"ሉዕላዊ አገር እንጂ ሉዕላዊ ክልል የለም።" ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከተናገሩት ...
እንኳን ደህና መጡልኝ። „ሉዕላዊ አገር እንጂ ሉዕላዊ ክልል የለም። እንደ አፈዎ ያድርግልን ይሁንልን እስኪ … „ ጋሜል። አንዳልወጣ በዙሪያ ቅጥር ሠራብኝ። ሰንሰለቴንም አከበደ።“ ሰቆቃው ኤርመያስ ፫ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 01.02.2019 ከእመ ዝምታ ኪሲዊዝሻ። „ሉዕላዊ አገር እንጂ ሉዑላዊ ክልል የለም“ ይህ ከዛሬው ከጠ/ሚር አብይ አህመድ መልስ የተወሰደ ነው። · እንደ እኔ ዕይታ እና ተደሞ ልሄድበት ወደድኩኝ። እንዲህ … ይህ የሆነበት መሰረታዊ ጉዳይ አለ። ይህ መሰረታዊ ጉዳይ ትግራይ እንደ ሉዑላዊት አገርነት ነው 27 ዓመት የቆዬችው። ቀደም ባለው ጊዜ እኔ ስጽፍ ተጋድሎው ኢትዮጵያዊነት እና ትግራዊነት ነው እል ነበር። በጣም ለረጅም ጊዜ ስጽፍ ተጋድሎውን ስምለከተው የነበረው ትግራዊነት ኢትዮጵያዊነት ተክቶ ለመውጣት ስለመሆኑ ነበር የሚረዳኝ። ነውም ። ሂደቱም ሁኔታው የነበረው ኢትዮጵያ ትታይ የነበረው እንደጠላት አገር ነው ። ቅኝ እንደተገዛች አገር። የህወሃት ማንፌስቶ ጸረ ኢትዮጵያ ነው ልክ እንደ ኦነጉ። ኦነግ ሥልጣኑን ቢያገኝም ከቻለ በዚህ መልክ ህወሃት 27 ዓመት በነበረበት ልክ ካልቻለ ደግሞ የራሱን አገር መፍጠር ነው። ህልሙም ዕውነቱም ይኸው ነው። መንትዮሹ መንገዳቸው ይኸው ነው። ባዶ ቤት አግኝተው ጊዜያዊ ጋብቻ የፈጸሙትም በዛ መልክ ነበር። አጅሬው ወያኔ ለቀን ያደረሰውን ሻብያንም፤ ሽፋን ሰጪውንም ኦነግንም በጊዜ ሸኝቶ በለሱን...