ልጥፎች

ከኖቬምበር, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አማራ ዘሩ እንዲጠፋ የተወሰነበት ጭምት ህዝብ ነው። 25.11.2020

  አማራ ዘሩ እንዲጠፋ የተወሰነበት ጭምት ህዝብ ነው። አባ ቅንዬ የአማራ ህዝብ የዘመኑን ባህሬ በማንበብ የህሊናዊነት አድማሱን ሊያሰፋ ይገባል። ከሩትን ተግባር ወጥቶ ባለ እርስትነቱን በሉላዊ ህግጋት ማስከበር ግድ ይለዋል። ሰርክ የቹቻ እና የሰኔል መሰናዶ ሊሰለቸው ይገባል። ዘወትር ሊቃናቱ ተለይተው ለካቴና፣ ለባሩድ፣ ለካራ፣ ለሳንጃ፣ ለሜጫ፣ ለእሳት ሲዳረጉ ለምን ብሎ እራሱን ይፈትሽ አማራ! በቃኝን ለምርምር ያውል። በስተቀር የኩርድሽ ዕጣ ክፍሉ ይሆናል። ማንም እንዳይኖረው ነው ሊቃናቱ በረድፍ የተረሸኑት፣ ልቅምቅም ብለው አሁንም ለካቴና የተሸለሙት የትውልዱ ተስፋ ቀና እንዳይል፣ ተስፋ ቢስ እንዲሆን ነው የታለመው። የሚከወነው። አለኝታ፣ ጋሻ እንዳይኖረው ማድረግ ሙሉ ፕሮጀክት ነው የአገዛዙ። ስለዚህም የአማራ ህዝብ በማስተዋል መራመድ፣ አቅሙን ቆጥቦ ማስተዳደር፣ ከፈጣሪ ከአላህ ጋር መምከር ይኖርበታል። ቂም፣ በቀል የፀነሰ ዕለት ከሰዋዊ ውርጅብኝ በላይ ሰማያዊ እሳት ይወርድበታል። ሰው ሆኖ የመፈጠሩ ሚስጢር ፈርኃ እግዚአብሔር፣ ፈርኃ አላህ መሆኑን ሆኖ በመገኘት፣ ማክበር፣ ማስከበር ይኖርበታል። ጥላቻ አመድ፣ ክሰል፣ ትቢያ ነው። እሱ አልተፈጠረበትም። እና ለሰከንድ እንዳያስጠጋው። በስተቀር ምርቃቱ ይነሳል። ሁላችንንም ያጠፋናል። መክሊታችን ይሰረዛል። ሰብዕነታችን ፍግ ይሆናል። አደራ። ከዚህ ባሻገር ባለው ተጋድሎ ቆርጦ ትግል ውስጥ መግባት ይኖርበታል። ቀን እዬቆጠረ ፀረ አማራ፣ ፀረ ተፈጥሮ፣ ፀረ ሰው አዬሩ ይጠራል። ሥራው የመዳህኒዓለም ነውና። ከሰብዕነት ተርታ ለጠፋት ፈጣሪ የንሥኃ ጊዜ ይስጣቸው። አሜን። እኛ የተሰጠንን መልካምነት ይዘን የሚጠሉን ክፋነትን ሰንቀው ቢጓዙ ችሎቱ የእዮር ነው። ካለ ካህሊ - ሥልጣናችን ዘው አንበል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ኢትዮጵያዊነት በጉልት አውጫጭኝ አልተፈጠረም። 25.11.2020 የበህግ አምላክነትን ጥሳ እናት ወደ ዬት?

