#የኔታ! ትንሽ ስለ ቴዲ አፍሮ።

 

#ምዕራፍ ፲፱።
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። 
 
የቅኔ ~ ቃና
ዕውነትን ~ ሊያቀና
በማስተዋል ልቅና፤
ያበራል ---------- በልዕልና
የምዕት ማሾ - ገ- ናና።
 
መምህር ~ የዝምታ
የፊደል ቋሚ -----------የገበታ
የውስጥነት - ይሁንታ
የተሰጠህ - ከጌታ!
 
የፓን አፍሪካ ሁነኛ
ዓውዳችን የእኛ - ለእኛ
ምንግዜም አለኽልን - ለእኛ
የሆንክልን የመታገስ -------- እረኛ
የእምዬ የሃቋ መከታ ዘበኛ።
 
የሰውኛ ልዩ ፍቅረኛ
ተፈጥሮኛ የሆንክ ህሊነኛ
የማዕዶት ሥህነ --------ቀመርኛ፤
አለኽልን የተደሞ ዳኛ
የዕድምታ ቀና ማኛ።
 
የመቻቻል ቋሚ - በረኛ
ለአብሮነት ታዛዥ - እሽተኛ
ለኪዳንም ጽኑ ---------ቃልኛ፤
የቅንነት አዝመራ ሰብለኛ
የብራ ሆይ! ዜመኛ።
 
የእኔ ድንግል ትጠብቅህ! አሜን።
ሳቅህን - ታዝልቅልህ! አሜን።
ጥረትህን - ታስብልልህ። አሜን።
ጥላ ከለላ - ትሁንልህ። አሜን።
እናትነቷን ትመግብህ። አሜን።
 
አሜን - ወ - አሜን
ትንግርት ነህና - ለዘመን
የጥበብ ዓውራ - የንብ፤
የብራና ሰንደቅ - ነባቢት
የብዕር አደራ -------ትሁት፤
ሆነ እኮ! ----ር ትህ
ችሎት - ኽ። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
 
ኑሩልኝ። አሜን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergite©Selassie.
29/04/026
21:45
ሲዊዘርላንድ ቢንተርቱር ከተማ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።