ልጥፎች

ከዲሴምበር 25, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ይህን ማንዴላነት ኮ/ ጎሹ ወልዴ ብቻ ነው ሊወጡት የሚችሉት።

ምስል
ብሄራዊ የእርቀ ሰላም ማቋቋሚያ ኮሚሽን አዋጅ የተግባራዊነት የአቅም ልቅና ፅላተ ማንዴላነት ለስኬቱ... „ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ሥርዓት በሥርዓት፣  ሥርዓት በሥርዓት፤ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ“ ትንቢተ ኢሳያስ ፳፰ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 25.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ማንዴላ! ·        መነ ሻ። https://www.youtube.com/watch?v=UR7B8bjrM4U የምክር ቤቱ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን ማፅደቀ v     ተ ምኞት የሚቀዳ የሃሳብ ፍሰት! „ቸር ተመኝ ቸር እንድታገኝ።“ እንዲህ ቸር ተመኘሁኝ ተዚያ በፊት ግን እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ቅኖቹ? ደህና ናችሁ ወይ? አሁን ከፋናም ከዋልታም ቴሌቪዥን እንደሰማሁት ዜና የኢትጵያ የተዋካዮች ምክር ቤት ዛሬ የብሄራዊ የእርቅ ማቋሟሚያ ረቂቅ ዓዋጅ በአንድ ድምጽ ተዕቅቦ፤ በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ማጽደቁን አዳመጥኩኝ ። ትልቅ እርምጃ ነው። ትልቅ እርምጃነቱ በዳይም ተበዳይም፤ የተጣላም የሚታረቅም የለም የሚል ጠሐይን የገለበጠ ሙግት ስለነበር። እርግጥ ነው ሥራው እጅግ ውስብሰብ ነው። ሃላፊነቱም ግዙፍ ነው። ማስተዋልን፤ ትዕግስትን፤ መቻልን፤ አብዝቶ ማድመጥን፤ አረግቶ መቀመጥን፤ የሰፋ እና የዘለቀ የህይወት ተመክሮን፤ ነገሮችን በተያዬ አቅጣጫ ማዬትን፤ ተግባቢነትን፤ አቃፊነትን፤ ህሊናን መፍራትን፤ ትውፊት - ባህል - ወግ - ታሪክ - ህዝብ - ህግ አክባሪነትን፤ ፈርኃ እግዚአብሄር መኖርን መቀበልን፤  ሙሉሰው የሆነ ሰብዕናን ይጠይቃል። ጭንቅ ሃላፊነት ነው። እንደ ኢትዮጵያ ባለ የቂም ፖለቲካ ባህል፤ የበቀል ሥልጣኔ፤ የቁርሾ ቱማታ፤ የስሜት አው