የበህግ አምላክነትን ጥሳ እናት ወደ ዬት?    ኢትዮጵያዊነት በጉልት አውጫጭኝ አልተፈጠረም። ኢትዮጵያዊነት ዩንቨርስቲ ገብተው የሚማሩት ፍልስፍና ነው። ኢትዮጵያዊነት የዓለም መድህን የሆነ የምርምር ማዕከል ነው። ኢትዮጵያዊነት አናባቢም ተነባቢም ቅዱስ በረከት ነው። ኢትዮጵያዊነት ተዘርዝረው በማይዘለቁ ንጥረ ነገሮች የተቀመመ ምጥን ማንነት ነው። ኢትዮጵያዊነት በጉልት ገብያ አውጫጭኝ አልተመሰረተም። ኢትዮጵያዊነት በውስጥህ ከኖረ ክህደት፣ ዝቅጠት፣ ስላቅ፣ ዝንፈት፣ መስቃ፣ ትዕቢት፣ ፀረ ሰውነት አያሸንፋህም። ኢትዮጵያዊነት ተፈጥሯዊነትም፤ ሰዋዊነትም ነው። ኢትዮጵያዊው ሰው ፀጋው ዝልቅ ነው። ተማረ አልተማረ። ሰማዩን አይቶ የአዬሩን ባህሬ ይነግርኃል። ዛፍ ቆርጦ ዕድሜውን ይነግርኃል፣ የሰውነት ዛላህን አይቶ ውስጥህን ያነበዋል። ያብራራዋል እንደ ዘመንኛው ራዲወሎጂ በለው። ኢትዮጵያዊነት መርኽም ነው። ኢትዮጵያዊነት መንገድም ነው። ኢትዮጵያዊነት በህግ አምላክነትም ነው። ህግ ነው። ኢትዮጵያዊነትን በውስጡ ለፈቀደ ብርኃን ነው። ከፍ ቢል ዝቅ ቢል መጥኖ በቁጥብነት መኖርን ያኗኑራል። ሊቀ ሊቃውንቱ ፕ/ ኃይሌ ላሪቦ ኢትዮጵያዊነትን "ረቂቅ ሚስጢር" ይሉታል። አባ ትሩጉም አቶ እስክንድር ነጋ ደግሞ "የኢትዮጵያዊነት አፈጣጠር ኦርጋኒክ" ነው ዬሚል ጥልቅ ፍልስፍና አለው። ውስጡን ላጠናው ዕውነት ነው። ይህን የሚሸከም መሪ ማግኜት ግን አልተቻለም። ለዚህ ነው የአፍሪካ አገር መሪዎች እዬተሸማቀቁ ያሉት። አፍረውብናል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ኢትዮጵያዊነት ቅኔ ነው።  

የአማራ እርቀ ሰላም እንዴት ከእነማንስ ጋር?

ምስል

ቅዱስ ሲኖዶስ ስንቱን የቅድስና እረኝነቱን አግልሎ ሊዘልቅ ይሆን?

ምስል

''ፀጋዬ ሼክስፒርን በአማርኛ ያናገረ ሰው ነው'' | እንዳለጌታ ከበደ ከአበበ ባልቻ ጋር | ''እሳት ወይ አበባ'...

ምስል

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተሳሳተ ትርክት፥ "አማራ የነገድ ማንነት የለውም" ሲፈተሽ

ምስል

ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል መታገታቸው ተደመጠ፨ 24.11.2023

ምስል

የአማራ እረቀ ሰላማ እንዴት? ከእነማንስ ጋር??? #ሚስጢረኛችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት!

