©ሥላሴ። Sergite©Selassie. 29/04/026 21:45 ሲዊዘርላንድ ቢንተርቱር ከተማ።

#ለብልፄው ብርሃነ ትንሳኤው ምኑ ይሆን? አቶ ዩሱፍ ያሲን እና፤ ወይዘሮ ማህሌት ሰለሞን ሁለት የቴዲ አፍሮ የቅርቦች መታሰራቸውን ሰማሁኝ።

  #ለብልፄው ብርሃነ ትንሳኤው ምኑ ይሆን?   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   ምዕራፍ ፴፩።   ብልፄው ትንሳኤን አስመልክቶ የፖለቲካ እስረኞችን ከህሊና እስረኝነት ለቆ ይቆዬኛል ስል ተጨማሪ እስረኞችን አስሮ ነው ያገኜሁት። ከጥሞና ስመለስ። አዝኛለሁኝ። ሰሞነ ህማማት አልፎ ትንሳኤ በዳግም ህማማት??   በትንሳኤ እንደምን የሰው ልጅ ይታሰራል?    ትንሳኤ እኮ የኃጢያት ግድግዳ ተንዶ ብርኃን የታወጀበት የሐሤት ሰሞን ነው።    #እናት እንደዚህ ተይዛ ትታሠራለችን?   እናትነትን እንዲህ መቀጣጫ ማድረግ ይገባልን? ዕድሜስ - አይከበርንም? ሙያ መከበሩ፤ ጥበቃ ማድረጉ ቢቀር እንደምን እንደ ቀራንዮ ዕለት እንዲህ ያለ የግፍ አያያዝ ይፈጸማል? ይህ አክሰሱ ላላቸው አዲሱ ትውልድ ይበጃል ወይ?   #ለመሆኑ ?   ለመሆኑ ኢትዮጵያ ምን ያህል ታዳጊ ወጣት አላት? በዚህ አፈፃጸም ታዳጊ ልጆች የሥነ - ልቦና ስቃይ አይደርስባቸውምን?   " #የብሬ ቀን።"   ትናንት "የብሬ ቀን" ነበር ማለት ይቻላል። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ከትምህርት ሚኒስተር ጋር ሆነው ለልጆቻችን እየሠሩ እንደሆነ ማብራሪያ ሲሰጡ ነበር። ምን ዋጋ አለው። ያን የትምህርት ሚኒስተር ድንቅ ጥረት እንዲህም ተናደ እኮ። ለዛውም 5 ሚሊወን የአማራ ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን #ቆዬን ብለን ወረፋ አስይዘን ማለት ነው።   ሰሞኑን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ "ወቼው ጉድ" ከሚባል ፖድ ካስት ጋር ረጅም ግን የማይሰለች መምህር ቃለ ምልልስ አድርገዋል። እሳቸው ስለተጠየቁ ነው ያዳመጥኩት። ከሚበልጡት ሰው በታች ሥር ሆነው መሥራትን መፍቀዳቸው የምመሰጥበት ክስተት ነው...

ውህድ ማንነትን አናስደንግጠው። #ክብርት ወ/ሮ አምለሰት ሙጬ ፖለቲከኛ ናት ብዬ አላምንም። ስትሆን ለሙግቱ እኔው እበቃታለሁኝ።

  ውህድ ማንነትን አናስደንግጠው። #ውህድ ማንነት የኖኽ መርከብ ነው። • ውህድ ማንነት የማማራችን መክሊታችንም ነው።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   ምዕራፍ ፲፱።   #እፍታ ።   ማህበረ ቅንነት እንዴት ሰነበታችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። የብርኃን ሰሞናቱን አስመልክታችሁ እንኳን አደረሰሽ ላላችሁኝ አዱኛወቼ ሁሉ ውስጤ ለእናንተ ያለውን ልዩ ጣዕም ያለውን አክብሮት በትህትና አቀርባለሁኝ። ኑሩልኝ። አሜን። ማድመጥ፤ ጥሞና፤ ዘለግ አድርጎ ለማሰብ አደባዊ መሆን ይረዳል። ለዛ ነበር ጥፍት ያልኩት። ይህ ባህሌም ነው።   #ጠብታ ።   ውህድ ማንነት በየትኛውም ዓለም ሁነኛ ባለቤት የለለው፤ ውሃ በቀጠነ ቁጥር ለጥቃት የሚጋለጥ የሰብዕና ዓይነት ነው። ውህድ ማንነት በተለምዶ ከሁለት እና ከዚያ በላይ ከሆኑ ቤተሰቦች መገኜት ብቻ አይመስለኝም።   ከእኔ ተመክሮ እንደ ተማርኩት ከሆነ ከአኗኗር ዘይቤም አዳዲስ ማንነቶች ሊመጡ ይችላሉ። ልክ እንደ ፆታ፤ እንደ ኃይማኖት፤ እንደ ሆቢ፤ እንደ ሙያ፤ እንደ ቁመና፤ እንደ ዞግ፤ እንደ ዜግነት፤ እንደ ሃይማኖት ወዘተ። አሁን እኔ እምኖርበት አገር ሲዊዘርላንድ ነው። ከተማዬ በዙሪክ ክፍለ አገር በደጓ ቪንተርቱር ከተማ ነው።    ሌላ ዓለም ከሚኖሩ ጓደኞቼ፤ ቤተሰቦቼ ጋር እንኳን ለየት የሚያደርገኝ የአኗኗር፤ የአለባበስ፤ የአስተሳሰብ፤ የምልከታ ሁኔቴ በራሱ አዲስ ማንነት ሰጥቶኛል። ሁላችንም ስደተኞች ሆነን ኮሬያ ስሜን እና ደቡብ፤ ህንድ፤ ቻይና፤ አሜሪካ፤ ካናዳ፤ በወል መጠሪያው አውሮፓ፤ በተናጠሉ ሲዊዝ ስንኖር ሳላውቀው ማንነታችን በዛ አገር የአዬር ባህሪ፤ ባህል፤ ወግ እና ልምድ ይገነባል።   የብዙ ነገሮች የፍላ...