የአጤ አባይ #ዳግም ልደት እና የኢትዮጵያ #የፖለቲካ እስረኞች።

 

የአጤ አባይ #ዳግም ልደት እና የኢትዮጵያ #የፖለቲካ እስረኞች።
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
እኔ በኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ በኢትዮጵያ ቴሌኮም፤ በኢትዮጵያ ሠራዊት፤ በኢትዮጵያ አባይ ግድብ ኢትዮጵያን በጥልቀት በሚወክሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች እና ተቋማትን በሚመለከት የየዘመኑን ገዢወች በምሞግትበት ሁነት ፈጽሞ አላያቸውም። እራሳቸው ትውልድ ስለሆኑ። በጣም እጅግ #ቁጥብ ነኝ። በሙግት ፈጽሞ አልነካካቸውም። ይልቁንም ዝምታየን በማስተዋል እመግባቸዋለሁኝ።
#እስቲ ዛሬ ……… 
 
#አያድርግብኝ እንጂ እኔ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ብሆን ኖሮ፥ ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞችን ይዤ የአባይ ግድብን ዳግም #ልደትን እንዲዩ አደርግ ነበር። ይህ አዲስ ክስተት ለሌላ ንጹህ ግሎባል ፖለቲካ ሁነት ጋር ልዩ ቀረቤታ ሊኖረው ስለሚችል፤ አዲስ ጎዳና ይጠርግ ነበር። የዓለምም አዲስ #አጀንዳ ይሆን ነበር። ለግሎባሉ የሰብዓዊ መብት አስጠባቂ ተቋማትም ፈር ቀዳጅ የፊደል ገበታ በሆነ ነበር።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች የመናገር፤ የመፃፍ፤ የማሰብ፤ የመራመር፤ ሃሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ መብታቸው ላይ የኢትዮጵያ ህገ - መንግሥት ፈቅድነውም አልፈቀድነውም፤ በሚፈቅደው ድንጋጌ ልክ ሊሆን ይገባል። የሚዲያ ሠራተኞች፤ ጸሐፊወች ሞጋቾችን እና የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚያገናኘው ድልድይ የኢትዮጵያ ህገ - መንግሥት ርካብ ብቻ ነው።
 
የሆነ ሆኖ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ በድንገቴ ተውኔት የተዋጣላቸው ናቸው እና የፖለቲካ እስረኞችን ከአጤ አባይ ከሆደ ሰፊው፤ ከታጋሹ ጋር ፊት ለፊት ካአገናኙ በኋላ፤ ከእንግዲህ የፈለጋችሁ አብረን እንመለስ፤ የፈለጋችሁ ከዛሬ ጀምሮ መንግሥታችን ከቤተሰቦቻችሁ ጋር ትቀላቀሉ ዘንድ ፈቅዷል ቢሉ? ምንኛ #በታደሉ ነበር።
 
ያ በራሳቸው ጊዜ ውሃ ነስተው እየታዬ #ያደረቁት የፍቅር፤ የተቀባይነት የአበባ ዘርም እንደገና #ያጨበጭብ ነበር። አጤ አባይ እኮ ለዚህ የክብር - ክብር፤ የልዕልና - ልዕልና የበቃው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ #በይቻላል መንፈስ ቁርጠኛ ውሳኔ በመውሰዳቸው ነው። በዚህ ማዕቀፍ ያልታቀፋ ኃያላን አገሮች የታሪኩ ባለቤት እና አጋር ለመሆን መሻታቸው ሲመረመር የውሳኔውን ረቂቅ ብቃት ማየት ይቻላል። ሃሳቡ እጅግ #የላቀ ነበር።
 
እርግጥ ነው ግድቡ የተሰራበት ቦታ እና ግድቡ በአማራ ክልል እንዳይሆን ያደረጉበት ሁነት ትክክል ነው ብየ አላምንም። የግዮን መነሻ በዓት የአጤ አባይ ዳግም ልደት መመሳጠሪያ ሊሆን ይገባ ነበር ባይ ነበር። ሚስጢርን መዳፈር የማይታዩ ረቂቅ እክሎችን ይፈጥራል እና። የወደብ እና የባህር በር ጉዳይን በሚመለከት፤ የዞግ ፖለቲካ ሽንሸና ህመሞች ናቸው ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት።
 