ምስል
  የአማራ እረቀ ሰላማ እንዴት? ከእነማንስ ጋር??? እንዴት አደርን? የቅኔ አድባራት እንዴት ውለው አደሩ ይሆን? እነ ማህበረ ቅንነትስ እንዴት አላችሁልኝ??? #ሚስጢረኛችን #ኢትዮጵያ #ብቻ #ናት ! "የቤትህ ቅናት በላኝ።"       ይህ ጥያቄ ከ32 ዓመት በላይ ተቀንቅኗል። አማራ እንደ አማራ የጠላውም፤፦የሚጠላውም፤፦የሚያሳድደውም፤፦የሚያወግዘውም፤ ያፈናቀለውም፤፦ያሳደደውም፤ መኖሩን የቀማውም፤ ጋብቻ የከለከለውም፤ በጉርብትና ፊት የነሳውም፤ በግብይት ያገለለውም አይደለም ማህበረሰብ፤፥ተቋም ቀርቶ ግለሰብም የለም። ልብ እና ኩላሊት የሚመረምረው አምላክ አላህ ያውቀዋል። የእኛን ቅንነት እና ገራገርነት። ስለዚህም አማራ ሊታረቅም ብሎ አቤቱታ የሚቀርብለት ግለሰብ፤፥ተቋም ማህበረሰብ የለውም። ይልቁንም ከሙሉ የህሊና ካሳ ጋር ሊካስ የሚገባው የአማራ ህዝብ ነው። በዳዮቹ መበደላቸውን አቁመው ይቅርታ ጠይቀው ሊክሱት ይገባል። የመንፈስ ካሳ። ውሃ በቀጠነ ማቱ የሚወርደው በአማራ ላይ ነው። ነፃ አውጪወች ሲደራጁ የማኒፌስቷቸው ጭብጥ ፀረ አማራነት ነው። ስለዚህ ይህን ጭብጥ ቢተውት ተቋማቸው የሁሉም ይፈርሳል። እርቀ ሰላሙ ይህ እና ይህ ብቻ ይሆናል።   ህወሃት ሙሉ 47 ዓመት ሚዲያው ሊቃውንቱ ዛሬም ፀረ አማራ ዲስኩር ነው። ጦርነት የከፈተው የ፬ኪሎው ኦነግ ሆኖ ዛሬም ናዳ የሚለቀቀው በአማራ ላይ ነው። ኦነግ ፬ ኪሎ የንጉሦችን ንጉሥ የአጤ ሚኒሊክን ቤተመንግሥት በአማራ ትጋት እና ሙሉ ድምጽ አግኝቶ ዛሬም አማራ ላይ ዛሩ እንደተደረረ ነው። የከተማ ተቋማቱ፤ የጫንካ ክንፋ ውግዘቱም ምንጠራውም አማራ እና ጠረነ አማራ ብቻ ነው። የኦነግ ሊቃውንት የላንቃቸው ጠበለ ጣዲቅ ይህው ፀረ አማራነት ነው። ተማሩ አልተማሩ አንድ አይነት ማት ይፈሳል። እዬረሸኑም፤ እ

ቅዱስ ሲኖዶስ ስንቱን የቅድስና እረኝነቱን አግልሎ ሊዘልቀው ይሆን?

ምስል
      ቅዱስ ሲኖዶስ ስንቱን የቅድስና እረኝነቱን አግልሎ ሊዘልቀው ይሆን? "ከነገር፡ ሁሉ፡ አስቀድሞ፡ ሄኖክ፡ ተሠወረ። ከሰውም፡ ልጆች፡ በተሠወረበት፡ ቦታ፡ ሳለ፡ የሚያውቀው፡ አልነበረም፡ ይሙት፡ ይዳንም፡ የሚያውቅ፡ የለም። ሥራው፡ ሁሉ፡ በተሠወረበት፡ ወራት፡ በቅዳሴያቸው፡ ከሚተጉ፡ መላዕክት ጋርና፤ ከቅዱሳን ጋር ነበር። (መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፬ ቁ ከ፩ - ፫) የፀጋ // የበረከት /// የምርቃት /// የቅብዓ // የትንግርት// የትንቢት// የመሰጠት// የምኞት // የራዕይ// የቅዱሳን// የደናግል፤ የሰማዕታት፦ ባዕት ፍልስፍናዊት ኢትዮጵያ የእኛ! ቅድስ ሲኖዶስ ዬቅዱስ ላሊበላን ብጽዕና፤ ልዕልና ሞገሥ እና ግርማ አግልሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ የቅኔው ደብረ ኤልያስ ገዳምን ሰማዕትነት አግልሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ የቅዱስ ደብረ ማርቆስን #ካስማነት አግልሏል። እንዲህ በሁለገብ ሸፍት ቅድስናው ሲስተጓጎል??? ዝምታ??? ቅዱስ ሲኖዶስ እያንዳንዱ በዕት የሊቀ - ሊቃውንት መፈጠሪያ የሆኑትን መላ የአማራ ክልል ገጠራም ቅዱስ ባድማወችን አግልሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ የሻሸመኔን ሰማዕታት ገድል እና ታምራትን አግልሏል። ከዕጬጌው ጀምሮ ብፁዓኑ እዛው ሄደው ጉባኤ ሊያካሂዱ ይገባ ነበር። ግን በነበር ተከዘነ። ይህ ማለት ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደራዊ ተግባሩን እንጂ የዶግማውን መተግበሪያ ቋቱን በሚመለከት ዝሏል። ለዚህም ነው ብፁዓንወቅዱሳን አባቶቻችን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚገናኙበትን መሰላል መዘርጋት ግድ የሚላቻው። የወሉ ወይንም የጋራው ሱባኤ ሳይሆን ለእኔ ከሊቅ እስከ ደቂቅ አቨው ብፁዓን ሊቀ ጳጳሳት ገዳምን በሱባኤ የሚያገኙበት ትልም ሊኖራቸው እንደሚገባ ይሰማኛል። የተከበሩ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ የንስኃ አባት ሊሆኑ አይችሉም! ፈጽሞ! ግን ኃይማኖትስ አ

