አማራ ዘሩ እንዲጠፋ የተወሰነበት ጭምት ህዝብ ነው። 25.11.2020

 

አማራ ዘሩ እንዲጠፋ የተወሰነበት ጭምት ህዝብ ነው።
አባ ቅንዬ የአማራ ህዝብ የዘመኑን ባህሬ በማንበብ የህሊናዊነት አድማሱን ሊያሰፋ ይገባል።
ከሩትን ተግባር ወጥቶ ባለ እርስትነቱን በሉላዊ ህግጋት ማስከበር ግድ ይለዋል። ሰርክ የቹቻ እና የሰኔል መሰናዶ ሊሰለቸው ይገባል።
ዘወትር ሊቃናቱ ተለይተው ለካቴና፣ ለባሩድ፣ ለካራ፣ ለሳንጃ፣ ለሜጫ፣ ለእሳት ሲዳረጉ ለምን ብሎ እራሱን ይፈትሽ አማራ! በቃኝን ለምርምር ያውል። በስተቀር የኩርድሽ ዕጣ ክፍሉ ይሆናል።
ማንም እንዳይኖረው ነው ሊቃናቱ በረድፍ የተረሸኑት፣ ልቅምቅም ብለው አሁንም ለካቴና የተሸለሙት የትውልዱ ተስፋ ቀና እንዳይል፣ ተስፋ ቢስ እንዲሆን ነው የታለመው። የሚከወነው። አለኝታ፣ ጋሻ እንዳይኖረው ማድረግ ሙሉ ፕሮጀክት ነው የአገዛዙ።
ስለዚህም የአማራ ህዝብ በማስተዋል መራመድ፣ አቅሙን ቆጥቦ ማስተዳደር፣ ከፈጣሪ ከአላህ ጋር መምከር ይኖርበታል።
ቂም፣ በቀል የፀነሰ ዕለት ከሰዋዊ ውርጅብኝ በላይ ሰማያዊ እሳት ይወርድበታል። ሰው ሆኖ የመፈጠሩ ሚስጢር ፈርኃ እግዚአብሔር፣ ፈርኃ አላህ መሆኑን ሆኖ በመገኘት፣ ማክበር፣ ማስከበር ይኖርበታል።
ጥላቻ አመድ፣ ክሰል፣ ትቢያ ነው። እሱ አልተፈጠረበትም። እና ለሰከንድ እንዳያስጠጋው። በስተቀር ምርቃቱ ይነሳል። ሁላችንንም ያጠፋናል። መክሊታችን ይሰረዛል። ሰብዕነታችን ፍግ ይሆናል። አደራ።
ከዚህ ባሻገር ባለው ተጋድሎ ቆርጦ ትግል ውስጥ መግባት ይኖርበታል። ቀን እዬቆጠረ ፀረ አማራ፣ ፀረ ተፈጥሮ፣ ፀረ ሰው አዬሩ ይጠራል።
ሥራው የመዳህኒዓለም ነውና። ከሰብዕነት ተርታ ለጠፋት ፈጣሪ የንሥኃ ጊዜ ይስጣቸው። አሜን።
እኛ የተሰጠንን መልካምነት ይዘን የሚጠሉን ክፋነትን ሰንቀው ቢጓዙ ችሎቱ የእዮር ነው። ካለ ካህሊ - ሥልጣናችን ዘው አንበል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergite©Selassie
ኃራም ጥላቻ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።