የፔጄን ህግ መጠበቅ ግዴታ ነው። ዘለፋ እና ማዋረድም #ማቆም ግዴታ ነው።

 

የፔጄን ህግ መጠበቅ ግዴታ ነው። ዘለፋ እና ማዋረድም #ማቆም ግዴታ ነው።
 
"ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ።"
 May be an image of 1 person and text
ከእኔ ፔጅ ላይ #silent Discrimnation & #silent Emotional neglation ፈጽሞ አይፈቀድም። ዛሬ በውል ተደራጅተው የመጡ የዚህ ስሜት ተጋሪወች ቤታችን አጉድፈውታል። ሃሳብን አቅርቦ በሃሳብ እኔን መሞገት ይቻላል። አቅሙ ከኖረ። በስተቀር ግን በሰው ልጅ በገጽ አቀማመጥ፤ በዕድሜ፦ በፆታ፤ በሃይማኖት፤ በቆዳ ቀለም ምንም ዓይነት ተጽዕኖ ለማሳደር መሞከር ፈጽሞ አልፈቅድም።
 
በተጨማሪም ስድብ፤ ማዋረድ፤ ነውረኛ ቃላትን እና ሐረጋትን መጠቀምም አልፈቅድም። ለምን ብቻዬን አልቀርም። አይደለም ከእኔ ፔጅ በጓደኞቼ፤ በተከታዮቼ ፔጅ ላይም #ነውረኛ ነገር ካዬሁ መልስ አያስፈልግም #መራራ #ስንብት ይሆናል። ጋዜጠኛ፤ ፀሐፊ እና ሞጋች አቶ ታዲዮስ ታንቱ ወገኔ ናቸው።
 
በዚህ ዕድሜያቸው #በበቀል #መቀጥቀጣቸው ውስጤን ያሳምመዋል። በማረፊያቸው ጊዜ፤ በመመስገኛ ጊዚያቸው እንዲህ #የካቴና #ቀለብ ሲሆኑ እንደ ትውልድ ያንገበግበኛል። የማይስማማ ሃሳብ ካነሱ መሞገት እንጂ ሥልጣን አለኝ ተብሎ እንዲህ #በበቀል ማንገላታት የተገባ አይደለም። 
 
ስንት እና ስንት አገር እና ትውልድን ማኒፌስቶ ነድፈው #ገዝተው#ገድለው#አስረው#አግተው ህዝብ #አሰቃይተው እንኳን በሰላም እዬኖሩ ነው። ማንም ፍፁም አይደለም። ግድፈት ተፈጥሯዊ ነው። የማይገድፍ #ዕቃ መሆን አለበት። ግድፈት እንኳን ቢኖር በዚህ መልክ መበቀል #የሥልጣኔ ማነስ ነው። በሌላ በኩል #የበታችነት ስሜትም ነው። በራስ መተማመን ሲያንስ #ምቀኝነት#ቅናት እና #በቀለኝነት አይቀሬ ነው።
 
ለዛውም አገር እዬገዙ ህዝብ እያስተዳደሩ ከአንድ በዕድሜ ከገፋ አዛውንት ጋር ይህን ያህል ጉግስ አይገባኝም። እንዲገባኝም አልፈቅድም። የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና ሞታቸው ተጠበቀ እግዚአብሄር ደግ አምላክ ነው አሉ በሕይወት። እኒህ ለአመኑበት ዓላማ ትጉህ አዛውንት አንድ ነገር ቢሆኑ #እርግማን ይሆናል። 
 
መታሠራቸው አልበቃ ብሎ ደግሞ በሳቸው የአፈጣጠር ፀጋ መሳለቅ፤ ማላገጥ ከዚህ ቤት አይፈቀድም። እኔ እንዴት ዓይነት ቤተሰብ እንደሚታደግ ግራ ይገባኛል። ኢትዮጵያ እኮ አፈጣጠሯ በሰብ ክብር በፈርኃ አላህ እና እግዚአብሄር ነው። አሻቅቦ መናገር እኔ በተፈጠርኩበት በዓት ነውር ነው። አይፈቀድም። 
 
ብዙ የረቀቁ የሰለጠኑ ባህላት፤ ወጋወጎች እና ልማዶች ኢትዮጵያችን አላት። ያን እዬጠቀጠቁ እና እያወረዱ ከእኔ ጋር መቀጠል አይፈቀድም። ፈጽሞ። ለዛውም እስር ላይ ያሉ፤ አዛውንት፤ የአንጀት በሽተኛ።
 
እረፋ። ህግ አትተላለፋ። መታረም ሳይኖር ነገን ማግኜት አይቻልም። ቤተሰብ ልጅ ከኖረም እንዴት ልታስተዳድሩት ይሆን? ከሁሉ የሚከፋው አክሰሱ ላላቸው ታዳጊወች ምን እያስተማራችሁ ነው? በእኔ ፔጅ ይህ ቀልዳ ቀልድ፤ ይህ ሰብን መዳፈር አይፈቀድም። ፈጽሞ። አቅሙ ያለው ሃሳቡን ይዞ ይምጣ እንሟገት። የወጣልኝ ሞጋች ነኝ እኮ። 
 
ዝምታዬ #ዝም በማለት የሚድን ክስተት ከኖረ በሚል ነው። #ዝምም መልስም ስለሆነ። እንጂ #ሙግት ጥሪዬም የኖርኩበትም ነው። በአገሬ ፖለቲካ፤ በአፍ መፍቻ በአማርኛ #ቋንቋዬ ምንም ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገኝም። ፖለቲካ እኮ የሠራሁበት ነው። ከገጠር እስከ ከተማ፤ ከአገር እስከ ስደት። 
 
የሆነ ሆኖ ፔጁ የማይመቻችሁ በሰላም ስንብት ማድረግ መብት ነው። እስረኛን ለማዋረድ መኮልኮል ግን አይፈቀድም። ከእስር እስኪፈቱ እኔ አጮኽላቸዋለሁኝ። ይህ አይቀሬ ነው። የሳቸውን አፈጣጠር ስታቃልሉ፤ ስታጣጥሉ ሚሊዮኖችንም ስለመሆኑ፤ ዕምነት ካላችሁም አማላካችን አላኃችን ማቃለል ስለመሆኑ ልታውቁት ይገባል።
 
 የትኛው ሰባዕዊ አያያዝ የሚያስመካ ሆኖ ነው ከኢ ሰባዕዊነት ጎን ተሰልፋችሁ ያን እምትከበክቡ? በቀል እኮ አሳፋሪ ድርጊት ነው። #ጎግማነት#ቆባነትም ነው።
 
ማህበረ ቅንነት እንዴት ናችሁ። ኑሩልኝ።
 ቸር እደሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
31/07/924
 
ሰውነት ይከበር!
ቅድሚያ ለሰው ልጆች ክብር!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።