19.11.2020 ረመጥ ነው ወልቃይትወጠገዴ።

ምስል
  ረመጥ ነው ወልቃይትወጠገዴ።   እፍታ። በድጋሚ ለጥ ብዬ እጅ እነሳለሁኝ። ህወሃት ከድል እስከ ውድቀቱ የጎንደር ሁነት ምን ነበር የሚለውን የነበርኩበትን በምልሰት ቅኝት አቅርቤያለሁ። ማንበብ ፀጋቸው ለሆኑ ወገኖቼ፣ ታሪክን እንደ አግባቡ ለሚያዳምጡ፣ ለሚይዙ ወገኖቼ፣ በጭልፋ ፕሮፖጋንዳ የወልቃይትጠገዴ ጉዳይ ላይ ለሚያላግጠው የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥትም ነገረ ሥራው የሳሙና አረፋ ነውና ውስጤን ያይ ዘንድ የፃፍኩት ነው። ልቀት። የወልቃይት እና የጠገዴ ጥያቄ ከአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ዘመን መባቻ ብቻ የሚመስላቸው አሉ። ህወሃት ጫካ ሆኖ ሲወስን ከህወሃት ጋር የነበሩ የጠገዴ፣ የወልቃይት ልጆች አፈንግጠው ወጥተው በለመዱት ዱር ገደል ሲታገሉ ነበር። ውጭ የወጡትም ለአንዲት ሰከንድ ከተጋድሏቸው ዝንፍ አላሉም። በዘመነ ህወሃት ረጅሙ ተጋድሎ ጋር የዘለቅን በርካታ ጎንደሬዎች የህሊናችን ሞተር እርስታችን ነው። ይህ ሊታወቅ ይገባል። ውስጣችን የማይበርድ ረመጥ አለ። የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ሲነሳ አቶ አሥራት አብርኃ የገብያ ግርግር ሲሉት ወጥቼ ቅጥ አስይዠዋለሁ። ማንነት ሸቀጥ አይደለም በገብያ ህግ የሚተዳደር። ድፍረታቸው ልክ ስላልነበረው ነበር ወጥቼ የሞገትኳቸው በደጉ ሳተናው ድህረ ገፅ። ኢሳትም ሳቢያ እያለ ሲያላግጥ፣ ግንቦት ሰባትም የነፃነት ኃይል ተጋድሎ እያለ ሲለነቁጥ ልካቸውን እንዲይዙ የብዕር ቦንብ ተልኮላቸዋል። ጠቅላዩ ወደ ሥልጣን ሳይመጡ ጭምጭምታ ሳይኖር በዝርዝር ለዛን ጊዜው የኦህዴድ ሥራ አስፈፃሚ የፅህፈት ቤት ኃላፊ፣ ለዛሬው ጠቅላይ በስክነት አስረድቻቸዋለሁኝ። የወልቃይትወጠገዴ ጉዳይ አገር በማስቀጠል ጉዳይ ምክንያታዊ ነው። ገዢ መሬት ነው። ህወሃት ሞተ ተብሎ ማወጅ የሚቻለውም ይህ ርስት ወደ ባለቤቱ ሲመለስ ብቻ ነው። በዚ

