ልጥፎች

የአካዳሚ ነፃነት የትውልድ አውንታዊ ብቅል ነው!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  መ ሠ ረት። „የፃድቃን መንገድ ቅን ናት፤ አንተ ቅን የሆንህ የፃድቅናንን መንገድ ታቃናለህ።“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፭ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ© ሥላሴ Seregute©Selassie 14.01.2019 ከእመ ዝምታ - ከሲዊዘርላንድ። ·        እ ፍታ። እንዴት አመሻችሁ ውዶቼ ደህና ናችሁ ወይ? ይህቺ እንደነፍሴ የምወዳት አገር እምዝምታ ሲዊዝሻ ጸጥታውን እዬመገበችኝ ነፍሴን ታፍነሽንሸኛለች። እኔ ግርግር ጩኽት - ሁካታ-  የአገር ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አልፈቅደውም /ሰላማዊ ስልፉ/። ድምጽ የባዘበት ቦታ ይጨንቀኛል። አንድም ከቤቴ ድምጹ ከፍ ብሎ የሚሰማ ነገር የለም። እቃ ሲታጠብ በጸጥታ፤ በር ሲከፈትም ሲዘጋም በዝግታ ነው። ራሱ ጎረቤቶቼ ስለመኖሬ ወይንም ስላለመኖሬ የሚያውቁት ምንም ነገር የለም። ጸጥ ረጭ። እናላችሁ ሲዊዚሻን ሳስባት ለእኔ ተብላ የተፈጠረች ይመስለኛል። አብሶ እኔ ያለሁበት ቪኒቲ። ቪንቲ የቁልምጥ ስሙ ነው። ከዚህ ከተማ የተፈጠሩትም የገጠሙኝ ሁሉ ቤተሰብዐው ስብዕና ያላቸው ናቸው። ይህችን እንደ ወግ ቢጤ ካደርኩኝ ስለዛሬው ቁም ነገር ልንገራችሁ … ትውልድ። ·        ትውልድ። ትንተና የለውም እንዲሁ በመደዴው ስሄድበት ግን ትውልድ በመኖር ውስጥ ያለ የአገር መኖር ማለት ነው። አገር ለማኖር ደግሞ የትውልድ መኖር ብቻውን በቂ ነው ሲባል ጥማድ በሬ ገዝቶ ማሳ የሌለው ገበሬ ይሆናል። እና የትውልዱ መኖር መበራከት ብቻውን አገርን የማስቀጥል አቅም ሊኖረው አይችለም። ማሳው በበጎ በፈቃደኝነት፤ በባለቤትንት፤ በታማኝነት፤ በምክንያታዊነት መታነጽ ካልቻለ። ለዚህ ደግሞ አራት ተቋማት ወሳኝ ናቸው።   አንደኛው ቤተሰብ ወላጆች ወይንም

እንደ ሴት እንደ እህትም እንደ እናት እንደ ዜጋም ምን ይሰማችኋል?

