ኢትዮጵያን #መዳፈር አይገባም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን #ማጣጣል እና #መናቅ፤ ባለፈም #መታገልም አይገባም።
ኢትዮጵያን #መዳፈር አይገባም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን #ማጣጣል እና #መናቅ ፤ ባለፈም #መታገልም አይገባም። "አቤቱ ንጹህ ልብፍጠርልኝ።" አሜን። ጤና ይስጥልኝ እንዴት አደራችሁ ቤተ - ሥርጉትሻ ቅኖቼ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከዩንቨርስ ጋር ያላት የዕውቀት ደረጃ #የሰመረ ነው። ሳይንስ በደረሰበት ዘመን አይደለም ሳይንቲስቷ ኢትዮጵያ ሳይንቲስት የሆነችው። ፈላስፊት ኢትዮጵያ ፈላስፋ የሆነችው ሳይንስ የዕውቀት ዘርፍ ሆኖ ግሎባሉ ዓለም በተቀበለበት ዘመንም አይደለም። ዩንቨርሷ ኢትዮጵያ ዩንቨርስን የቀመረችበን መክሊቷ የምዕት ነው። ኢትዮጵያ ጀማሪ አስትሮኖመር አይደለችም። #የፊደል ገበታ እንጂ። የእሷነት ሚስጢሯ ማህለቅ ደግሞ #ግዕዝ ቋንቋ ነው። ግዕዝ ቋንቋ ብቸኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅብዓዋ ነው። የተሰጠችው ከእዮር ነው። ኢትዮጵያ ዊዝደሟ ከምድር እስከ እዮር የዘለቀ መሆኑ እኛ በደረስንበት ዘመን እንሆ #ገሃድ እየወጣ ነው። ከስድስት ዓመት በፊት ብላቴናዋ ዶር ሮዳስ ጽፈው፤ ተንብየው፤ ተፈላስፈውበት የነበረው የፋክት እንክብል እንሆ ዕውን ሆነ። ሊቅነት በታምራት፤ ዕውነት በትንግርት ኢትዮጵያ #ልኳን ስታገኝ እንዲህ ነው። ሊቀ - ሊቃውንቱ ዶር ሮዳስ ከእግዚአብሄር በታች እራሳቸውን ይጠብቁ ዘንድ በትህትና ላሳስባቸው እወዳለሁኝ። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። ሚስጢር እንዳይፈስ በአጓጉል ሁኔታ ጥንቃቄ አጀንዳወት ቢሆን ምኞቴ ነው። ዓለማችንን በዩንቨርስ ዕውቀት የሚተረጉሙ ኢትዮጵያ ከተፈጠረች በኋላስንት ሺህ ዘመናት በኋላ የተቋቋሙት የአስትሮኖመር የምርምር ተቋማት እንኳን የኢትዮጵያን የህሊና የሥልጣኔ ደረጃ ሊመክት ወይንም ሊለካካ ...