31.10.2020

ምስል
  በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ። አሜን።     "የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፣ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" ምሳሌ 16/9 የነግህ ፀሎት። 1) የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ እንዲገባ መሻት። 2) የአማራ ክልል የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎች ከክልላቸው ውጪ ወደ ሌላ ክልል እንዳይመደቡ መሻት። 3) በኦህዴድ ኦነግ የበቀል መሥመር እንደ ወጡ የቀሩት የአማራ እጩ ሊቃናት የደንቢደሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን መጨረሻ ለማወቅ መሻት። 4) ሰው አጥፊው የህወሃትወኦነግ ህገ መንግሥት ሙሉለሙሉ እንዲቀዬር መሻት። 5) መርዛማው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ ይጠፋ ዘንድ መፀለይ። 6) የሥርዓት ለውጥን መሻት። ወሥብኃት ለእግዚአብሔር። ወስብኃት ለእግዚአብሔር።

19.11.2019 የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ ህወሃት ነው።

  የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ ህወሃት ነው። የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ ህወሃት ነው። ይህን ግርባው ብአዴን፣ ተደማሪው ግንቦት ሰባት እስከ ቲፎዞው፣ ሚዲያው ኢሳት፣ የኦዳው ኢንፓዬር መለከት ነፊ የአንድ አፍታ አወያይ ጦማሪ ስዩም ተሾመ ቀጥ ሰጥ ለጥ ብለው የማፏሸኪያ ብር አንባር በመሆን ያስፈፅማሉ። ሁሉም ሰው ህሊና ያለው ሁሉ ከማፏሸኪያ እንቅልፍነት ያወጣው ዘንድ አምላኩን ይማጠን። እኔ አፈንጋጯ ሥርጉተ ሥላሴ የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ፣ እንቅልፍ አማጭ ባለመሆኔ እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ። ህወሃትን በሚመለከት የራሱን ድርጅት በቅጡ መምራት ያልቻለው የአብይ መንፈስ እኔን በዛ ቦይ ውስጥ ማስገር ፈፅሞ አይችልም። ፕሮፖጋንዲስትም አልፈልግም። ቀስቃሽም አያሰኜኝም። ምክንያት። ገና በልጅነት ዕድሜዬ በተደራጀ ፓርቲ በከፍተኛ ህዝባዊ የኃላፊነት ሆኜ ታግዬዋለሁ። ጫካውንም ካቴናውንም ስደቱንም አውቀዋለሁ። እነሱ ከህወኃት የሥልጣን ፍርፋሪ ለቃሚ ኦፋ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ ሥርጉትሻ ህወሃትን ሞግታለች። የራሷም ወርቅ የሆነ አሻራ ከእነ ሙሉ ማስረጃው አላት። አሁን እነሱም ከፖለቲካ ድርጅት ተቆጥረው የጭካኔያቸው መለበጃ አዲስ ፀረ ህወሃት ዘመቻ ቢጀምሩ ሸማ በዬዘርፋ እንደሚለበስ ሥርጉተ ሥላሴ ጠንቅቃ ታውቃለች። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አንዲት ቀን ድርጅታቸውን መምራት ሳይችሉ ነው በአማራ አቅም የሚፎክሩት፣ የሚያቅራሩት። መቼ ነው እሳቸው ሙሉ ኢትዮጵያን የመሩት፣ ያስተዳደሩት? መቼ ይነገረና። እሩብ አገር እንኳን ይመራሉን? ይህ አቅም ሲያንሳቸው በሴራ ፖለቲካ፤ በህዝብ ሰቆቃ መንበራቸው የማይደፈር አድርገው ለማሳዬት ይጥራሉ። ውሽልሽል። ጉዳዩ የውሽማ ሞት ነው። ገናና አገር እንዲህ ላርባ መሆን እንኳን ባልቻለ አቅም ልትመራ አይገባትም። ህወሃት አረረም መረረም 27 አመት