ኢትዮጵያን #መዳፈር አይገባም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን #ማጣጣል እና #መናቅ፤ ባለፈም #መታገልም አይገባም።

 

ኢትዮጵያን #መዳፈር አይገባም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን #ማጣጣል እና #መናቅ፤ ባለፈም #መታገልም አይገባም።
 
"አቤቱ ንጹህ ልብፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 
ጤና ይስጥልኝ እንዴት አደራችሁ ቤተ - ሥርጉትሻ ቅኖቼ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከዩንቨርስ ጋር ያላት የዕውቀት ደረጃ #የሰመረ ነው። ሳይንስ በደረሰበት ዘመን አይደለም ሳይንቲስቷ ኢትዮጵያ ሳይንቲስት የሆነችው። ፈላስፊት ኢትዮጵያ ፈላስፋ የሆነችው ሳይንስ የዕውቀት ዘርፍ ሆኖ ግሎባሉ ዓለም በተቀበለበት ዘመንም አይደለም። ዩንቨርሷ ኢትዮጵያ ዩንቨርስን የቀመረችበን መክሊቷ የምዕት ነው። ኢትዮጵያ ጀማሪ አስትሮኖመር አይደለችም። #የፊደል ገበታ እንጂ። የእሷነት ሚስጢሯ ማህለቅ ደግሞ #ግዕዝ ቋንቋ ነው። ግዕዝ ቋንቋ ብቸኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅብዓዋ ነው። የተሰጠችው ከእዮር ነው።
 
ኢትዮጵያ ዊዝደሟ ከምድር እስከ እዮር የዘለቀ መሆኑ እኛ በደረስንበት ዘመን እንሆ #ገሃድ እየወጣ ነው። ከስድስት ዓመት በፊት ብላቴናዋ ዶር ሮዳስ ጽፈው፤ ተንብየው፤ ተፈላስፈውበት የነበረው የፋክት እንክብል እንሆ ዕውን ሆነ። ሊቅነት በታምራት፤ ዕውነት በትንግርት ኢትዮጵያ #ልኳን ስታገኝ እንዲህ ነው። 
 
ሊቀ - ሊቃውንቱ ዶር ሮዳስ ከእግዚአብሄር በታች እራሳቸውን ይጠብቁ ዘንድ በትህትና ላሳስባቸው እወዳለሁኝ። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። ሚስጢር እንዳይፈስ በአጓጉል ሁኔታ ጥንቃቄ አጀንዳወት ቢሆን ምኞቴ ነው።
 
ዓለማችንን በዩንቨርስ ዕውቀት የሚተረጉሙ ኢትዮጵያ ከተፈጠረች በኋላስንት ሺህ ዘመናት በኋላ የተቋቋሙት የአስትሮኖመር የምርምር ተቋማት እንኳን የኢትዮጵያን የህሊና የሥልጣኔ ደረጃ ሊመክት ወይንም ሊለካካ የሚችል አቅም እንደሌላቸው የሰሞኑ ክስተት በቂ ምስክር ነው። ኢትዮጵያ ቀደምት አገር ስንል፤ ኢትዮጵያ ፈላስፊት ስላት፤ ሳይንቲስቷ ኢትዮጵያ ስል የሆነችውን ነው።
 
#ግዕዝ ቋንቋ እንደ አንጡራ ጠላት የሚመለከቱ፤ የኢትዮጵያ ቀደምት የፍልስፍና ቋትን የሚጠየፋ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የህሊና ልቅና እና ልዕልና የሚያጣጥሉ ነፃ አውጪ ነን የሚሉ የፖለቲካ ተቋማት የመነሻ መሠረት የተናደ፤ በፍርስራሽ ላይ የቸከለ ስለመሆኑ ፋክት እና ዕውነት እንዲህ ሞግቶ የፋንታዚ ጉዟቸውን ምድር ላይ በዓለም አደባባይ ያሰጣዋል። #ስጦ ነው የሆኑት።
 
