ልጥፎች

ከጃንዩወሪ 15, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የደብርዬ¡ ምሾ ይሁን፤ የአስተዛዛኞች ዓላማ እና ግብ ግን አልገብቶም!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዝብር ቅር ቅ። „አቤቱ እጅህ ከፍ ከፍ አለች፤ አላዩምም፤ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ እሳትም ጠላቶችህን ትበላላች“  ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፮ ቁጥር ፲፩  ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 15.01.2019 ከእመ ብዙሃን። ·        ማ ሟሻ … ውዶች ክብሮቼ እነ ናፍቆት የአገሬ ልጆች እንዴት ናችሁ? ደህን ናችሁ ወይ? ውይ ዛሬ ፏ ፍንተው ብሏለኝ አዬሩ፤ እትጌ ልዕልተይ ጠሐይ መጥታ ትፍነሸነሻለች - ታፍነሸንሻለች፤ ለነገሩ የዚህ ዓመት ክረምት ቀለል ያለ ነው። ምን ትፈሪያለሽ ብባል ክረምትን ነው የምላችሁ፤ አገር ቤት እያለሁ አብሶ አዲስ አባባ ኗሪ በነበርኩበት ጊዜ ክረምት እህቶቼ በፈረቃ ይመጡልኝ ነበር፤ ሆዴ ርብሽብሽ ነው የሚለው፤ በተለይ ነጎድጓድ አልወድም። በዬአራት ዓመቱ አንድ ጊዜ እንዲህ የያዝነው ዘመን ዓይነት ሲመጣ ደግሞ ሳንክ አይጠፋም። ብቻ ጠሐይ ካለች ተስፋ ነው። ተስፋ ደግሞ ያጀግናል። ·          ተዚህ ላይ ዕለቱንስ አብረን ብናዘክር። ዛሬ ጥር ሥላሴ ነው። የጎንደሪት የልጅነት ጊዜ ታወሰኝ፤ የዋሾ ሜዳ፤ የማርገጃው ወይራ…  ዓይኔ ዕንባ አቀረረ። አያቶቼ ነዳይን ፍሪዳ አርዳው በቁርጥ የገና ጾምን እንዲፈቱ የሚያደርጉበት ዕለት ነበር ዛሬ - ትውፊቱ እንደዛ ነበር። ሸንበቆው ተሰንጥቆ፤ እንደ ካራ ይዘጋጃል፤ ጤፍ እንጀራው ዘንጠፍ ብሎ ታጥፎ በአዋዜ ቁርጥ ለሚፈልግ ቁርጥ፤ ጥብስ ለሚፈልግ ጥብስ አደግድገው መላከብርሃናቱ አያቴ እና ታናሽ ወንድማቸውም መላከብርሃን ነው አሱም እንግዶቻቸውን ነዳያን ያስተናግዳሉ፤ እህታማቾች ደግሞ ለቅዳሴ የመጣውን ቤት ለእንግዳ በማለት ደስ ብሏቸው ያሰተናግዳ