#ውስጥነት።

 

 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
የሰውነት መለኬያ የውስጥነት #ንጽህና ይመስለኛል። ይመስለኛል እኔ አዘወትራለሁኝ። 
ምክንያቴ #ጥናታዊ ተግባር ስላልከወንኩበት ነው። 
ወደ ቀደመው ስመለስ ለመኖር፤ መኖርን ለማስቀጠል ውስጥን በተፈጠረው ልክ #በንጽህናው ማስቀጠል ነው።
 ንጽህና ደግሞ ከራስ እንጂ #ከደጅ አይጀምርም። 
እያንዳንዳችን የቅድሚያ ተግባራችን ሊሆን የሚገባው በብዙ ድሪቶ የታጀለውን የውስጥ ቆሻሻ ለማጽዳት #መቁረጥ#መወሰን፤ ውሳኔውን ደቂቃ ሳያጠፋ ወደ ድርጊት ማሸጋገር ይገባል።
 እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። ኑሩልኝ። አሜን። 
ሥርጉትሻ 2025/08/26
 
 
 
 
#አጤ ዘመን እና #አጤ ሂደት እንደምን ባጃችሁ?
"አቤቱ ንጡህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
አጤ ዘመን ወይንስ አጤ ሂደት ማን ይሆን #ቀዳሚው? ማን ይሆንስ? #መሪው? እኛስ በአጤ ዘመን እና በአጤ ሂደት ተፈጥሯዊ ክንውን #ሾለክን ወይንስ ልካችን በሚፈቅደው ልክ አብረን #ተጓዝን? ፈተናው ይኽው ነው።
 ሌላውን
#መተቸት #ቁልቁለት ነው። ኧረ ከቁልቁለትም የተሻለ ሞዞቦልድ አልጋ ነው። እኛን ሌላው ሲተቸን ደግሞ #ዳጥ እና #ምጥ ነው። ለምን? ሰውነት ግድፈትም ጸጋው ነው ብየ እኔ በግሌ እቀበለዋለሁኝ። 
 
መግደፍ እንዳሻህ ብለን ባንወስንለት እንኳን ሊሆን የሚችል፤ የሚጠበቅ መሆኑን ልንቀበለው ይገባል ባይ ነኝ - እኔው ሥርጉትሻ። እኛ #ሰወች ነን። ልንሳሳት መቻላችን የተፈጥሯችን ልጥፍ ወይንም ደባል ሳይሆን #ውህድ ነው። 
እንደ ፕላዝማ ማለት ነው።
 ግን በተመሳሳይ ግድፈት በመመላለስ መዳከር ለእኔ #መታመም ነው።
 ይህን ነው ወደን እና ፈቅደን ማረም ያለብን። 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። 
ሥርጉትሻ 2025/08/26 
 
ዕውነት #ይሸመግላልን?
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
#ዕውን = #የሚታይ#የሚጨበጥ#የሚዳሰስ ፋክት ነው። 
ይህ የሚታይ፤ የሚጨበጥ የሚዳሰስ ክስተት #ተፈጥሯዊ ነው። ለምሳሌ ፀሐይ #በምስራቅ ወጥታ #በምዕራብ የመጥለቋ ዕውነት። 
ይህ በፈጣሪያችን፤ በአላሃችን እጅ ያለ የቃሉ የትርጉም ዕለታዊ ክንውን ነው። 
በልዕልት ፕላኔታችን ያለው የለት - ተለት ክንውናችንስ #በዕብለት ወይንስ #በዕውነት በምን #እየተዳኛ ይሆን?
 ዕውነት ይሸምግለው።
 እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉትሻ 2025/08/26 
May be an image of 1 person and smiling 
 
 #ሽሽት ለምን?
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።

የሚከፋው፤ የከፋውም ከተፈጥሮ፤ ከሰዋዊነት #ሽሽት ነው። 
ለምን? በልኩ፤ ስለልኩ፤ ለልኩ መሆን ስለሚሳነን?  
#መሳን በእጅ በሌለ ነገር ቢሆን - በሆነ፤ ግን ነገር ግን እኛ በምንችለው ነገር ለምን በራስ ተፈጥሯዊ #አቅም ላይ #ሽሽትን እንፈቅዳለን? ሰው ሆኖ ስለ ሰው ልጅ #ደህንነት በቅንነት ማሰብ፤ ማሰላሰል እንዴት ያቅታል? 
 እንፈታተሽ ከራሳችን የሰብዕና #አወቃቀር#አደረጃጀት እና #አመራር ጋር። 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። 
ሥርጉትሻ 2025/08/26
 
 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?