ጀግኖቹ፤ ብልሆቹ ጀርመኖች #ግዕዝን አንግሰው የምርምር ቋንቋ ሲያደርጉት፤ ልጆቻቸውን በዩንቨርስቲ ደረጃ ሲያስመርቁበት፤ የዕውቀት የወራረስ እንዲኖርም፤ የግዕዝ ቋንቋ ሚስጢረኛው ቋንቋም እንዲገዳደፋም አዋቂው፤ ብልሁ የጀርመን መንግሥት አማርኛ ቋንቋንም ክብር እና ዕውቅና ሰጥተው በዕውቀት ዘርፍ ሲያካቱት የብልህነታቸውን ዲካ ይገልፃል። እኔ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ የሌላ ዕምነት ተከታዮችም ግዕዝን ቢያጠኑ ቢጠቀሙ እንጂ የሚጎዱበት አንድም ምክንያት የለም። የአገራቸው በረከት ነውና። ምክንያት ግዕዝ የሰማይ ጥበብን ገላጭ #ልዩ #ዓይን ስለሆነ።
 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ከተገለለች ጀምሮ ለእኔ የኢትዮጵያ ጉዞ ነቀልተከልነት #ከፈን አልባ እርቃኑን የኢትዮጵያ ፖለቲካ እየተጓዘ እንደሆን ይሰማኛል። በግዕዝ ቋንቋ ውስጥ የሚገኘው ሚስጢር #ምርቃት ነው። ምድራዊ ያልሆነ ሰማያዊ ምርቃት። የኢትዮጵያ የቀለም ትምህርትን በአግባቡ የተማሩ ሊቃናት ግዕዝን ሲያክሉበት ከሁለት ባለ ዓይናማነት ወደ #ዓራት ዓይናማነት የሚሸጋገሩትም ዕውነት የግዕዝ ቋንቋ ካለው ምርቃት መንፈሳዊ አቅም ስለሚመነጭም ነው። ይህ ሃሳብ የማንነት ቀውስ ባለበት ሰብዕና ይሁን ተቋም እንደሚኮሰኩስ አውቃለሁኝ። ዕውነትን ፈሪወች ስለሆኑ።
 
የማንነት ቀውስ ከዘር ሐረግ ብቻ የሚመጣ አይደለም። ከብዙ የመኖር የአኗኗር ዘይቤወችም ይቀዳል። ከሃይማኖት፤ ከዕውቀት ደረጃ፤ #ከኋለኝነት፤ ከኢኮኖሚ አቅም ስሱነት፤ ከዞግ ቁጥር አናሳነት ወዘተ ………
 
ኢትዮጵያ በየትኛውም መከራ ተፈትና እንደ ወርቅ ነጥራ የምትወጣበት የገዘፈው ሚስጢር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና #ልሳኗ፤ አንደበቷ #የግዕዝ ቋንቋ ምርቃት ነው። ራሱ ዜማዋ ግዕዝ፤ አራራት እና ዕዝል ከያሬዳዊ ጸጋ እና በረከቷ ዕጹብ ድንቅ ነው፤ ይሄ የሌለው፤ ይሄ ያልነበረው ግድግዳ ሰርቶ ቢያነቆንቅ አይፈረድበትም። ያጣው፤ የነጣበት፤ የሌለው ነገር አለና። በራስ የመተማመን አቅም ቁርጭምጭሚት ላይ ሲሆን እምናስተውለውም ለዚህ ነው። 
 
ይህ አገላለጽ የሚሻክረው በማንነት የቀውስ ምች የገጠማቸው ዕሳቤወች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው፤ ከጥላቻ #ድፍድፍም ተለይተው የጠራውን ጸጋ እና በረከት፤ ንጥሩን እዮራዊ ምርቃት በዕውቀት ዘርፍነት ወደ ውስጣቸው የማቀራረብ ወኔ ቢኖራቸው ከብዙ ገረጭራጫ ፍቅ ግድፈቶች ሊድኑ ይችላሉ።
 
መዳህኒቱ እና ፈውሱ እኔ የኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያም የእኔ ብሎ የሚነሳ በራስ የመተማመን መንፈስን በውስጥ ማስረጽ ነው። የአስተሳሰብ ድህነት በወረሰው እከካዊ ጉዞን ማስቀጠል ከሆነ ግን ዱካክ መሆን ነው። የኢትዮጵያዊነት ባለጸጋነት የሁላችንም ነው። የላይ የታች፤ የግራ የቀኝ፤ የራስጌ የእግርጌ ተብሎ ደንበር ሊሠራለት አይገባም። ይኽንን የፈቀዱ ናቸው በበታችነት ስሜት ህመም እየማቀቁ የሚገኙት። 
 
