ጦርነት እና "ትርፋ።" ፈላስፊት ኢትዮጵያ #የጸና #ሰላም ትሻለች።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ከብስጭት፤ #ከቁጣዊ መስመር መውጣት ይኖርበታል።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
እኔ በልጅነቴ ነበር ጠላፊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጠልፎኝ #ሰምጬ የቀረሁት። የፖለቲካ ህይወቴ ምን ያህል እንደ ጠቀመኝ የማውቀው ነገር በውነቱ የለኝም። ሳውቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ብስጩ፤ #ገረጭራጫ፤ እና #ቁጡ
ነው።
ትናንትም፤ ዛሬም ይኽው ነው። አሁን ባለው ሙሉ ዕድሜየ ላይ ሆኜ ሳስበው ምክንያቱንም፤ ሳንሰላስለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ የስንቁ መሠረት የየዘመኑ ወጣቶች መሆናችን ይመስለኛል። ወጣትነት የአቅም ክምችት፤ የተግባር ፍጥነት እና ትጋት ያለበት ቢሆንም በዕድሜው በራሱ #የመቸኮል፤ ያሰቡት ሲዘገይ #የመበሳጨት ባህሪ የፖለቲካ ድባቡን ይውጠዋል።
እናም የኢትዮጵያ ፖለቲካ በዚህ መሰል በማይታይ ሁነት ግን ብዙ ባለብሩህ ዕሳቤ ያላቸውን ወጣቶችን የሚያጣበት ክስተት ይህ ይመስለኛል። በአመዛኙ በየዘመኑ ለጥቃት የሚጋለጡት ወጣቶች ናቸው።
አንዲት አገር ወጣቶቿን ባጣች ቁጥር ነገን ለማሰብ ይከብዳታል። ይህን ችግር ለመፍታት ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉትሻ 2025/09/01
ጦርነት እና "ትርፋ።"
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።"
ጦርነት
ለሚናፍቃችሁ፤ ጦርነትን ለምትመሩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኢሊቶች ሆይ! በተሳተፋችሁባቸው የጦርነት አውዶች ሁሉ ህዝበ
ጠቀም የሆነ ያተረፋችሁት ነገር አለን????? "ትርፍ" የሚለው ቃል እራሱ ለሰው አጫጁ ጦርነት የማይመጣጠን ነው።
ቃሉ በንግድ አግባብ፤ በገብያ ህግ አፈፃጸም ነው ትክክለኛ ቦታው። በሰው አፈጣጠር፤ አስተዳደግ እና አመራር
"ትርፍ"
ይከብደዋል የተፈጥሮን ታምራት የፈጣሪን ጥበብ የመሸከም። የሆነ ሆኖ እኔ ከሁሉም ቀድሜ ነበር ኢትዮጵያ ጦርነት በቃት ብየ ያወጅኩት። ጦርነቶች ባይኖሩ ኢትዮጵያ ትናንትም፤ ዛሬም የት ደረጃ በደረሰች ነበር። ጦርነት የሚያራምደው ፖሊሲ #ጭካኔ ነው። ጭካኔን ለምትወደው፤ ለምታከብረው ህዝብ መጋበዝ የተገባ አይደለም።
ጦርነት አሰልቺ፤ አድካሚ፤ አውዳሚ #ከንቱ #ክስተት ነው። "ድል" የሚባለው ክስተት በሰው ልጅ #ደም #የደላው ነው። የአገር ሉዓላዊነት ሲደፈር አገርን ማስከበር ትውልዳዊ ድርሻችን ነው።
ከዛ በመለስ ያሉ ጥያቄወችን ግን በጨመተ፤ በበሰለ ፖለቲካ መልስ እንዲያገኝ መትጋት ይገባል። የእኔ መስመር ይህ ነው።
ሥርጉትሻ 2025/09/01
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
የብልጽግናው መንግሥት፤ ተፎካካሪወች፤ ተቃዋሚወች፤ ተጠማኞች በራሳቸው መቆም የማይችሉትን ነው እኔ #ተጠማኞች የምላቸው፤ ሁሎችም አገር የሚመሩት ያስፈልጋቸዋል። ህዝብ እንቆምለታለን የሚሉት ያስፈልጋቸዋል።
ሁለቱንም ማግኜት የሚችሉት ግን #በሰላም #የጸናች አገር ስትኖር ብቻ ነው። ሰላም የምንሻ ስደተኛ ልጆቿ የዘወትር ጸሎታችን የእናት አገራችን እና የልጆቿን #የጸና ሰላም ፈጣሪያችን አስጠብቅልን ነው። ለዚህም ነው የርስበርስ ጦርነትን የማልደግፈው። ኢትዮጵያ የምትናፈቅ፤ ሥሟ #የሚያሳሳ፤ የሚቀናባት፤ የምታጓጓ የትንግርት አገር ናት።
እኔ እወዳታለሁኝ። የውስጥ #ማህተሜ ናት። ክብሬም፤ ዘውዴም ናት። ደራሽ ታጋዮች ሊያሸብሩን ይሻሉ። #አይሞክሩት። የበቃ ተመክሮ ያለን ጽኑ ልጆች ለኢትዮጵያ አለናት። ለህዝባችን ሰላማዊ ህይወት ትጋት #የማይደክመን። እናት አትሰለችምና።
የጎደለውን በአመክንዮ በተለይ በሰባዕዊ መብት አያያዝ ያለውን ጫና እንሞግታለን። ሥልጣን፤ ክብር፥ ጭብጨባና ውዳሴ አልሻም እኔ በግሌ። አጀንዳየም አይደለም።
ሥርጉትሻ 2025/09/01
#በተረፈ ………
ዕርዕስ ይሁን ውድቼ፤ በተረፈ ቸሮች ናችሁ እና የቤተ - ሥርጉትሻ ታዳሚወች፤ ቅኖች ናችሁ እና የሥርጉ - ቤተኞች፤ #ከቁጣ፤ #ከብስጭት፤ #ከመዘላለፍ የታቀባችሁ #ጭምት #ቅኖች ናችሁ እና የእኔ አዱኛወቼ #ውብ የሆነ፤ #የፈካ፥ #የተባ ቀን ይሆንላችሁ ዘንድ ከነቃው ህሊናየ እመኝለሁኝ። ኑሩልኝ። አሜን። የእኔ ድንግል ትጠብቅልኝ። አሜን።
የእስልምና ዕምነት ቤተኞቼ ትዕግሥታችሁ ሁልጊዜም #ቆሞ እንደሚያስተምረኝ ልገልጽላችሁ እወዳለሁኝ። #ኑሩልን። አሜን። #ክብሮቻችን #ሞገሶቻችን #ህብራዊነታችን ናችሁ እና።
#ቸር አስበን፤ ቸር #እንሁን፤ ቅን አስበን፤ #ቀና እንሁን። አሜን። ሥርጉትሻ 2025/09/91
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