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።    እንደ ሴት እንደ እህትም እንደ እናት እንደ ዜጋም ምን ይሰማችኋል ? „ በዚያ ቀን እግዚአብሔር ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን፣   ጠማማውን እባብ ሌዋታንን በጠንካራ በታላቅም   በብርቱም ሰይፍ ይቀጠዋል በባህርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል። “ ትንቢተ ኢሳያስ ፳፯ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ  Sergute©Selassie  14.01.2019 ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? የኢትዮጵያ እናቶች መቼ ይሆን ዎህ የሚሉት ይሆን? መቼ ይሆን የሚያርፉት - ከሰቀቀን? መቼ ይሆን ከሞት በመለስ ባሉ የልጆቻቸው የመኖር ውጤታማ፤ ስኬታማ ትርጎሞች እያዩ እፎይ የሚሉት? ከቶ መቼ ይሆን ያቺ ምስኪን የኢትዮጵያ እናት ከጉንጯ አልፎ ደረቷን በሚያርሰው የህሊና ወራጅ የዕንባ ቋት ተላቃ የልጆቿን ቁም ነገር አይታ ነገን በመልካምነት የምታስበው? መቼ ይሆን የኢትዮጵያ እናቶች ከስጋት የሚወጡት? የኢትዮጵያ መንግሥት አንድ ሰው በቁም እስር ማስቀመጥ ተስኖት አሁንም የወለጋ እናቶች ያለቅሳሉ። የወ/ሮ ታደሉ እንባ በቃህ እንዳይባል አንድ የዘመን እሾኽ ተፈጥሮበት አሁንም ዋይታ በረከተ።  አሁን ያን ሁሉ የሬቻ ዘግናኝ መከራ ያዬ፤ ያን ሁሉ የካቴና ዘመን ያሳለፈ፤ ያን ሁሉ መገፋት እና የስላቅ ዘመን በቃህ የተባለ ነፍስ እንደገና በትግሉ ባመጣው ነፃነት መጠቀም ሲገባው በአውሮፕላን ጥቃት ተፈጸመበት መባል ሲሰማ እኔን ሥርጉተን እንደ ሴት፤ እንደ እህት፤ እንደ እናት፤ እንደ ዜጋም ከሬቻው ጭፍጫፋ ባለነስ  ውስጤ እርር ኩምትር ብሏል።   ደግሞም ከጅምሩ „ትጥቅ አልፈታም አላለም ተብሎ በተንታኞች ሲተረጎም፤ በመንግሥትም ለጨዋታ ሟሟያ ነው ሲባል መጪ

ዝበት ወይንስ ስክነት?

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዝበት ? ስክነት ? „በዓመታት መካከል ትታወቅ፤  በማዓት ጊዜ ምህረትን አስብ“ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·        ማነው ጥፈተኛው? ማነውስ ይቅርታ ጠያቄውስ? https://www.youtube.com/watch?v=a7aWV6r9Q6k&t=3s ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚነሱ ግጭቶች ላይ የምሁራን አስተያየት Fana Television Published on Jan 10, 2019 ጋዜጠኛ አቶ አዳም ታደስ /አወያይ/ ·        ማካሄጃ። "ፕ /" አባባው አያሌው በአማራ ቴሌቪዥን አሁን ከሆነ ይቀርባሉ ለቃለ ምልልስ፤ ያው እሳቸው የሚፈ ለጉ ት የአማራ ብሄርተኝንት ጎልቶ ሲወጣ ወይንም ዩንቨርስቲዎች ችግር ተከሰተ ሲባል ብቻ ነው። ከዚህ ያለፈ፤ ከዚህ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ተወክለው አይተን አናውቅም። ሌላው ቀርቶ ከታሪክም ከጥበብም አንጻር ብርቱ ሰው በሚያስፍልጋቸው አገራዊ ጉዳዮችም እንዲሁ ያን የመሰለ በፍጹም ሁኔታ የሚመሰጠው ብቃታቸው እዬባከነ ነው የሚታዬው የተገባውን ቦታ አላገኝም እንደማለት። ውጭ ያሉ ሊቃናት አገር እንዲገቡ ሲፈለግ አገር ውስጥ ላሉት ሊቃነት ያላቸውን አንጡራ ሃብት ጥቅም ላይ ለማዋል ያለው ዕድምታ ፈተናው አይሎ አያለሁኝ። መሰረታዊ ምክንያቱ ብቃት አቅም እውቅት ሳይሆን መለኪያው የፖለቲካ ድርጅት አባልነት ስለሆነ፤ የኮታ ጉዳይ ስለሆነ፤ ይህ ብቻ ነው እንዳልል ደግሞ ከዚህ የወጡ ሹመቶች እና ዕውቅናዎች ሲሰጡ ደግሞ አያለሁኝ፤ በተጨማሪም በምደባም እንዲሁ የሥራ ድልድል ፈንገጥ ያለ ሁኔታም አልፎ አልፎ አያለሁኝ።