አንድ የኢትዮጵያ ሊቅ ውጭ አገር የሚኖሩ "ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ካስፈለገን እንቀይረዋለን" ሲሉ አንከር ሚዲያ ላይ ቀርበው ነበር። ይህ አገላለጽ እራስን በቅጡ አለማወቅ ምን ያህል #ግርድፍድፍ ዕዳ እንደሆን ተረድቸበታለሁኝ። "ኢትዮጵያ" የሚለው ሥያሜ በፊት ይሁን በጀርባ ቅጥያ ቢኖረው እንኳን ያ ሰማያዊ ኢትዮጵያዊ ጸጋ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ በሰጩ በእግዚአብሄር በአላህ ይነሳል። ከዛ በኋላ ሥጦ መሆን ነው። ልሙጥ መሆን ነው። 
 
የፋና ብሮድ ካስትን ፔጅ ዊክሊ ላይ መረጃ ፈልጌ ሳነብ ብሄራዊውን የሥራ ቋንቋ አማርኛ ቋንቋን፤ ዋሽንግተን ያህል የዓለም የፖለቲካ ማዕከል የሥራ ቋንቋ ያደረገውን ቋንቋ የሰጡት ደረጃ ግርም ነው ያለኝ። ይሄ እኮ ነው እኔ አሉታዊ ዴሞግራፊ፤ የህሊና ነቀላ እና ተከላ የምለው። ዴሞግራፊን እኔ በሁለት ከፍየ ነው እማየው። እሱም አሉታዊ እና አወንታዊ በማለት። አወንታዊው በተፈጥሮ አደጋ ለሚከሰት ቀውስ ህዝብን ከቦታ ቦታ ማሸጋሸግ ሲሆን፤ የሃሳብ ተጫኝነትን ለማፍለቅ የሚካሄደውን ዘመቻ ግን አሉታዊ እለዋለሁኝ። እዚህ ላይ የፋና ብሮድ ካስት ኢትዮጵያዊ ሚዲያ እራሱን ሸብሽቦ ጥብቆ አድርጎ ሳገኜው ግርም ነው ያለኝ።
 
ቢያንስ ሲነሪትን ማሰብ እንዴት ያቅተዋል አንድ ዘመን ጠገብ ግሎባል ሚዲያ? ቅደም ተከተሉ እንዲህ ነው የተሠራው።
 
1)Afaan Orom.
2) Tigrina.
3) Somali.
4) #Amharic. *******
5) Afar Arabic.
6) English. ቅደምተከተሉ ይህ ነው።
 
Fana Broadcasting Corporate - Wikipedia https://share.google/46kjOmHwv78ldF4tW
 
አረብኛ የትኛው የኢትዮጵያ በክልል በመደበኛ እንደሚሠራበት አላውቅም። በሌላ በኩል ቅኝ አገዛዝን የተጠየፈች፤ የቅኝ ግዛትን ግሎባል ምኞት ያነኮተች ጀግና አገር ኢትዮጵያ የድሏ የምሥራች አንባቢ፤ ተርጓሚ እና አመሳጣሪ ባለ #ፊደሉ እጅግ ምቹ ቅኔው የአምርኛ ቋንቋ ለመወርወር ተንቆርጥጦ አገደል አፋፍ ላይ እንዲቀመጥ የተደረገበት አግባብ ኢትዮጵያን እንደ አገር ለማስቀጥል ትልቁ ሳንክ ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ልብ ያሸፍታል። ክብር ለሚገባው በልኩ ክብር መስጠት ከአንድ አገር ከሚመራ መንግሥት ይጠበቃል። በችሮታ ሳይሆን መደበኛ ተግባሩ ስለሆነ። 
 
አገር የሚመራበት መብቱ ከኢትዮጵያ ውስጥነት ስለሚቀዳ። ታቅዶ እንደ ተከናወነ አውቃለሁኝ። ግን አይጠቅም። እያንዳንዱ ቋንቋ የራሱ ማንነት፤ የራሱ የተፈጠረበት ሚስጢር እና መክሊት አለው። መክሊቱን ተዳፍረኽ ስትደፋው የሚያስከትለውን ዶፍ በቅጡ ማሰብ ይገባል። ግልብነት ለስኬት መሰናክል ነው። ቅጽበታዊነትም ትነት። 
 
የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን አጀንዳ ፍለጋ እየባተለ መሆኑን እሰማለሁኝ። ወጬ አልባ ከፊቱ ያለውን የታሪክ #ድርቆሻዊ ሂደትን ለማረም ከውስጡ እንዳልጀመረው በዚህ አመክንይ አስተውየበታለሁኝ። በሌላ በኩል በሲነሪትም ቢሆን ከአረብኛ ቋንቋ ይልቅ ለኢትዮጵውያን #እንግሊዘኛ ቋንቋ ይቀርበናል። ለእንግሊዘኛ ቋንቋ የተሰጠው ደረጃም በር ጠባቂ ዘበኝነት ነው። 
 