ወደ ቀደመው ስመለስ ያን #የላቀ ሃሳብ በአስፈፃሚነት አቶ መለስ ዜናዊ የመረጡት ደግሞ እንደ ወርቅ ተፈትነው ሌሎች የሃይል ማመንጫወችን ስኬት ላሳዮዋቸው #ለሰማዕቱ ኢንጂነር ስመኜው ሰጡ። የዚህ ቁርጠኝነት ኢትዮጵያ ትክክለኛ መሪ በትክክለኛ ጊዜ ስታገኝ አቅሟ #ሊያበራ፤ ሊጎመራ እንደሚችል #ያመሳጠረ አመክንዮ ነበር። የዘመናችን አዲስ የትምህርት #ካሪክለም ነው። 
 
የሆነ ሆኖ ነገረ የአባይ ግድብ ብዙ የፖለቲካ ብሄራዊም፤ ግሎባልም #ወጀብ ነበረው። ፈተና ነበረው። ኢትዮጵያን አስቦ የተነሳ ሃሳብ ስለነበረ በሌሎች ጉዳዮወች የቀድሞው ጠቅላይ ሚር አቶ መለስ ቢወቀሱም ይህኛው ግን የኢትዮጵያ ቀደምት መሪወች በውስጣቸው ይዘውት የነበረውን ትልም ዕውን ያደረገ ታላቅ ተጋድሎ ነበር። ትልሙ የአጤ ኃይለሥላሴም እንደነበር ቋሚ ምስክሮች አሉ፤ ከዛም በቀደመ ዘመን አባይ እና የኢትዮጵያ መሪወች #በውስጥነት #ሲያወጋጉ ቆይተዋል።
 
ተጋድሎው እንዲያበራ ደግሞ የኢትዮጵያ #እናቶች ሙሉ ተሳትፎ አለበት። እና ኢትዮጵያ ስትስቅ የኢትዮጵያ እናቶች እኩል እንዲስቁ እስረኛ ልጆቻቸው እንዲፈቱ ቢደረግ #ብልህነት ነው ብየ አሰብኩኝ። እኔ በኢትዮጵያ ከወንጀል ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት የፖለቲካ እስረኛ በአገሬ በኢትዮጵያ ሊኖር አይገባም ባይ ነኝ። 
 
ህወሃት ፈቅዶ ስልጣኑን እንዲለቅ ያደረገው ቁምነገርም ይህ ነው። ህወሃትን በቋሚነት፤ በጽናት እኔ በተከታታይነት የሞገትኩበት አመክንዮ ይኽው ነበር። እናም ለእስረኛ ቤተሰቦች ወላጆች፤ የትዳር አጋሮች፤ ልጆች፤ ቤተሰቦች፤ አድናቂወች ጋር ኢትዮጵያ ስትስቅ አብራችሁ ትስቁ ዘንድ #ፈቅደናል ቢሉ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #ሰናዩ ሙሉዑ ይሆን ነበር። 
 
ወደ ሥልጣን ሲመጡ ተሰጥቷቸው የነበረው ምርቃት እና ፍቅር ሙሉ ለሙሉም ባይሆን የተወሰነውን መልሰው ባገኙ ነበር። አዲስ ዓመት ሲመጣ፤ አደይ አበባ ሲፈካ ጋራ ሸንተረሩ ለምልሞ ሲያውካካ የኢትዮጵያ እናቶችን አብሮ ማሰብ ይገባል። የድምጽ አልቦወቹ የኢትዮጵያ እናቶች እንባ እንዲቆም በተደረገው አድካሚ ተጋድሎ ነበር 50% ካቢኔው የኢትዮጵያ #ሴት ሊቃናት እንዲሆን የተደረገው። 
 
