ልጥፎች
ከጁላይ 30, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ
የፔጄን ህግ መጠበቅ ግዴታ ነው። ዘለፋ እና ማዋረድም #ማቆም ግዴታ ነው።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የፔጄን ህግ መጠበቅ ግዴታ ነው። ዘለፋ እና ማዋረድም #ማቆም ግዴታ ነው። "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ።" ከእኔ ፔጅ ላይ #silent Discrimnation & #silent Emotional neglation ፈጽሞ አይፈቀድም። ዛሬ በውል ተደራጅተው የመጡ የዚህ ስሜት ተጋሪወች ቤታችን አጉድፈውታል። ሃሳብን አቅርቦ በሃሳብ እኔን መሞገት ይቻላል። አቅሙ ከኖረ። በስተቀር ግን በሰው ልጅ በገጽ አቀማመጥ፤ በዕድሜ፦ በፆታ፤ በሃይማኖት፤ በቆዳ ቀለም ምንም ዓይነት ተጽዕኖ ለማሳደር መሞከር ፈጽሞ አልፈቅድም። በተጨማሪም ስድብ፤ ማዋረድ፤ ነውረኛ ቃላትን እና ሐረጋትን መጠቀምም አልፈቅድም። ለምን ብቻዬን አልቀርም። አይደለም ከእኔ ፔጅ በጓደኞቼ፤ በተከታዮቼ ፔጅ ላይም #ነውረኛ ነገር ካዬሁ መልስ አያስፈልግም #መራራ #ስንብት ይሆናል። ጋዜጠኛ፤ ፀሐፊ እና ሞጋች አቶ ታዲዮስ ታንቱ ወገኔ ናቸው። በዚህ ዕድሜያቸው #በበቀል #መቀጥቀጣቸው ውስጤን ያሳምመዋል። በማረፊያቸው ጊዜ፤ በመመስገኛ ጊዚያቸው እንዲህ #የካቴና #ቀለብ ሲሆኑ እንደ ትውልድ ያንገበግበኛል። የማይስማማ ሃሳብ ካነሱ መሞገት እንጂ ሥልጣን አለኝ ተብሎ እንዲህ #በበቀል ማንገላታት የተገባ አይደለም። ስንት እና ስንት አገር እና ትውልድን ማኒፌስቶ ነድፈው #ገዝተው ፤ #ገድለው ፤ #አስረው ፤ #አግተው ህዝብ #አሰቃይተው እንኳን በሰላም እዬኖሩ ነው። ማንም ፍፁም አይደለም። ግድፈት ተፈጥሯዊ ነው። የማይገድፍ #ዕቃ መሆን አለበት። ግድፈት እንኳን ቢኖር በዚህ መልክ መበቀል #የሥልጣኔ ማነስ ነው። በሌላ በኩል #የበታችነት ስሜትም ነው። በራስ መተማመን ሲያንስ #ምቀኝነት ፦ #ቅናት እና #በቀለኝነት አይቀሬ ነው። ...