ውስጥን እንዲህ እየጣሉ፦ ሚስጢርን ፈቅደው እየከነበሉ፥ መክነፍ ለየትኛውም ተቋም አይጠቅምም። ምርቃት ተነስቶ ጭድነትን ያከናንባል። ሌላ ሚዲያ ላይ ቢሆን አይደንቀኝም። ፋና በብዙ ሁነቶች የብልጽግና መንግሥትን ሁነት ማዳመጥ ስሻ አክብሬ የማደምጠው ሚዲያ ነው። ጥራቱም ስቦኝ ከምከታተለው ሚዲያ እንደዚህ ያለ የዕውነት ዳጥ እና ምጥ ሳዬ ተረግመናል ነው ያልኩት። የራሱ የፊደል ገበታ፤ የራሱ የስዋሰው እርባታ፤ የራሱ ግርማ ሞገስ፤ የራሱ የድምጽ ቃና እና ሜሎዲ ያለው #ጉልላቱን የአማርኛ ቋንቋ #እግርጌ ጠባቂ መደረጉ የኢትዮጵያ የሚዲያ ሁነት ከኢትዮጵያዊነት ቀደምት የጥበብ ማዕከል ጋር ያለውን መራራቅ ምስክር ነው።
 
ጨዋታን ጨዋታ ስለሚያነሳው። ሰሞኑን የኢትዮጵያ አንደበት የነበሩት ዶር ለገሰ ቱሉ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ሰምቻለሁኝ። ለኢትዮጵያ #የልሳን መሪነት አለመመጠናቸውን ስሞግት ቆይቻለሁኝ። በትካቸው የፋና ሥራ አስፋፃሚ መሪ እንዲሆኑ ዕይታየን በጹሁፍም አጋርቼ ነበር። ይህም የሆነው በተለያዬ ጊዜ ጊዜ ሰጥቼ በማስተውላቸው ቁምነገሮች ነበር። ሌላው የገረመኝ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚር እንደ ኮንቴይነር መታየቱ ነው። አዲስ ማዕረግ ተስጥቷቸዋል " አንባሳደር" ዶር ለገሰ ቱሉ። #ይበዛባቸዋል። 
 
በምን የታረመ አንደበት፤ በምን የማሳመን አቅም ለዚህ ዘርፍ ይበቃሉ ተብሎ እንደታሰበ ሳስበው ዕቃዕቃ የልጆች ጨዋታ ነው የሆነብኝ። አንባሳደርነት አገርነት ነው። ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ህግነት ነው። በአፍ እላፊ፤ በውስጥ ቂም፤ በቀል ጥላቻ ሲብተከተክ፥ ሲትከነከን፤ በግድፈት ውስጥ ሰርክ ሲገኜ የባጄ ሰብዕና የኢትዮጵያ ምልክትነት? ተተኪው ማን እንደሚሆን ደግሞ እናያለን። ያው ከተለመደው የኢህአዴግ ችክ ቤተሰብ ሊሆን ይችል ይሆናል። ለዚህም ነው እኔ ኢትዮጵያ የከበደችን ለሁላችንንም ነው እምለው። በእኛ ትውልድ የተዝረከረከ መከራ ነው የገጠማት ጥበቢት ኢትዮጵያ።
 
የሆነ ሆኖ የዶር ሮዳስ ታደሰ ሊቀ - ሊቃውንትነት ምንጩ ከኢትዮጵያዊነት ህሊና የፈለቀ ነው። ያ ደግሞ ከአጤ ግዕዝ፤ የአጤ ግዕዝ ባለቤት ከሆነችው የዕውቀት ምኽዋር ከቅኒት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፈጽሞ የሰው ልጅ ሊደርስባቸው የማይችሉ ረቂቅ የዕውቀት፤ የጥበብ፤ የነብይነት፤ የሐዋርያነት ሚስጢር ናት። በየዘመኑ ብትገለልም፤ ፈተና ላይ ብትወድቅም የላይኛው የሰጣት ዕንቁ አቅም ግን እንዲህ የሙሉ ዘመን ጧፍ እየሆነ ይቀጥላል። ተመስገን።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08/09/2025
 
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።