ያ ድል ከወንዝ ዳር የታፈሰ አሽዋ አልነበረም። መኖራችን ገብረን፤ ሁለመናችን መግበን በተጋንበት መስመር የተገኜ ነው። #ለተሿሚ ሴቶች ያልደከሙበት ስለሆነ ምናቸውም አይደለም። እኛ ግን የኢትዮጵያ እናቶች እንባ የኢትዮጵያ ፖለቲካ #የገበርዲን እና #የሱፍ መሆኑ ነው በሚል መሥመር በተደረገ ተጋድሎ ነው ይህ ዕድል የተገኜው። 
 
ምንም እንኳን #የብልጽግና የኢትዮጵያ ሴት ሊቃናት በዚህ እረገድ ትዝ ብሏቸው ባያውቅም። በነፃ የተገኜ እና በነፃ የታፈሰ ዕድል ስለሆነ።
የሆነ ሆኖ የአቶ መለስን የአባይ ግድብ ሌጋሲ አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ፤ የአቶ ኃለማርያም ደስአለኝን የአባይ ሌጋሴ በሌላ ቀለም፤ ሌላ ቀለም የምለው የኢንጂነር ስመኜው ሰማዕትነት፤ የአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት ታክሎ ቀለሙን ይለውጠዋል። በራሳቸው የሥራ አፈፃጸም ፕሮጀክት ጀምሮ በመፈጸም ብዙም የማይታሙት ጠቅላይ ሚር አብይም ጉሽትሽት ባለ ዘመን፤ በጦርነት በኢኮኖሚ ቀውስ፤ በሚታዩ እና በማይታዩ ችግሮች ሁነው ለስኬት ማብቃታቸው መልካም ነገር ነው። ማስቀጥል ብቻ ሳይሆን ፍፃሜውን አሳምሮ መቋጨት ለኢትዮጵያ ትንሳኤ አንድ ግዙፍ ድል ነው። ድሉ ሙሉ ይሆን ዘንድ ነው የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ ያነሳሁት እንጂ ድሉ ድል ብቻ ሳይሆን አዲስ የኢትዮጵያዊነት #ካሪክለም ሊሆን የሚገባው ነው። ክብር ለሚገባው ክብር መስጠትም ይገባል። ለድካም፤ ለልፋት ዕውቅና መስጠት ህሊናዊ ጉዳይ ነው። ዕውነት ሊሸሽ አይገባምና። 
 
የሆነ ሆኖ ስለ ኢትዮጵያ ያገለገሉ ሁሉ ሊመሰገኑ የሚገባበት ዕለት ለሁሉም ካለወሰን፤ ካለደንበር በንጹህ ልቦና ማመስገን ይገባል።ኢትዮጵያ በምትስቅበት ቀን እኒህ አባት በእስር ላይ ሆነው የምሥራቹን እንዴት ሊጋሩ ይችሉ ይሆን? አባት ጋዜጠኛ እና ጸሐፊ አቶ ታዲዮስ ታንቱ ግን እንዴት ሰነበቱ? ደህና ነወት ወይ? 
 
ሌሎቻችሁ የሚዲያ ባለሙያወች፤ ጸሐፍትም እንዴት ሰነበታችሁልኝ። ካለምንም ጠያቂ ሙሉ የአብይዝም የሥልጣን ዘመን የታሠራችሁ ከ1300 የጦላይ እስረኞች ውስጥ ተነጥላችሁ በእስር እንድትቀጥሉ የሆናችሁ ቢጫ ለባሾችስ እንዴት ናችሁ? 
 
እግዚአብሄር አምላክ ለቤታችሁ ያብቃችሁ። አሜን። ባላችሁበት ፈጣሪ ይጠብቃችሁ። አሜን። ለቤተሰቦቻችሁም ብርታትን አምላኬ ይስጥ። አሜን። 
 
የአኔ ክብረቶች የሥርጉትሻ ውድ ቤተሰቦች እንዴት አደራችሁ? መልካም ሰንበት ይሁንልን። አሜን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን፤ አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
6/09/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?